>

" ህግ መከበር አለበት ሲባል ለአባገዳም ይሰራል!!!" (ቦጋለ ሰለሞን  ዘውጋ) 

” ህግ መከበር አለበት ሲባል ለአባገዳም ይሰራል!!!” 
   ቦጋለ ሰለሞን  ዘውጋ 
   ሰሞኑን  በመንግስት እና በኦነግ መካከል በተደረገው የሰላም ስምምነት ዙሪያ አንዳንድ ነጥቦች ማንሳት አስፈላጊ ነው። በስምምነቱ መሰረት መንግስት የራሱን ሐሳብ ያቀረበ ሲሆን ፣ ኦነግም የሚደራደርበትን ጉዳይ አቅርቦአል። ከዚህ በተጨማሪ በአደራዳሪነት የተገኙት የአባገዳ ሽማግሌዎች ከሽምግልናው ባለፈ ውሳኔ እንዳስተላለፉ እየተነገረ ነው!!
   ከአባገዳ ውሳኔዎች እንዱ ኦነግ በለውጥ ሂደቱ የፈጸማቸውን ( ፈፅሟል ተብሎ የተጠረጠረበትን)  ወንጀሎች አስመልክቶ አባገዳዎች ምህረት እንዳደረጉ የሚገልጽ ጉዳይ ነው!!!!
  የዚህ ፅሁፍ አላማ ምህረት እና ይቅርታ ማድረግ የሚችለው በኢትዮጵያ ህግ ማነው?  የትኛው ተቋም ነው?  የሚለውን ማየት ነው! !!  ምህረት የሚደረግበት ጉዳይስ ምንድነው? ? የባህላዊ ተቋሞቻችን ስልጣንስ እስከምን ድረስ ነው???
   ምህረት ማለት አንድ ሰው( ቡድን)  ተከሶ ወይም ሳይከሰስ ፈፅሞታል የሚባል ወንጀል ካለ ከፍርድ በፊት  የሚሰጥ ውሳኔ ሲሆን ፣ ይህንንም ውሳኔ የሚሰጡ የተለያዩ አካላት አሉ።
   ይቅርታ ማለት አንድ ሰው በወንጀል ተጠርጥሮ ከተቀጣ በኋላ ፣ ቅጣቱን ሳይፈፅም በይቅርታ የሚለቀቅበት ሁኔታ ነው።
 ሁለቱ ጉዳዮች በግለሰቡ የወደፊት የህይወት እጣ ፋንታ ላይ የተለያየ ውጤት አላቸው!! ዋናው ጉዳይ ይህ ስላልሆነ እንለፈው!!!
    ምህረት እና ይቅርታ የማይደረግባቸው ጉዳዮች ምንድናቸው???
   ምህረት እና ይቅርታ የማይደረግባቸው  ጉዳዮች በአለም አቀፍ ህግ አና በሃገራችን ህጎች ተደንግገው ይገኛሉ!!
  የሃገራችን ህገ መንግስት አንቀፅ 28 በአለም አቀፍ ህጎች፣ በሐገሪቱ ህጎች ፣ የተደነገጉ በሰው ልጆች ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች፣ የዘር ማጥፋት፣ ከህግ ውጪ የሚፈፀሙ ግድያዎች ፣ መሰወር፣ ኢሰባዊ ድብደባ ምህረት እና ይቅርታ እንደሌላቸው ይደነግጋል!! በተጨማሪም ማንኛውም የመንግስት አካል በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ምንም ስልጣን የለውም!!! ( አይደለም አባ ገዳ! !!!!)
 ይቅርታ መስጠት የሚችለው በህገ መንግስቱ አንቀፅ 71 መሰረት የሐገሪቱ ፕሬዚደንት ሲሆን ፣ በወንጀል ተከሰው ለተቀጡ ሰዎች ነው። ጉዳያቸው እየታየ ላሉ ግለሰቦች ከሳሹ አካል ክሱን ሊያቋርጥ ይችላል። ያ ማለት ግን ምህረት አግኝተዋል ማለት አይደለም!!!
  ስለዚህ በሃገራችን ምህረት የመስጠት ስልጣን የተሰጠው ለህግ አውጪው ነው የሚል እንድምታ ያለው የህግ ሁኔታ አለ!!!!
 
  ነጥብ አንድ!
  ምህረት የመስጠት ስልጣን የአባገዳዎች አይደለም!! በህግ መንግስቱ ባህልን የማሳደግ መብት ቢኖርን፣ በአንቀፅ 9 ላይ ፣ ህገ መንግስቱን እና አለማቀፍ የሰባዊ መብቶችን የሚቃረን ማንኛውም ውሳኔ ተፈፃሚነት እንደሌለው ተደንግጎ ይገኛል!! ስለዚህ ኦነግ በተጠረጠረበት ጉዳይ ( ከፈፀመ ይቅርታ የሚያሰጥ አይደለም) አባገዳዎች ምንም ስልጣን የላቸውም!!!!!!
  ነጥብ ሁለት!! 
  ጉዳዩ ምህረት ሊያሰጥ ወይም ይቅርታ ሊያሰጥ የሚችል ቢሆን እንኳን በህጉ መሰረት የህግ አውጪው እና የፕሬዚደንቱ ስልጣን ነው ሊሆን የሚችለው!!!
 
 ነጥብ ሶስት!!! 
   የተፈፀመው የወንጀል አይነት ሳይለይ ፣ ለምህረት፣ ለይቅርታ፣ እራስን ማሰጋጀት፣ መወሰን ፣ በራሱ በህገ መንግስቱ የተቀመጠውን የመንግስት እና የባህላዊ ተቋማትን ሚና በአግባቡ ያለመረዳት ነው!!!
  በመጨረሻም ህግ መከበር ያለበት በሁሉም አካላት ላይ ነው!!!!
Filed in: Amharic