>

የፌደራሊዝሙ አንድምታ! (ሚኪ አማራ) 

የፌደራሊዝሙ አንድምታ!
ሚኪ አማራ
ኦዴፓ በፌደራሊዝሙ አልደራደርም ብሎ የተናገረዉ ነገር ብዙዉ ሰዉ overreact ያደረገ መስሎኛል፡፡ ወይም ከላይ ከላይ እንጅ ብሄረተኝነቷ ወደ ዉስጥ አልዘለቀችም ማለት ነዉ፡፡
እኔ ኦዴፓ ያለዉ ነገር  ለእኛ ፈረንጆቹ a blessing in disguise የሚሉት ነገር ነዉ፡፡ ፌደራሊዝም በመሰረቱ ከብዙ የመንግስት አወቃቀሮች አንዱ ነዉ፡፡ ጥቅም አለዉ ጉዳት አለዉ፡፡ ፊደራሊዝም ትተን ሌላ መስመር እንከተል ቢባል ሁሉም የሚጠቀም እንጅ አንድ ቡድን ተለይቶ የሚጠቀምበት ነገር አይታየኝም፡፡ አሁን ያለዉን የፌደራሊዝም አዎቃቀር ለጊዜዉ የተወሰኑ ቡድኖችን የጠቀመ ይመስላል፡፡ የተጠቀሙ የመሰላችዉ ደግሞ እኛ የሚገባንን ባለመጠየቃችን ወይም እኛ እንደ ኢትዮጵያዊ ችግር የለም ብለን የእኛን ድርሻ ሁሉ አሳልፈን በመስጠታችን እሱን የሚያግበሰብሱ ቡድኖች የተጠቀሙ መስሏቸዋል፡፡ እኛ የሚገባንን እየጠየቅን ነዉ፡፡ በመሆኑም አዉቀንም ሆነ ሳናዉቅ በእንዝላልነት የተዉናቸዉን ነገሮች በሙሉ መየጠቅ እና መጠቀም ስንጀምር ፌደራሊዝም ለእነዚህ ቡድኖች painful መሆኑ አይቀርም፡፡ የእኛ ስራ መሆን ያለበት ይሄዉ ነዉ፡፡
በፌደራሊዝም ስረአት ዋና ዋና የሚባሉት:-
 1) የህዝብ ብዛት
2) የሃብት መጠን
3) እራስን በራስ ማስተዳደር
 4) ተገቢዉን ፓወር ማግኘት ናቸዉ፡፡ በመሆኑም እኛ ማጆሪቲ ህዝብ ነን፤ ሃገሪቱ የምታስገባዉ ገቢ ባብዛኛዉ በአማራ ህዝብ ጫንቃ እና ሃብት ላይ የተመሰረተ ነዉ፤ የአማራ ህዝብ ማንም ቢያስተዳድረዉ ደንታ አልነበረዉም፡፡ በመሆኑም ባግባቡ የሚገባንን ከጠየቅን በፌደራሊዝም ስትራክቸር ዉስጥ ከሌላዉ በባሰ ሁኔታ ተጎጅ ሳይሆን የምንጠቀምበት መንገድ ሁሉ ይታየኛል፡፡ እኛ አሁን የሚያስፈልገን በአማራነታችን በኩራት በመደራጀት የሚገባንን መዉሰድ፤ ትክክለል ያልሆነዉ የፌደራሊዝም አካል ማስተካከል/እንደገና መስራት፤ የመደራደር አቅምን መጨመር እና ብሎም ባጠቃላይ በኢትዮጵ ፖለቲካ ላይ እንደማጆሪቲ ህዝብ ተገቢዉን ተጽእኖ መፍጠር፡፡ይሄን ማድረግ ስንጀምር በየትኛዉም የሀገሪቱ ከፍል ያለ አማራ ተጠቃሚ ይሆናል፡፡ ዋናዉ አቅም ማዳበር ነዉ፡፡ የተወላገደዉን የፌደራሊዝም አካል ማስተካከል አንዱ አላማችን ነዉ፡፡ ከዚህም በፊት እንዳልኩት ይሄን ማድረግ ከቻልን አይደለም በብሄር የተዋቀረ ፌደራሊዝም በባል እና ሚስት ቢዋቀርም ለእኛ ችግር አይሆንም፡፡ ዋናዉ ጥቅማችን አሳልፈን አለመስጠት ነዉ እናም መዋቅሩን ለሚደሳሰቱበት አካላት ቢቀርብንስ እስኪሉ ድረስ አስቀያሚ ማድረግ እንችላለን፡፡ የአኛ ትልቁ ችግር አለመስገብገባችን ነዉ፡፡
በመሰረቱ የአንድነት ቡድን ነኝ የሚለዉ ወይም ስለዜግነት ፖለቲካ የሚያወራዉ (እነተከርቸም) ነበር መንጫጫት ያለበት ነገር ግን አይጥ እንደዋጠ ድመት ጸጥ ብሏል፡፡ በእርግጥ በቀደም እንደጻፍኩት ነዉ፡፡ ይህ ቡድን በመሰረታዊነት ደረጃ አሁን ያለዉን አወቃቀር የሚጠላ አይደለም፡፡ ይሄን እኛ እንዲሁም አብን በሚገባ በመጠቀም ከጨዋታ ዉጭ የማድረግ ስራ መስራት ያስፈልጋል፡፡ የአማራ ህዝብም እንደ ገበታ ዉሃ ወዲያ እና ወዲህ የሚዋልለዉን ነገር ማቆም አለበት፡፡ የአማራ ኢሊት ነኝ የሚለዉም እንግዲህ እኛም እየነገርንህ ነዉ መንግስትም እየነገረህ ነዉ፡፡ አማራነትህን ተቀላቅለህ የሚገባንን ጥቅም እንድናገኝ እርዳን፡፡ አለያ ዘወር በሉልን እንቅፋት አትሁኑን፡፡
ከመጀመሪያዉም ጀምሮ ያነሳናቸዉ አጀንዳወች እና ጥያቄወች በአማራ ብሄርተኝት ማእቀፍ ዉስጥ የሚመለሱ ናቸዉ፡፡ ብሄርተኝነታችን አጥብቀን ስንይዝ ብቻ ነዉ መገዳደር የምንችለዉ፡፡ መገዳደር እና ማስጨነቅ የጀምርነዉ ብሄርተኝነታችን ስንጀምር፤ እንደ አብን አይነት የፖለቲካ ፓርቲ ሲመጣ ነዉ፡፡ የኢትዮጵን ፖለቲካ ለልመና እና ለልምምጥ በፍጹም አይመችም፡፡ አዉሬ መሆንን ይጠይቃል፡፡
Filed in: Amharic