>

ቶ ” ባለትንቢቱ ንጉስ ቶዎድሮስ ማነው ?? ”  (ሶሎሞን መቅደላ)  

ቶ ” ባለትንቢቱ ንጉስ ቶዎድሮስ ማነው ?? ” 
ሶሎሞን መቅደላ  
–  እነሆ  ቶ …!!!
       ከቀደሙት ኢትዮጵያውያን አባቶች የጥበብ አሻራ አንዱ የሆነውን ፍካሬ ከዋክብትን መሰረት ያደረጉ አንዳንድ ግለሰቦች የቶዎድሮስን መወለድ በቀጥታ በዓለማችን ላይ ጥሩም ይሁን መጥፎ ነገር ሰርተው ካለፉ ተጽእኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ከተወለዱበት ክስተት ጋር ያገናኙታል፡፡ የፍካሬ ከዋክብት ሊቃውንት በዓለማችን ታዋቂ የሆኑ ተጽእኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ከመወለዳቸው አስቀድሞ ሆነ ከተወለዱ በኃላ ግብራቸው የከዋክብትን እንቅስቃሴ  እና ባህሪ መሰረት ተደርጎ አስቀድሞ እንደሚነበብ ይናጋራሉ፡፡ ነገሩን ግልጽ ለማድረግ የሚከተሉትን ምሳሌዎች እንመልከት ጠቢቡ ሰለሞን ታላቁን ቤተመቅደስ ከመስራቱ አስቀድሞ በሚሰራበት ቦታ ላይ አሰድ እሳት የተሰኘችው ኮከብ እና ጸሀይ በ45 ዲግሪ ትይዩ ወጥተው ነበር፡፡ በዚህም የተነሳ እስራኤል የአንበሳ ከተማ ተብላ ትንቢት ተነግሮላታል አንበሳ አሰድ እሳት የተሰኘው ኮከብ መለያ ምልክት እንደሆነ ልብ ይበሉ፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደ ወቅት ይህ አሰድ እሳት የተሰኘው ኮከብ ከጸሀይ ጋር ትዩዩ ሆኖ በመውጣት የጌታችን ንጉስነትን አብስሯል፡፡ ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተሰቀለበት ወቅትም ጸሀይን ጨምሮ የተለያዩ ኮከቦች የመስቀል  ቅርጽ ሰርተው በእየሩሳሌም አናት ላይ ታይተዋል፡፡
ይህ የከዋክብት ምስጢራዊ ክስተት እንዲሁ በመስቀል ጦርነት እና በሌሎችም የዓለም ጦርነቶች እንደተስተዋለ የሚገልጹት የፍካሬ ከዋክብት ሊቃውንት የቶዎድሮስ መወለድን ደግሞ የዛሬ 46 ዓመት ገደማ በሰማዩ ንፍቅ ክበብ ሐመል እሳት የተሰኘው ኮከብ አሰድ የሚባለው ኮከብ እና እሬቶ የተሰኘው ኮከብ ሶስት ጎንዮሽ ሰርተው በደሴ ከተማ መታየታቸው ለውልደቱ ምልክት እንደሆነ ይገልጻሉ፡፡ የኢትዮጵያን ትንሳኤ  እና የተቀረውን ዓለም የወደፊት እጣ ፈንታ የሚያሳይ በሰማይ ላይ ላይ የሚታዩ የከዋክብት አንድምታ በምስጢር  እንደ  ይምርሃና ክርስቶስ ባሉ ገዳማት ጣራ ላይ በምስጢር ተጠልሰመው እንደሚገኙ ይነገራል፡፡
አጼ ዮሐንስ 4ኛው በዘመነ መንግስታቸው አንድ የሚያበራ ኮከብ በመታየቱ ደስ ብሎኛል ሲሉ የወሎ ክፍለ ሀገር ዋና ከተማን ደሴ ብለው መሰየማቸው የሚዘነጋ ታሪክ አይደለም፡፡ በርግጥ የላኮመንዛ ስያሜ ከዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስም ጋር ትስስር አለው ። አፄ ቴዎድሮስ ኢትዮጵያ አንድ ለማድረግ ዘመቻ በሚወጡበት ዘመን ደሴት የተሰኜች ቀይ ድንኳን ነበረቻቸው ይችን ድንኳን ተክለው  የድንኳናቸውን ስም ለቦታው ሰይመው እንደሔዱ እና ከዛን ጀምሮ ደሴ ተብላ እንደተጠራች ይነገራል ።
ከባለትንቢቱ ንጉስ ቴዎድሮስ ጋር በተያያዘ ከሚነሱ የትንቢት መጽሀፍት አንዱ ፍካሬ ኢየሱስ ሲሆን የታሪክ ሊቃውንቱ እንደሚገልጹት ስለምድራችን የወደፊት እጣ ፈንታ በስፋት የሚተነትኑት መጽሀፍት በሁለት ጥራዝ የነበሩ ሲሆን የመጀመርያው በጎንድር ቁስቋም ቤተክርስትያን የነበረ ሲሆን በኃላ በጀምስ ብሩስ ተሰርቁ በእንግሊዝዋ ንገስት እጅ ይገኛል ይህም ስለኢትዮጵያ የወደፊት እጣ ፈንታ ለመረዳት አስችሎዋቸዋል ታዲያ ይህ መጽሀፍ ንጉሱ ሃይለ ስላሴ በስደት በነበሩበት ወቅት መተርጎሙን እንዳይዘነጉ፡፡
 ይህን መጽሀፍ የመመልከት እድሉ የነበራቸው አባቶች እንደሚገልጹት ይህ ምስጢራዊ ሰው እናቱ ከሐረር አካባቢ እንደሆነች እና የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ እንደሆነች ገልጸው ጊዜው ደርሶ ንግስናውን እስኪረከብ በሀገሪቱ ከሚገኙት የተሰወሩ ገዳማት በአንዱ ከቅዱሳን አባቶች ጋር እንደሚገኝ ይጠቁማሉ፡፡ ጥንት ከክርስቶስ ልደት በፊት የነበሩ ኦራክል ተብለው ይጠሩ የነበሩ በግሪክ እና በግብጽ የሚታወቁ አስራሁለት ትንቢት ተናጋሪዎች መካከል አንዷ ጥቁር ንጉስ ከኢትዮጵያ እንደሚነሳ በዘመኑ መጀመርያም  በነውጥ ዓለምን የሚያምስ በኃላም  ሰላምን አስፍኖ ዓለምን እንደሚገዛ ትንቢት ተናግራለች፡፡  ከሂንዱ አማልክት አንዱ ክርሺኖ የግሪክ አማልክት ተደርገው የሚወሰዱት ዜዋስ እና አፖሎ የግብጻውያን አማልክት ተደርገው የሚወሰዱት ኦሲሪስ አይሲስ እና ሆረስ የቻይናው ፋሂ  የጃፓኑ ዛሃ ጥቁሮች ተደርገው በተሰረላቸው ጥንታዊ ሃውልቶች እና ምስሎች መገለጻቸው   በኦራክሎች የተነገረውም ትንቢት መሰረት አድርገው እንደሆነ ይገለጻል ይህም ቶዎድሮስን እኛ ኢትዮጵያውያን ብቻ የዓለሙ ህብረተሰብ እንደሚጠብቀው ማሳያ አድርገን ልንወስደው እንችላለን፡፡
አዳም በተፈጥሮው ያገኘውን የምድራዊ ሰማያት ገዥነት በድሎ ባጣ ጊዜ ቅዱሳን መላእክት የዚች ምድር ገዥ መሆን የሚያስችለውን ጥበባት እንዳስተማሩት  መጽሀፈ ሔኖክን ጨምሮ ሌሎችም ቅዱሳት መፃህፍት ይገልፃሉ ። እነዚህን ለዘመናት ከሰው ልጆች የተሰወሩትን  የሰማያተ ሰማያት የገዥነት ምስጢራትን ጠቅልሎ እንደሚይዝ የተነገረለት ቶዎድሮስ ከሰማያዊ ሃይላት ጋር በሚፈጥረው ህብረትም የተፍጥሮ ሃይሎችን በማዘዝ በሰማይ ላይ የሚዞሩ ሳተለይቶችን በኒኩለር ሃይል የሚሰሩ የሃይል ምንጮችን የተለያዩ የኮምፒዩተር ኔትወርኮችን መዝጋት የሚያስችል ሃይል እንደሚኖረው ይታመናል፡፡ በዚህም የተነሳ አሁን ባለው የፍሪማስነሪዎች የቴክኖሎጂ ምጥቀት በመደምሰስ የኢትዮጵያን ትንሳኤ በማረጋገጥ በምድር ላይ ገዢ ሃገር  እንደሚያደርጋት የቀደሙት ናይት ኦፍ ቴምፕላሮች እና አይሁዶች ያምናሉ፡፡
እነዚህ ሁለት አካላት ይህን ሰው በመጥለፍ የግላቸው ለማድረግ ያልቆፈሩት ጉድጓድ የለም፡፡ አይሁዶች በአለም ላይ ገዳይ ጀርሞችን በማሰራጨት በሀገሮች መካከል ጦርነት በመቀስቀስ ሀገራትን እርስ በርስ እንዲተራመሱ በማድረግ ዓለምን በአንድ ለመግዛት የሚያደርጉትን ሴራ በ1903 ሩስያ ውስጥ የታተመው የጽዮን ፕሮቶኮል ያጋልጣል  ታዲያ ከሰይጣን ጋር እጅና ጓንት ሆነው ሆነው ለዘመናት የሸረቡት ሴራ በቶዎድሮስ እንደሚከሽፍ የተረዱት አይሁዶችም ሆኑ ናይት ኦፍ ቴምፕላርስ ቶዎድሮስ በሀይሉ እንዲነሳ የሚያደርጉት ሰማያዊ ሃይል ያላቸው ምስጢራት  ከሰማይ ወርዶ ያረፉባቸውን ምስጢራዊ የክብር ቦታዎች መለየት ችለዋል፡፡
አይሁዶች በነዚህ ቦታዎች ላይ በተለያዩ የዓለም ክፍላት የሚገኙትን አይሁዶች በማሰባሰብ በነዚህ ቦታዎች ላይ የማስፈር ስራዎችን የሰሩ ሲሆን በዋንኛው የምስጢር ማእከል በሆነው የየረር ተራራ ላይ ለማስፈር ሙከራ አደርገው አልሳካ ቢላቸው በሰባቱ የክብር ቦታዎች ላይ የሚገኙትን መንፈሳዊ ምስጢራትን ለመቀራመት በሰለሞናዊ  ስርወ መንግስትን አማካይነት በሀገሪቱ ውስጥ እራሳቸውን እና ፍልስፍናቸውን በመሰግሰግ እስካሁን ድረስ አሻራው ያልጠፋ አስከፊ ሴራዎችን ሰርተዋል፡:   በ1928 ዓ/ም ኢትዮጵያ  በፍሪማስነሪዎች ድጋፍ  በፋሽሽት ጣልያን  በተወረረችበት ወቅት ዳግም አይሁዶችን ከተለያዩ የዓለማችን ክፍላት በየረር በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል እና አፋር አካባቢ ለማስፈር ከሞሶሊኒ እና ከፕሬዝዳንት ሩዝልቬልት ጋር ደብዳቤዎችን መለዋወጣቸው ይነገራል፡፡
የንጉስ የሃይሉ መገለጫ ተደርገው በሚወሰዱት ቦታዎች ላይ ሰዎቻቸውን የማስፈር ሴራቸው አልሳካ ያላቸው አይሁዶች የኃላ ኃላ ከፍሪማናሲኖች ጋር በማበር የተለያዩ ድራማዎችን በተለያዩ ገዳማት ውስጥ ሰርተዋል ይህም አሁን ለምንመለከታቸው ቅባትና ጸጋ ተሃድሶ እና ማህበረ ስላሴ ዘደቂቀ ኤልያስ ለሚባሉት የክህደት ቡድኖች መፈልፈል ምክንያት ሆኗል፡፡ በየገዳማቱ በገንዘብ የገዟቸውን የበግ ለምድ የለበሱ መነኩሴዎችን በመሰግሰግ ከቻሉ በቀጥታ ቶዎድሮስን በመያዝ የግላቸው ለማድረግ ጥረው ባለመሳካቱ  በየገዳማቱ የሚገኙትን የምስጢር መዛግብት አስመዝብረዋል፡፡
ከዚህ ጋር ተያይዞ የውጭዎቹ አካላት ብቻ ሳይሆን በሰለሞናዊ ስርው መንግስት ስር የነበሩ ከ25 በላይ ነገስታት የቶዎድሮስ የሃይሉ መገኛ ተደርገው ከሚወሰዱት ቦታዎች አንዱ በሆነው የረር ተራራ ላይ መቀመጫቸውን አድርገው ምስጢራቱን ለማግኘት የራሳቸውን ጥረት አድርገዋል ይህም የንጉሱን ሃይል ለመቀራመት መሆኑ ነው፡፡ ቶዎድሮስ የተሰኘው ባለትንቢቱ ንጉስ ከተነገረለት ሃይል አንጻር እና ከፍሪማስነሪዎች ምስጢራዊ አካሄድ አንጻር ንጉስን ከቻሉ የራሳቸው ለመድረግ ካልሆነም ለማጥፋት የሚያደርጉትን ሴራ የሚያስገርም  ባይሆንም የኛ ሀገር የውስጥ ባንዳዎች የነርሱ ጋሻ ጃግሬዎች መሆናቸው ብዙ ነገሮችን አበለሻሽቷል፡፡
ንጉስ ሃይለስላሴ ከሌሎቹ በተለየ የፍሪማስነሪዎች መንገድ በመከተል የሆራ ሃይቅ ላይ የደም መስዋእት በመሰዋት ምስጢራቱን ለማግኘት ሞክረዋል ይህ ሂደትም ለራስተፈርያን መመስረት መንገድ እንደከፈተ የአካባቢ ነዋሪዎች ይገልጻሉ፡፡ በ1998 ዓ/ም  የመንግስት አካላት በየረር ቶዎድሮስ ገዳም የሚገኙ አባቶች ላይ ጥቃት ማድረሳቸው በዋልድባ ገዳም በደጀን በሚገኙ ገዳማት ላይ እየተስተዋለ ያለውም ጥቃት ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሚነሳ ነው፡፡
”  እግዚአብሔር ከቴማን ቅዱሱም ከፋራን ተራራ ይመጣል ክብሩ ሰማያትን ከድኖአል ምስጋናውም ምድርን ሞልቶአል፡፡ ፀዳሉም እንደ ብርሃን ነው ጨረር ከእጁ ወጥቶአል ኀይሉም በዚያ ተሰውሮአል፡፡ ቸነፈር በፊቱ ይሄዳል የእሳትም ነበልባል ከእግሩ ይወጣል፡፡ ቆመ ምድርን አወካት ተመለከተ አህዛብንም አናወጠ የዘላለምም ተራሮች ተቀጠቀጡ የዘላለምም ኮረብቶች ቀለጡ ከዘላለም ነው፡፡ የኢትዮጵያ ድንኳኖች ሲጨናነቁ አየሁ የምድያም አገር መጋረጃዎች ተንቀጠቀጡ ” (ትንቢተ ዕንባቆም 3) ይህን ትንቢት መሰረት አድርገው ናይት ኦፍ ቴምፕላርስ  ይህ ትንቢት የተነገረው ለክርስቶስ ነው ብለው አምነው የቆዩ ቢሆንም ክርስቶስን ከየመን ጋር የሚያገናኘው ታሪክ እንደሌለ ተረዱ በኃላ የነርሱ እርዝራዥ የሆኑ የአረብ ሰዎች ትንቢቱን ከነቢዩ መሐመድ ጋር ለማገናኘት ቢሞክርም ሰውየው የተወለደው እና የኖረው ከየመን በርካታ ኪሎሜትሮች ርቃ በምትገኘው ሳውዲ ውስጥ እንደሆነ ከፍተኛ ተቃውሞ ስለገጠማቸው ትንቢቱ ከምድር ጥፋት ጋር የሚያያይዘው ታሪክ ካለው አንድ ግለሰብ ጋር የሚገናኝ እንደሆነ ገልጸው ትተውታል፡፡
  የቶዎድሮስ የሃይሉ መገለጫዎች ከሆኑትና ከሰባቱ ምስጢራዊ ቦታዎች አንዱ የሆነው የመን(ፋራን) ሲሆን ይህ ቦታም ባለፉት ሺህ አመታት ውስጥ የኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ይጠቃለል ነበር፡፡ ታዲያ ከቶዎድሮስ መነሳት ጋር ተያይዞ እንደሚፈጸሙ ከሚጠበቁት ትንቢቶች አንዱ ኢትዮጵያ ቀድሞ የነበሯትን ግዛቶች ማስመለስ መቻሏ ነው ስለዚህ ከየመን ጋር ተያይዞ የተነሳው ትንቢት መፈጸም የኢትዮጵያ ትንሳኤ ወይም የቶዎድሮስ መነሳት ጋር ተያይዞ ነው ይህን ለማለት የሚያስችለን አንደኛው ነገር ቦታው  ከሰባቱ የክብር ቦታዎች አንዱ መሆኑ እና የነዚህ ቦታዎች ምስጢራት መክፈቻ እና ማእከል ኢትዮጵያ መሆኗ ሲሆን ሁለተኛው በትንቢቱ ላይ የተገለጸው ጥፋት ከቶዎድሮስ መነሻ አስቀድሞ የሚፈጸም ክስተት እንደሆነ በሌሎች የትንቢት መጽሀፍት መጠቀሱ ነው፡፡
ለንጉሱ ቶዎድሮስ መነሻ ተደርገው ከተነገሩት ትንቢቶች መካከል አንዱ በሁለተኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጨረሻ የተነገረው ሲሆን ይሔውም ከሰባት መቶ አስራ ሶስት ዓመታት የጥፋት እና የጨለማ ዘመን በኃላ የኢትዮጵያ ትንሳኤ እንደሚሆን ነው፡፡ በዚህ መሰረት እነዚህ የመከራ ሰባት መቶ ዓመታት የሚፈጸሙት በ2013 ዓ.ም ነው፡፡
ከ 13 ኛው መቶ ክፍለ ዘን ጀምሮ የኢትዮጵያ ግዛት እያነሰ የበሬ ግንባር አክላ ቀርታለች ።  በጎንደር ነገስታት ሀያልነቷ እንደ ቀን ጀንበር ታይቶ እየጠፋ ኖራለች ።  በጠላቶቿ ግራኝ መሀመድን ጨምሮ በዙ መከራ ስታሳልፍ እንደኖረች አስታውሱ ..!
በ1959 ዓ/ም ታየ  የተባለው እሬቶ የተሰኘው ኮከብ ወደምድር ወድቆ  ጥፋት እንደሚያደርስ በዮሐንስ ራዕይ ላይ የተነገረ ሲሆን ይህም እንዲሁ ለቶዎድሮስ መነሻ ምልክት እንደሆነ ይነገራል፡፡ ሌላው በትንቢተ ዕንባቆም 3 ላይ እንደተገለጸው  ምድር በእርስ በእርስ ጦርነት በኢኮኖሚ ድቀት በድርቅ በጎርፍ በእሳት በአውሎ ንፋስ ትጠቃለች ታዲያ ይህ ወቅት ለኢትዮጵያ ትንሳኤ እና ቶዎድሮስ መነሻ ምልክት እንደሆነ ይገለጻል የዓለም ህዝብም ከጥፋቱ ለማዳን ወደኢትዮጵያ ይፈልሳል በዚህም ምክንያት ድንኳኖቻችን ይጨናነቃሉ፡፡ ይሔን ለማረጋገጥ የመናዊ መሆን አይጠበቅብንም 200 ሽ ህፃናት በየመን በረሃ በድርቅ እየረገፉ ሲሆን  ያለ መሪ የቀረችው የፋራን ተራራ መገኛዋ የኢትዮጵያ ግዛት ሀገር የመን አንዷ ምስክር ነች ።
   ከራፋቶኤል እና ቅዱሳት መፅሐፍት የተወሰደ 
 የኢትዮጵያ ትንሣኤ_ያሳየን 
Filed in: Amharic