>

የሁለቱ ፕሮፌሰሮች ወግ !!! (ሳምሶን ሚሀይሎቪች)

የሁለቱ ፕሮፌሰሮች ወግ !!!
ሳምሶን ሚሀይሎቪች
 
ህይወት ሁሌም ባይሆን ፍትህ በምድር poetic justice አይነት ነገር ትጫወታለች። ደጋጎችና ቅን አሳቢዎች ውጣ ውረዱን አልፈው ሲያሸንፉ ፣ እበላ ባዮች opportunists ደግሞ ቀን ሲጥላቸው የምናይበት አጋጣሚ ከስንት አንድ አይጠፋም። የፕሮፌሰር ምንዳርያለው ዘውዱ እና የሌላው መምህር ዘሪሁን ተሾመ ታሪክ ይህን አይነት እውነታ አለው። 
 
በኢትዮጵያውያን አቆጣጠር 1985 ምንዳርያለውም ዘሪሁን ተሾመም ” የድሮ ስርዐት ናፋቂ ” ተብለው ከሚያስተምሩበት ዩኒቨርሲቲ ተባረሩ። ዘሪሁን ወደ እሜሪካ መጭ አለ ፣ ምንዳርያለው ሀገሩ ላይ ፍዳውን ተቀበለ በስተመጨረሻም ወደ አያቶቹ ስራ ግብርና እንዲመለስ ተገደደ። እነ አዜብ ጎላ በአንድ ሌሊት ከ፬ኛ ክፍል ዘለው የህግ ምሩቅ ሲሆኑ “ነፍጠኛው” ምንዳርያለው መሀይም ይሆን ዘንድ ከሚሰራበት ዱካውን እየተከተሉ የስንብት ደብዳቤ የሚያጽፉበት ደህንነቶች ተመደቡበት። 
 
ወደ ምርጫ 97 መቃረቢያ ወራት ህወሃት ‘ በድሮ ስርአት ናፋቂነት’ ከስራው ያባረረው ዘሪሁን ተሾመ አዲሷን ሙሽራውን ሚሚ ስብሀቱን ተከትሎ ወደ ሀገሩ ተመለሰ። ዘሪሁን ወደሀገሩ ሲመለስ ሚስት ብቻ ሳይሆን ‘ኢፍትን’ የምትባል ከደህንነት ጋር የምትሰራ ጋዜጣ ይዞ ነው አደባባይ የወጣው። ዘሪሁን በግፍ ከሀገሩ ካስወጣው አፋኝ ቡድን ጋር ሆኖ እርሱም በተራው አንገታቸውን ቀና ያደረጉ ዜጎችን ያሳድድ ጀመር ። ኢፍትን ዛሬ ከደህንነት የመጣ መረጃ ያወጣችበት ተቃዋሚ አልያም ጋዜጠኛ በሀገር አይሰነብትም ወይ ዘብጥያ ትወርዳለህ ካልሆነም ኑሮህን ጣጥለህ ወደ ስደት ትፈረጥጣለህ። 
 
ዘሪሁን ተሾመ በራሱ ምርጫ በግፍ ከስራ ያባረረውን ስርዐት ማገልገል ሲጀምር ምንዳርያለው ደግሞ በተደጋጋሚ ይቀርብለት የነበረው የይቅርታ ጠይቅ ተማጽኖ እምቢ ብሎ የግብርና ኑሮውን ይመራ ነበር። 
 
ዛሬስ ? ዛሬ እነ ዘሪሁን ተሾመ ይፏልሉበት የነበረው የክብ ጠረጴዛ ውልቅልቁ ወጥቷል። ዘሪሁን ከደህንነት እንደ ሽልማት ያገኘው ‘ ዛሚ ሬዲዮ ‘ በኪሳራ ተዘግቶ እርሱና ሚስቱ ስደትን መርጠው self imposed exile ወደ እሜሪካ አቅንተዋል። የእነ ሚሚና ዘሪሁንን አይነት ገመና የተሸከመ ሰው አሜሪካም ብትሆን ቀላል ኑሮ አትሆነውም ። ሀበሻ ባየህ ቁጥር ‘ ምን ይለኝ ይሆን ? ” ብሎ መሳቀቅ በራሱ ከባድ ስቃይ ነው። ገበሬው ፕሮፌሰር ምንዳርያለው ዘውዱ ደግሞ ወደሚወደው የመምህርነት ስራ ተመልሷል ። ከዚህ በላይ ብድር በምድር  poetic justice ይናራልን ?
Filed in: Amharic