>
5:13 pm - Thursday April 18, 2080

በረከት ስምኦን -ታክሲደርሚ!!! (ተስፋዬ ሀይለማርያም)

በረከት ስምኦን -ታክሲደርሚ!!!
ተስፋዬ ሀይለማርያም
 
This is my time to lose
 
ታክሲደርሚ እንሰሳት ከሞቱ በሁዋላ በመድኃኒት በማድረቅና  የውስጥ ሰውነታቸውን በልዩ ልዩ ቁሳቁስ በመጠቅጠቅ በህይወት እንደኖሩ አድርጎ የማስቀመጥ ጥበብ ነው፡፡
 
በታክሲደርሚ የደረቀ እንሰሳ ለማያውቀው ሰው በህይወት ያለ ይመስል ያስፈራል፡፡
 
ባላገሩ ነብር በጠመንጃ ገደለና ቆዳውን ገፍፎ ለመሸጥ ወደ ታክሲደርሚ ድርጅት መጣ፡፡ ባለሞያው የቀረበለትን የነብር ቆዳ መረመረና እንዲህ አለ ፤
 
“ቆዳውን አልገዛህም”
“ለምን ጌታው?”
“ቆዳው በጥይት የተበሳበት ቀዳዳ አለው”
“ኧሯ! ታዲያ ነብሩን በጥይት እንጂ በጋቢ አፍኜ አልገድለው”
 
በረከት ስምኦን ወደ ታክሲደርሚ ገባ፡፡ በረከት ሞተ፡፡ ፖለቲካዊ ሞት ሞተ፡፡ እሱ ብቻ አይደለም፡፡ ህወሀትም እንዲሁ፡፡ 
 
በረከተ አለ፡፡ ደግሞም የለም፡፡ አዎ ጠጋ ብለን ብናየው በረከት በህይወት አለ፡፡ ነገር ግን በታክሲ ደርሚ ደርቆ ስለሚገኝ ዋጋ የለውም፡፡ ከዚህ በሁዋላ ጥፋተኛ ሆኖ ቢገኝም ባይገኝም ፣ ቢፈረድበትም ባይፈረድበትም በረከት (መብራህቶም) He is sufficiently cornered .
 
በመጨረሻም ከ25 ዓመት በፊት የጎንደር ህዝብ ለበረከት የገጠመለትን ግጥም ልጋብዛችሁ ፤
   በረከት አገሩ ….  ስለናፈቀው፣
   ዳሽን አናት ሆኖ……አሥመራን አየው፡፡
  በረከት በሰው ቤት…ሲገባ ሲወጣ ፣
   እኔም ቤት አልቀረ…..መርገም ይዞ  መጣ
—–
This is my time to lose
 
የአለማችን ተፈላጊው ወንጀለኛ ኤሊች ራሜሬዝ ሳንቼዝ ወይም ካርሎስ ቀበሮው ሱዳን ውስጥ በፈረንሳይ ፖሊሶች ሲያዝና ካቴና እጆቹ ላይ ሲጠልቅለት “This is my time to lose” ሲል ፖሊሶቹ ፊት በፀፀት ተናገረ፡፡
 
የኛው ቁራው በረከት የካርሎስን ታሪክ በሚገባ የሚያውቀው ይመስለኛል፡፡ እንደ ካርሎስ this is my time to lose  ባይልም በትግርኛ “ቀደም ሹምባሽ ነይርና ሎሚ ተዋሪድና” ትርጉም “በፊት የተከበርን ነበርን አሁን ተዋረድን” እንደሚል እርግጠኛ ነኝ፡፡ 
 
በርዬ ምን ታደርገዋለህ karma is karma እንልሀለን ፡፡ አንተ ደግሞ karma is a bitch  እንደምትለን አንጠራጠርም፡፡
 
በረከት ስምኦን  የተመሠከረለት ገጣሚ ነው፡፡  የሰው ህይወትና የአገር ሃብት እንደዘረፈው ሁሉ ምርጥ ቅኔ ዘራፊም ነው፡፡ በረሃ ሆኖ  በአሁኗ ሚስቱ የአይን ፍቅር ተንገብግቦ የቋጠራት ዝነኛ ስንኝ እነሆ
 
እንደተፋቀርን ላንተያይ – ሳንተያይም ልንፋቀር ፣
እንደመናኝ ከዓለም ነገር –  ከስሙ ተራ ስንባረር ፣
በታጋይ ህግ ተገድበን –  በአጉል ሥርአት ስንጠፈር ፣
መቸስ ምን እንላለን – በተስፋ ከመሞት በቀር፡፡
 
ምናለ በረከት ገጣሚ ብቻ ሆኖ ቢኖር ኖሮ!!!
Filed in: Amharic