>

ልሂቃኑ ስለ ትግራይ ወሰን ይህን ይላሉ  (ዮሀንስ አማረ)

ልሂቃኑ ስለ ትግራይ ወሰን ይህን ይላሉ 
ዮሀንስ አማረ
“የትግራይ ወሰን የተከዜ ወንዝ ነው”
      ልዑል ራስ መንገሻ ስዩም
“ወልቃይት ወደ ትግራይ እንዲገባ የተደረገው ወደ ሱዳን መውጫ ለማግኘት ነው”
         ዶክተር አረጋዊ በርሄ
“የጎንደር እና ትግራይ ግዛቶች የሚያዋስነው ተከዜ ወንዝ ነው”
         አቶ አሰገደ ገብረስላሴ
” የወልቃይት ህዝብ የዘር ማጥፋት እና ግዛት ማካለል የተጀመረው በ1970ዎች ነው። ህዋሃቶች ወልቃይቶችን ወደ ትግራይ ልትጠቃለሉ ነው ሲሏቸው ህዝቡ እምቢ በማለቱ ከዚያን ጀምሮ የሃይል ርምጃ እየተወሰደ ወልቃይትም በግድ የትግራይ ሆነ”
        አቶ ገብረመድሃን አርአያ
ወልቃይት ወደ ትግራይ ሲካለል ከሱዳን ጋር ለመገናኘት ስለነበር የህዝብን ፍላጎት አልጠበቀም። በመሆኑም የህዝብ ምርጫ ሊከበር ይገባል”
         አቶ ግደይ ዘርአጽዮን
~~~
እኒህ ሁሉም ትላልቅ ሰዎች ትግሬዎች ናቸው። ከልዑሉ በቀር ሁሉም የህዋሃት መስራቾች እና አመራሮች ነበሩ። ሁሉም ግን በአንድ ነገር ይስማማሉ። የትግራይ ድንበር ተከዜ ወንዝ መሆኑን።
 እኒህን ቋሚ መረጃዎች የምናቀርበው የታወሩት የወያኔ ካድሬዎች እና ወራሪ ህዝቦቻቸው ከራሳቸው ወገን ከሆኑ ሰዎች አንደበት እንዲሰሙ እና ቆም ብለው እንዲያስቡ ለማለት እንጂ የወልቃይት ጉዳይ ለምስክር እና ድርድር የሚቀርብ ሆኖ አይደለም። ወልቃይት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የአማራ ግዛት ነበር፤ አሁንም ነው ፤ ነገም ይሆናል አራት ነጥብ። ትላንት ዛሬ አይደለምና ቀኑ ይርዘምም ይጠርም ወልቃይት በሰላማዊ መንገድም ሆነ በሃይል ወደ እናት ምድሯ ትመለሳለች። ይህንን ለማየት ደግሞ ነብይ መሆን አያስፈልግም!
Filed in: Amharic