>
5:13 pm - Wednesday April 19, 6428

የኦሮሞ ብሔርተኞች   ትክክለኛው «የሕብረ ብሔራዊ ፌዴራሊዝም»  ምልክት!   (አቻምየለህ ታምሩ)

የኦሮሞ ብሔርተኞች   ትክክለኛው «የሕብረ ብሔራዊ ፌዴራሊዝም»  ምልክት! 
 አቻምየለህ ታምሩ
ከታች የተያያዘው ፎቶ ሓጂ ጃዋር መሐመድ «የሕብረ ብሔራዊ ፌዴራሊዝም» መገለጫ አድርጎ ያቀረበው ፎቶ ነው። ሓጂ ጃዋር «የሕብረ ብሔራዊ ፌዴራሊዝም» ምልክት አድርጎ የለጠፋቸው ሶስቱም ወጣቶች ኦሮሞዎች ናቸው። ፎቶው ኦነግና አባገዳዎች ዐቢይን በመሐል  አድርገው መያዝ እንዳለባቸው የሚያሳይ ይመስላል። በግራ በኩል ያለችዋ የአባ ገዳን አርማ ነው የለበሰችው። በመሐል ያለው ወጣት የለበሰው ዐቢይ  ቃለ መሐላ ከፈጸመ በኋላ  ቤተ መንግሥት ይዞት የገባው የጠቅላይ ሚንስትሩ  ባንዲራነው። በስተ ቀኝ በኩል ያለው ደግሞ የኦነግ ምልክት ነው።
ሓጂ ጃዋር «የሕብረ ብሔራዊ ፌዴራሊዝም» ምልክት አድርጎ ሊያሳየን  የፈለገው እንግዲህ አባገዳና ኦነግ ዐቢይን በመሐል አድርገው ከኦሮሞ ውጭ ሌላ ሰው የሌለበትን አሕዳዊ ሥርዓት ነው። ይህ በትናንትናው እለት እንደ ኦሮሞ ብሔርተኞች ፍጹም አሐዳዊ ስርዓት አራማጅና ጨፍላቂ እንደሌለ የሚያጠናክር ይመስለኛል።
የኦነግ  ልጅ ነኝ የሚለን  ሓጂ ጃዋር ሕብረ ብሔራዊ ፌዴራሊዝም ማለት ኦነግነት፣ አባገዳነትና ኦሕዴድነት የመሆን አንድ አይነትነት ወይንም አሕዳዊነት እንደሆነ ለምልክት የለጠፈው ፎቶ  የፌዴራል መንግሥት ተብዮውን ሥልጣን  የኦሮሞ ብሔርተኞች  የተከፋፈሉበትን ሞዴል የሚያሳይ ይመስለኛል።
የፌዴራሊዝም የመሰረት ድንጋይ አስርና ሀያ ምልክት ማውለብለብ አይደለም። የፌዴራሊዝም የመሰረት ድንጋይ  ስልጣንን በማዕከላዊ መንግሥትና  በክፍለ ሀረሮች መካከል ማከፋፈል ነው።
የኦሮሞ ብሔርተኞች ግን  የማዕከላዊውን መንግሥት ቁልፍ ቁልፍ ስልጣኖች  ጥርግ አድርገው  ጠቅልለውና  በአንድ ነገድ ሰዎች ሞልተው  የማዕከላዊ መንግሥትን ስልጣን መጋራትን የመሰረት ድንጋዩ ስላደረገው ፌዴራሊዝም  እንደነፍስ አባቶቻቸው ምልክት በመለጠፍ የአንድ «ብሔር» ሰዎች የሆኑትን  የኦነግ፣ የዐቢይና የአባገዳዎችን  ምልክቶች እየለጠፉ ብቻቸውን ጠቅልለ የወሰዱትን የመንግሥትነት ሥልጣን የፌዴራል ስርዓት እንደሆነ በፎቶ ሊሸነግሉን ይቃጣቸዋል። ድንቄም ፌዴራሊዝም!
Filed in: Amharic