>

በቀለ ገርባ አብዷልና ዘመዶች ካሉት ወደ ጠበል ወይንም ..... (አምባቸው ደጀኔ)

በቀለ ገርባ አብዷልና ዘመዶች ካሉት ወደ ጠበል ወይንም ወደ አማኑኤል ሆስፒታል ያስገቡት!

አምባቸው ደጀኔ

“ዱባ ካላበደ ቅል አይጥልም” – በቀለ ገርባ ሰሞኑን ተናገረው የተባለውን በጤናው ፈጽሞ ሊናገር አይችልም፡፡ ስለዚህ ታሞ ወይም አእምሮው በሆነ ነገር ታውኮ መሆን አለበትና ከዚህም በከፋ ጨርቁን ሳይጥልና የለዬለት ዕብደት ሳይገጥመው ሁነኛ ሰው ካለው ወደ ዘመናዊ ሆስፒታል ወይም ወደ ባህላዊ ህክምና አለዚያም ክፍሉ ተቆጥሮ ወደ ጠበል ይወሰድ – እስካሁኒቷ ደቂቃ ለይቶለት አብዶ ካልሆነ፡፡ የርሱ መሰል ዕብደት እንደውሻ ዕብደት በከፍተኛ ደረጃ ተላላፊ በመሆኑ ብዙዎችን ሳይበክል ይታከም፡፡ እንዲህ ዓይነቱን በሽተኛ ማሳከም ጥቅሙ አንድም ለነፍስ አንድም ለሀገር ነው፡፡

ሀገራችን በየቀኑ መነጋገሪያ አጀንዳ አታጣም – በተለይ በዚህ ዘመንና በጣም በተለይ ደግሞ ባለፉት 12 ወራት፡፡ በነዚህ ሁለት ቀናት ደግሞ “አትርሱኝ” እያለ ያለው በቀለ ገርባ ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች በሰዎች ዘንድ መነሳታቸውን እንጂ የሚነሱበት ጉዳይ መጥፎ ሆነ ደግ አያሳስባቸውም፡፡ የተፈጥሮ ስንኩልነት መገለጫው ብዙ ነው፡፡

እንደውነቱ ላለመረሳትና በሕዝብ አንደበት ዘወትር ለመወሳት በግድ ክፉና ጠማማ መሆን አያስፈልግም፡፡ በቀለንና ጃዋርን መሰል ሰዎች እንዴት ነው እያሰቡ ያሉት? እንዴትስ ነው ያድጋሉ ሲባሉ እያነሱና እየኮሰመኑ የሚሄዱት? ምን ቢነካቸው ነው? አንድ ሰው ዕውቀትንና ጥበብን መጨመር ቢያቅተው ያለውን ይዞ መጓዝ እንዴት ይሳነዋል?

በቀለ ገርባ (አሁን ‹በቀለ ገሪባ› ብለውም ሲያንሰው ነው – ‹ገሪባ› ማለት ታዲያን ዕውቀት የሚጎድለው ባላገር ሰገጤ ማለት እንደሆነ ልብ ይባልልኝ) በትልቅ የትምህርት ተቋም በመምህርነት ብዙ ጊዜ አገልግሏል፡፡ ያስተማራቸው ወጣቶችም ኢትዮጵያውያን እንጂ ከአንድ ጎሣ ተመርጠው የገቡ አይመስለኝም፡፡ ኢትዮጵያ ያለቻቸው ጎሣዎች ደግሞ ከ85 በላይ እንጂ ኦሮሞ ወይም አማራና ትግሬ ብቻ አይደሉም፡፡ በዚያ ዓይነት የትምህርት መድረክ የነበረ ሰው ዘረኝነትን ሊጠየፍና ኮዝሞፖሊታን አስተሳሰብ ሊላበስ ሲገባው እንደ አንድ ተራ ያልተማረ ዜጋ የዘረኝነት አዘቅት ውስጥ ተዘፍቆ ሲርመጠመጥ ማየት እጅግ ከማሳዘኑም በላይ ለሰውየው ለራሱ ማዘንም ተገቢ ነው፤ በቁም ለሞተ ሰው ማዘን ነግ በኔን ማሰብ ስለሆነ፡፡ ኢትዮጵያ እንደሆነች በቀለ ያን አለ ይህን አለ የምትሆነው የለም፡፡ እንኳንስ የበቀለ ከፋፋይ የዘረኝነት ንግግርና ስብከት መለስ ዜናዊና ዓለም አቀፉ የኢሉሚናቱቲ ፀረ-አቢሲኒያ ኃይላት ከ300 ዓመታት ለበለጠ ጊዜ ፈግተው ኢትዮጵያን አላፈረሷትም፤ በፈጣሪ ጥበቃ ሥር ስላለችም ትንገዳገዳለች እንጂ አትወድቅም፡፡ ይህ ብቸኛው ኢትዮጵያዊ ሃቅ ተፈጥሯዊና መለኮታዊ የማይሻር ህግ መሆኑን ለመረዳት የሀገራችንን ታሪክ ልብ ብሎ ማጤን ነው፡፡

በቀለን ግን ምን ነካው? አንድ ቋንቋ ከተናጋሪው ጋር የሚያያይዘው ምንም ባሕርያዊ የሆነ ነገር የሌለውና እንደ አንድ ተራ የምርት መገልገያ መሣሪያ ሊቆጠር የሚገባው በጣም አልባሌ መሆኑን እንዴት አጣው? ሁሉም ይረዳው – ሰዎች በአላስፈላጊ ሁኔታ ከሥነ ልቦናቸው ጋር እያቆራኙት በ“የኔ ነው፤ ያንተ ነው” ይቆራቆሳሉ እንጂ በመሠረቱ ማንኛውም ቋንቋ የማንኛውም ሰብኣዊ ፍጡር የጋራ ሀብት ነው፡፡ ቋንቋዎች የተለያዩት በሕዝብ ብዛትና በዓለማችን የቆዳ ስፋት እንጂ የቋንቋ ብዛትና ልዩነት ከቁም ነገር ተቆጥሮ እንዲህና እስከዚህ የሚንጠባረሩበት፣ በአካኪ ዘራፍ የሚያወራጭ ጉዳይም ሆኖ አይደለም – እንደማንኛውም ቁሣዊ ንብረትህ – ለምሣሌ እንደምትወዳት የገንዘብ ቦርሣህ – ስትሞት ነገ ጧት ትተው ለምትሄደው ተራ ነገር እንዲህ መሆን በታማሚነት የሚያስፈርጅ ነው – በጣም ያሣፍራል፡፡ እኔ በነዚህ ዓይነት ሰዎች እጅግ አፍራለሁ፡፡ የመጀመሪያ ቋንቋየ አማርኛ ነው – አነ ንአብነት፡፡ አማርኛ ገደል ቢገባና ትግርኛን ብደምቢ ለሚደ ካልኦትውን ብደምቢ ለሚደን ኩልና በዚህ ቋንቋ ብንጠቀም ጉዳየ አይደለም – ቃህ ይብለኒ እንዲያውም – ግን በሰው ሠራሽ መንገድና በገልቱዎቹ የእነበቀለ ቡድን ስሜታዊ አምባላይ ፈረስ የዕውር ድምብር ግልቢያ ሳይሆን በተፈጥሯዊ መንገድ ከሆነ ነው፡፡ በአማርኛ አልቆረብኩም፤ በሥነ ልቦናዊ ደዌም አልሰቃይም፡፡ ሰዎች ይገርሙኛል፡፡ በኔ እምነት ሰው ያለመሆን ትልቁ ምልክት በቋንቋ ሰበብ መጣላትና በሥነ ልሣናዊ የሥነ ልቦና በሽታ መሰቃየት ነው፡፡ ወንድሞቼ እባካችሁን በቋንቋ አንጣላ፡፡ የቋንቋ የልደትና የሞት ህግጋትንም እንወቅ፡፡ ከጥላቻና ከምቀኝነት፣ ከክፋትና ከተንኮል ራሳችንን ወጣ አድርገን ብናስበው ሁሉ ነገር ከንቱ ነው – በጠቢቡ አነጋገር ንፋስን እንደመከተል ያለ ከንቱነት፡፡

ይልቁንስ ስለዶክተር አንጋሣና መሰል የኦሮሞ አክቲቪስቶች የተሰማኝን ልዩ ኩራትና የአለኝታነት ስሜት በዚህች አጋጣሚ ልግለጽላችሁ፡፡ ያየሁት ትናንት ነው፡፡ አንድ ወጣትና ዶ/ር አንጋሣ በዩቲዩብ እየተናገሩ የሰማሁት ነገር በደስታ አሰከረኝ፡፡ የሚናገሩት ስለኦነግ ነው፡፡ በመቀመጫው ነው ቁጭ ያደረጉት፡፡ ፈልጉና አዳምጡት፡፡ የእናት ሆድ ዥንጉርር መባሉ ለዚህ ነው፡፡ እነበቀለ ቀርባና ጃዋር መሀመድ በተፈጠሩበት የኦሮሞ ኢትዮጵያውያን ግዛት ቶሎሣ ኢብሣንና ዶ/ር አንጋሣን፣ ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሣንና ሌሎችንም ብርቅዬና ውድ የኦሮሞ ልጆች ስናይ ውኃ እንዳገኘ የበረሃ ተክል ተስፋችን ይለመልማል፤ ህልማችንም እንደጽጌረዳ ያብባል፡፡ ተባረኩልኝ፡፡ ልጅም ይውጣላችሁ፡፡ በተቃራኒው ኢትዮጵያን ለማፍረስ የምትቃትቱ ወንድሞቼና እህቶቼ ጥቁር ውሻ ውለዱ፡፡

የነበቀለ ገርባ ጉዳይ ግን በተከድኖ ይብሰል ብቻ የሚተው አይደለም፡፡ ዘመድ ለመቼ ነው? አክስት አጎት ለመቼ ነው? ወዳጅ ጎረቤትስ ለመቼ ነው? ሳይብስባቸው በሰንሰለት አስሮ ወደሚቀርባቸው ጠበል መውሰድና የተሣፈረባቸው ወያኔያዊ የአጋንንት መንጋ እስኪለቃቸው ድረስ ማስጠመቅ ነው፡፡ የወሊሶው አባ ወልደትንሣኤ በሕይወት ቢኖሩ ኖሮ ይሄኔ ስንቱን የዲያብሎስ ጭፍራ ከሀገራችን ያስወጡልን ነበር፡፡ ወይ ነዶ!

በዚህች አድራሻ ግቡና የበቀለን ጉድ ተመልከቱልኝማ – https://welkait.com/?p=19441አንድ ሰው ካላበደ ወይ ካልሰከረ እንዲህ ያለ ማፈሪያ ነገር አይናገርም፡፡ ግን ምን ነካው?

በነገራችን ላይ “ወርቅ ላበደረ ጠጠር” እንዲሉ ሆኖ እንጂ አማርኛ ተናጋሪዎች የሚናገሩት ቋንቋ ለ87 ጎሣና ነገድ እንደ ድልድይ ሆኖ በማገልገሉ ሊሸለሙና ሊወደሱ ይገባ ነበር እንጂ ከምድር እንዲጠፉ ጩቤና ጎራዴ ሊሳልባቸው ባልተገባ ነበር፡፡ የሀገራችን ነገር ግና እንዲህ የተገላቢጦሽ ሆነና አረፈው፡፡ በሌላው ዓለም ቢሆን ኖሮ ስንትና ስንት ውዳሤና ሙገሣ ነበረው፡፡ “በባለጌ ቤት እንትንና ሥጋ ርካሽ ነው”ና በቋንቋው ምክንያት መመስገን የነበረበት ነገድ እንደማርያም ጠላት በእጁ በጎረሱ ሰዎች እንዲህ እንዲሳደድ ታሪክ ወልጋዳ ብይን ሰጠ፡፡ ይሁን፤ ይህም ያልፋል፡፡

`The English language is nobody’s special property. It is the property of the imagination: it is the property of the language itself.’ Derek Walcott

Filed in: Amharic