>
5:13 pm - Thursday April 19, 4103

"ከበፊቱ የከፋ አፈና አለ - በዚህ መንገድ ዴሞክራሲን መገንባት አዳጋች ነው!!!" (አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ)

“ከበፊቱ የከፋ አፈና አለ – በዚህ መንገድ ዴሞክራሲን መገንባት አዳጋች ነው!!!”
አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ – ለጀርመን ድምጽ ከተናገሩት
በኤልያስ ገብሩ
——-
“የፓለቲካ ምህዳሩ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ተዘግቷል። የኢህአዴግ የክልል አስተዳደር፣ መማቅርና አባለት ከቀደመው ስርዓት (ህወሃት/ኢህአዴግ) በከፋ መንገድ ምህዳሩን ዘግተውታል።
ጥሩ ጅምሮ ያሳዩት እነለማ መገርሳና አብይ አህመድ (ዶ/)፣ የሚሰሩት ትናንት በነበረው የኢህአዴግ መዋቅር ውስጥ በመሆኑ፣ የፖለቲካ ምህዳሩን ዘግተውታል። ችግሩ በከፋ መንገድ እየሄደ ነው። የስርዓቱ የዘር ፖለቲካ አራማጆች የዜግነት ፓለቲካ አራማጆችን በሀገሪቷ ውስጥ በአግባቡ እንዳይንቀስቀሱ አግደዋል።
 27 ዓመታት ቋንቋና ዘር ያማከለ ስርዓት ዋጋ እያስከፈለን ነው። በዘር ላይ የተመሰረተ ፖለቲካ ለዴሞክራሲ ደንቃራ ነው። ማንም አሸናፊ የማይሆንበት ሁኔታ ውስጥ እየገባን ነው። አካሄዱ ከፍተኛ ጥፋት ያስከትላል። ከችግር ወደችግር እየተላለፍን ነው። በዘር መደራጀት መከልከል አለበት!
 ‘በፌዴራሊዝሙ ላይ አንደራደርም!’ የሚባለውን ነገር አንቀበልም። የፌዴራሊዝሙ አደረጃጀት ለዴሞክራሲ እድገት ማነቆ ነው። አሁን የፌዴራል መንግስቱ ካለው በላይ የክልሎች ሃይል እየበለጠ ነው። በትግራይ 1.2 ሚሊየን ሚሊሻ ታጥቆ በፌዴራሊሙ ላይ አንደራደርም ማለት ምን ማለት ነው?! ከበፊቱ የከፋ አፈና አለ። በዚህ መንገድ ዴሞክራሲን መገንባት አዳጋች ነው።
 …ህዝብና የፖለቲካ ሃይሎች መወያየት አለባቸው።”
[የግንቦት 7 ዋና ጸሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ ከጀርመን ድምጽ ራዲዮ ጋር ካደረሩት አጠር ያለ ቃለ-ምልልስ የተወሰደ ሲሆን በዛሬ በDW ዕለታዊ ስርጭት ላይ የተላለፈ ነው። የአቶ አንዳርጋቸውን ሙሉ ሃሳብ ከDW ገጽ ላይ ያገኙታል።]
Filed in: Amharic