>
5:14 pm - Saturday April 20, 1715

አብርሀ ደስታ ነገ ፍ/ቤት ይቀርባል።

Abrha Desta 3የአረና ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኅላፊ የሆነው አብርሀ ደስታ ከ9 ቀናት እስር በኋላ ነገ ሀሙስ ጁላይ 17 ቀን ከጠዋቱ 10 ሰዓት ላይ ፍ/ቤት እንደሚቀርብ ተገልጿል።
ወጣቱ ፖለቲከኛና የዩንቨርስቲ መምህር ከሳምንት በፊት ጁላይ 8 ቀን መቀሌ ውስጥ በፖሊሶች እየተደበደበ መወሰዱ ከተመሰከረ ጀምሮ እስካሁን ዳኛ ፊት የመቅረብ ዕድል አላገኘም። ከትግራይ ወደ አዲስ አበባ ተልኮ በማዕካላዊ ዕስር ቤት የሰነበተው አብርሀ ጁላይ 10 ቀን ባልተለመደ ሁኔታ ከአመሻሹ 6 ሰዓት ላይ ወደ ፍ/ቤት መወሰዱ ቢታወስም ዳኛ ፊት እንዲቀርብ ያለመደረጉ ግን ተረጋግጧል። በወቅቱ ሰውነቱ ላይ ከታየው መጎሳቆል በመነሳት ተጨማሪ ድብደባ ሳይፈጸምበት እንዳልቀር የትግል አጋሮቹ ጥርጣሬያቸውን አሰምተው ነበር።
አብርሀ ደስታ በተለይም በፌስ ቡክ አማካኝነት አካባቢያዊ ዜናዎችንና የተለያዩ አመለካከቶቹን በማቅረብ ሰፊ ዝና ያተረፈ ደፋር ፖለቲከኛ መሆኑ ይታወቃል።
በተመሳሳይ መልኩ በሰሞንተኛው ወጣት የተቃዋሚ ፓርቲ የአመራር አባላትን የማሰር ዘመቻ የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የሆነው ሀብታሙ አያሌው፣ የድርጅት ጉዳይ ሀላፊው ዳንኤል ሺበሺና የሰማያዊ ፓርቲ የምክር ቤቱ ምክትል ሰብሳቢ አቶ የሺዋስ አሰፋ ለእስር መዳረጋቸው አይዘነጋም።
Filed in: Amharic