>
5:13 pm - Sunday April 19, 2961

"የአምቦ ህዝብ ዘረኝነትን አይሰብክም! ጥብቅናው ለኢትዮጵያ አንድነት ነው! ዘረኝነትን አይደግፍም!!!" (የአምቦ ወጣቶችና ምሁራኖች ንቅናቄ ሀሮምሳ ቱለማ)

“የአምቦ ህዝብ ዘረኝነትን አይሰብክም! ጥብቅናው ለኢትዮጵያ አንድነት ነው! ዘረኝነትን አይደግፍም!!!”
የአምቦ ወጣቶችና ምሁራኖች ንቅናቄ ሀሮምሳ ቱለማ
ጀግናው የአምቦ ወጣቶችና የምሁራኖች የውስጥ ስብሰባ በማድረግ  ከጥንት እስከዘሬ የለውን የአከባቢው ህዝባዊ እንቅስቃሴ ትግልና አላማን በመገናዘብ በሁኑ ግዜ የደረስንበትንም በማጤን በአንድ አንድ ጉዳዮች ላይ ትኩረትን ሰጥተዋል።
1-የአምቦ ወጣቶች ከጥንት እስከዘሬ እንዲሁም ታሪኩና አቋሙ በተመለከተ
2- የአምቦ ጀግኖች ትግል በመጤ አክትቭስቶች ለፖሊትካ  ፍጆታቸው መረገጡን የሚያመለክቱ ህዳቶች መከሰታቸውን
3- የአምቦ ህዝብ ዘረኝነትን አይሰብክም ጥብቅናው ለኢትዮጵያ አንድነት ነው ዘረኝነትን አይደግፍም።
በዝሁ የተነሳ የአኖሌ ፖሊትካ ጠንሰሾችም ሆኖ አራመዶች ከልተወገዶ ጀግናው የአምቦ ወጣት  የዘር ጥላቻን በመቃወም አቋም ይወሰዳል።
አኖሌ ከአምቦ ህዝብ ገር መጓዝ አይችልም።
4- የወለጋ ምሁራን እንድሁም አክትቭስቶች አምቦን እንደ አምቦ እንጅ እንደወለጋ ስላልሆነ ቀደምት ጀግኖቻችን የማረከስ ዘመቻን በአስቸኳይ እንድታቆሙ እንጠይቃለን
5 – ኦዴፓ -ኦሮሚያ ሰፍ ስለሆነ ሁሉም እንደአከባቢያቸው እንጅ እንደ አንደኛው የፖሊትካ ፍላጎት መስፋፍያ መሆን የለበትም።
6 -የአምቦ ህዝብ ከታርኩም ሆነ ከባህሉ ገር የምተዳደረው ከሾዋ ህዝብ እንጅ በቅርብ ግዜ በተፈጠረው ኦሮሙማ ፖሊትካ እንደልሆነ ምሁራኖች በይፋ ይግለፁልን።
ምክንየቱም ማንነት በጠረጴዛ ላይ ተሰብስበው በማቀናበር  ሰይሆን ታርክ የፈጠረው በህላዊ እድገት ገር የተያየዘ ህዝባዊ መብት ነው።
7-  ደግማዊ ሚንልክ ሎሬት ፀጋዬ ጃገማ ኬሎ  በቀላ መገርሳ አኩሪያችን እንጅ አስፋሪያችን አይዴሉም። ከዘረኝነት ይልቅ አገራዊ ማንነታችን
8. የአከባቢው ሃብት የጋረ ለጋረ እንድሆን ሙሉ ፍላጎታችን መሆኑን እንገልፃለን።
የአምቦ ጀግና የበላይነት ወይም የበታችነት ሳይሆን የዜጎች እኩልነት መርሆው መሆኑን ለመላው ዜጎቻችን መግላፅ እንወዳለን
ለአምቦና ለአከባቢው ለጋራ አቋምና ትብብር ድጋፍ ያስፈልጋል 
ኢትዮጵያ የሁላችንም ናት
Filed in: Amharic