>
5:13 pm - Saturday April 19, 5484

ኦነግ ፣ የኦዴፓ ልዩ ሀይልና ቄሮ በጥምረት የአርጎባ ህዝብ ላይ ወረራ እያካሄዱበት ነው!!! (ሸንቁጥ አየለ ና ሱሌይማን አበበ)

ኦነግ ፣ የኦዴፓ ልዩ ሀይልና ቄሮ በጥምረት የአርጎባ ህዝብ ላይ ወረራ እያካሄዱበት ነው!!!
ሸንቁጥ አየለ ና ሱሌይማን አበበ
* እጅግ አሳዛኙ ነገር “የሀገር መከላከያ” ሰራዊትም  ቀጥታ ከኦሮሚያ ልዩ ሀይል ጎን ቆሞ በአርጎባዎች ላይ እየተኮሰ መሆኑ ነው!!!

በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አሞራቤቴ ቀበሌ ለማ መገረሳ የኦሮሞ ልዩ ሃይልና ኦነግን በማቀናጀት በቄሮ የሽብር  ቡድን ፊት አውራሪነት በአርጎባ ማህበርሰብ ላይ ወረራ በማካሄድ ላይ ነው! በአማራ ክልልና በኦሮሚያ ክልል  አዋሳኝ ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ጋርዳ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ከትናንት ጀምሮ በአርጎባ ብሔረሰብና በከረዩ ጎሳ መካከል በተፈጠረ ግጭት የኦሮሞ ልዩ ሀይል ቀጥተኛ ተሳታፊ ነው።

,, ዛሬ ከጧት ጀምሮ እስከ አሁኑ ሰአት ድረስ  በአርጎባና በከረዩ ኦሮሞች  የተጀመረው ጦርነት እስካሁን እንደቀጠለ ነው። ጦርነቱ አሁን ተባብሶ ቀጥሏል።የኦሮሚያ ልዩ ሀይል በከባድ መሳሪያ እየተኮሱ ነው። አሁን በደረሰኝ መረጃ  መሰረት ከአማራ ክልል መሬት ውስጥ አርጎባዎች ይኖሩበት የነበረው #ጋርዳ የተባለውን ,ቀበሌ የኦሮሚያ ልዩ ሀይል  ተቆጣጥሮታል። የኦሮሞው ብዛት ልክ የለውም። #ከብየሁሉ ድረስ ዘምተው መጥተዋል። ለጊዜው ቁጥራቸው ያልታወቀ የሞቱና የቆሰሉ ሰዎች አሉ ።
ጦርነቱ በመከላከያ ስራዊት የታገዘ ነው።መከላከያ
ቀጥታ ከኦሮሚያ ልዩ ሀይል ጎን ቆሞ በአርጎባወች ላይ እየተኮሱ ነው።
የግጭቱ ዋናዉ መነሻም አርጎባዎችን ከእርሻ ይዞታቸዉ ላይ የኦነግ ሀይል ገፍቶ ለማስወጣት በተደራጀ መልክ ያደረገዉ የትጥቅ ወረራ መሆኑን እየተነገረ ነዉ::
ከማል ገልቹም ይሄን አጋጣሚ በመጠቀም ከሃያ በላይ መኪና ሙሉ ታጣቂዎችን በአካባቢዉ እያመላለሰ ጦርነቱን እያፋፋመዉ መሆኑ እየተገለጸ ነዉ::ይሄዉ አርጎባዎችን በማጥቃት የተጀመረዉ የኦነግ/ኦዴፓ የዘር ማጥፋት እንቅስቃሴ አድማሱን በማስፋት የአማራ አርሶ አደሮችንም የጥቃቱ ኢላማ ማድረጉ እየተገለጸ ነዉ::
የኦነግ/ኦዴፓ ሀይል በተደራጀ መልክ ጦርነት ቢከፍትም የብ አዴን/አዴፓ ሀይል ግን አርሶ አደሮቹን ለመከላከል አንዳችም እንቅስቃሴ እያደረገ አይደለም ተብሏል::ቢሆንም ግን አርሶ አደሮች በራሳቸዉ ጉልበት ብቻ የኦነግ/ኦዴፓን ሀይል እየተፋለሙ መሆኑን ተገልጿል::
ከዚህ በፊት በአካባቢዉ አንዳንድ ግጭቶች በአርሶ አደሮች መሃከል ቢፈጠርም እንደዚህ በተደራጀ መንገድ ግን ሌላዉን ብሄረሰብ የማጥቃት እንቅስቃሴ ተደርጎ አያዉቅም ይላሉ የአካባቢዉ ነዋሪዎች::
የሆነ ሆኖ ግን የተገፋዉም ወገን ከተደራጀዉ የኦነግ ሀይል ጋር ገጥሞ ቀጥተኛ የአጸፋ ምት እየሰጠ እየገኛል::
በዬ አካባቢዉ ሌሎች ነገዶችን የሚያፈናቅለዉ ኦነግ ከአዲስ አበባ እስከ ደቡብም: ከሶማሌ እስከ ሀረር: ከአማራ ክልል እስከ አፋር የራሱን ቁመት እየለካ ነዉ የሚሉ ተንታኞች ይሄ የኦነግ/ኦዴፓ አካሄድ እራሱን ያጠፋዋል እንጅ አይበጀዉም እያሉ ነዉ::ኦነግ/ኦዴፓ ግን እብጠት ላይ ነዉና እስኪፈነዳ አሁን ትንታኔ የሚባል ነገር የሚያደምጥ አልሆነም::
የሆነ ሆኖ ብዙዎች ኦዴፓ/ኦነግን ሰከን እንዲል ይመክራሉ:: አለዚያ አብሮ የኖሩ ማህበረሰቦችን ማጋጨት እና ትንንሿን ቀበሌ ሁሉ የኔ ናት ማለት ትልቁን ኦሮሚያን እራሱን ከእጁ እንደሚያወጣዉ አልተረዳዉም የሚል ትንታኔ እየሰጡ ይገኛሉ::
ፍትህ ለአርጎባ ህዝብ 
አዴፓ ሆይ ክልሉን ማነው የሚጠብቀው ?
Filed in: Amharic