>

" የባርነት ምቾትን የመረጠ የውሻ አሟሟትን መርጧል - ነጻነትን የመረጠ ሰው ሞቱ የሰማዕት ነው" (ፕሮፌሰር ምንዳርያለው ዘውዴ)

” የባርነት ምቾትን የመረጠ የውሻ አሟሟትን መርጧል – ነጻነትን የመረጠ ሰው ሞቱ የሰማዕት ነው”
የፕሮፌሰር ምንዳርያለው ዘውዴ ሙሉ ቃለመጠይቅ
* ወገን  በአረመኔው በወያኔው ተወልደ  ገ/ማርያም  ስለተባረረው የጎጃም አማራው ፓይለት ገበሬ  ዮሐንስ  የሰማነው ልክ የዛሬ 3 ወር  ገደማ ነበር እኮ አይ ወያኔ እህ!!። 
* ዛሬ ደግሞ  የመለስ ዜናዊ ናዚአዊ እርምጃ ሰለባ ስለሆነው ስለፕሮፌሰሩ ገበሬ ታምር እየሰማን ነው። እህህህህህ
—-
I am in a kind of bitter sweet emotion. Happy because he is free at last. The TPLF shackle that tied his  hand is broken and the fetter, the chain that bounded him is torn up. Embittered when I think of the perils he went through.
I am in a mood of እየሳቁ ማልቀስ. Tear drops are rolling from my right and left eyes – one of happiness and the other of pain and sadness. My God!
ኢቲቪ መዝናኛ ያቀረበው የፕሮፌሰር ምንዳርያለው ዘውዴ ሙሉ ቃለመጠይቅ ይሄንን ይመስላል:
:ተማሪ እያሉ ምንዳር ያለው ዘውዴ የA ሳይሆን የA+ ተማሪ ነበሩ:: ከመጀመርያ እስከ ተርሚናል ዲግሪያቸው ድረስ የከፍተኛ ማዕረግ ተመራቂ ነበሩ:: የሰቃይ ደንቡ ነውና አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ መምሕር ሆነው ተቀጠሩ:: በማስተማር ዘመናቸውም – እጅግ የላቀ መምሕር- በመሆን በተደጋጋሚ በዩንቨርስቲውም ሆነ በተማሪዎቻቸው ተሸልመዋል::
ህወሀት አዲስ አበባን ስትቆጣጠር ግን ብቃት ያላቸው የዩንቨርስቲ ምሁራን የጥቃት ሰለባ ሆኑ:: ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ብቻ 41 ፕሮፌሰሮች በ24 ሰዓት ግቢውን ለቀው እንዲወጡ ተበየነባቸው:: ምንዳርያለው አንዱ ነበሩ:: በሌሎች የትምህርት ተቋማት የሚገኙ ጎምቱ መምህራንም እየተለቀሙ ተባረሩ:: ከሲኒየርነታቸው አንጻር ያዲስ አበባ ዩንቨርስቲ 41ዱ ምሁራን ገዝፎ ቢነገርም በሀገር ደረጃ የተባረሩት የክፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከ200 በላይ ነበሩ:: ኢትዮጵያ ለፍታ ያስተማረቻቸው ከ200 በላይ ብርሃኖቿ እንዳያበሩ ተከለከሉ::
በነገራችን ላይ ጣልያንም አዲስ አበባ እንደገባ የመጀመርያ ስራው አሉ የሚባሉ የኢትዮጵያን ምሁራን መግደል ወይ ደግሞ ወደ ግዞት መላክ ነበር::አለማዊም መንፈሳዊ ምሁራኖችን እያደነ ያስርና ይገድል ነበር:: በዚህ እስር ምክንያት አይናቸውን ያጡት ሊቁ አለቃ ኪዳነወልድ ክፍሌ በመጽሓፋቸው ” የኢትዮጵያ ብርሃን የሆኑ ሊቃውንታ እየታደኑ ግዞት ተወረወሩ” ብለውታል::
የሚገርመው እነዚህ የአዲስ አበባ መምህራን አለወንጀላቸው መባረራቸው አይደለም:: ከተባረሩም በኋላ የትም ቦታ እንዳይቀጠሩ ይደርሳባቸው የነበረው ክትትል ነው:: የውጭ ድርጅቶችና ኤምባሲዎች ውስጥ እንኳን ሲቀጠሩ የህወሀት ሰዎች የተቀጠሩበት ቦታ እየመጡ ቅጥራቸው እንዲሰረዝ ያደርጉ ነበር:: ፕሮፌሰር ምንዳር ያለው የውጭ ኤምባሲ ተቀጥረው ነበር ( ይመስለኛል ያሜሪካ ኤምባሲ) የሚገርመው ግን መለስ ራሱ ኤምባሲው ድረስ ሄዶ ” ፕሮፌሰር ምንዳርያለውን ከስራ ያስወጣነው ለመቅጣት ነው:: እንዴት እናንተ ትቀጥሩታላችሁ” ብለው አስባረውታል::
እርግጥ ነው መለስ ካጣልያን ባንዳ ቤተሰቦቹ ሲዋረድ በመጣ የበታችነት ስሜት የሚሰቃይ አሳዛኝ ፍጡር ነበር:: የሀገሪቱን ምሁራን በማሰርና በማጥፋት እሱ ጎልቶ የሚታይ ይመስለው ነበር:: ዋናው ምክንያቱ ግን ይህ ብቻ አይደለም::
እውነቱን እንነጋገር ከተባለ ጉዳዩ የታቀደ structural racism እና  intellectual genocide ነው:: ትውልድን ለመግደል ዋናው ተግባር የዛን ትውልድ ምሁራንና አዋቂዎችን ማጥፋት ነው:: ምንዳር ያለውና ሌሎቹን ምሁራን የተፈለገው እንዳያስተምሩ ከሆነ ለምን ሌላ ቦታ እንዳይቀጠሩ እግር በግር እየተከታተሉ ማስባረር አስፈለገ? ግልጽ ነው:: እነዚህ ምሁራን ተርበው: ተዋርደው : ለስነ ልቡና ቀውስ ተጋልጠው እንዲጠፉ ስለሚፈለግ ነው:: This perfectly is intellectual genocide. የተባረሩት መምህራን የመጡበትንም የጎሳ መሰረትም ስንመለከት – 99%ቱ ተባራሪዎች የአማራና የኦሮሞ ጎሳ ተወላጆች ናቸው:: በመዋቅር ደረጃ እና በይፋ ዘር ተኮር ምሁራንን የማጽዳት ስራ ነበር የተካሄደው- structural racism.
ዛሬ ብዙው ሰው “በዩንቨርስቲዎች የሚታየው የተማሪዎች በዘር ተቧድኖ መጨፋጨፍ ከየት መጣ?” ብሎ ባግራሞት ይጠይቃል:: ድሮ ዩንቨስርቲዎች የሚታወቁት ለሙሉ ኢትዮጵያውያን በመጮህና ለፍትህ በመታገል ነበር:: ድሮ ብቃት ያላቸው አካዳሚሺያንስ ለተማሪዎቻቸው ሁለንተናዊ ( universal) የሆነ እውቀትን ያስተምሩ ነበር:: ተማሪዎቹም ተቀርጸው የሚወጡት በመምህራኖቻቸው በመሆኑ የሚመስሉት መምህራኖቻቸውን ነበር:: ዘር የሚበቅለው እንደተዘራው ነው:: ዛሬ እነዚህ መምህራን ተባረው በምትካቸው ” ድንጋይ ማምረቻ” ከሚባሉት ከነሲቪል ሰርቪስ የሚወጡ ካድሬ መምህራኖች የሚያስተምሯቸው መምህራንም ራሳቸው መምህራኖቻቸውን መስለው ይሄው በየዩንቨስቲው የምናየውን እያየን ነው::ብዙው ቦታ የዩንቨስርቲ ተማሪዎች ግጭት የሚመራው በነዚህ ሀሳዊ መምህራን ነው:: ዛሬ ብቃትን ሳይሆን ዘርን አይቶ ግሬድ የሚሰጥ መመህር ጉድ አያሰኝም::የተለመደ ከመሆን አልፏል::
አሁንም ቢሆን በየዩንቨስቲው ምርጥ ምሁራን ቢኖሩም : የተቻላቸውን ምርጥ ዜጋ ለማፍራት ቢጥሩም – ዋናውን መንበር የተቆጣጠሩት የፖለቲካ ሹመኞችና የዘር ነጋዴዎች ( Ethnic enterpreuters) ናቸው:: ከዩንቨርስቲ ፕሬዝዳንት ቅጥር ጀምሮ መስፈርቱ ዘርና ቋንቋ እንጂ ብቃት አይደለም:: ሌላው ቀርቶ ዩንቨስርቲዎች የክብር ዶክትሬት የሚሰጡት ላካባቢያቸው ምርጥ ሰው እየሆነ ነው:: ዩንቨስርቲዎች የስልጠና :ምርምርና ስርጸት ቦታዎች ከመሆን ይልቅ -የጎሳ : የቤተሰብ : የፖለቲካ ቤት ሆነዋል::
የዩንቨርስቲ መምህራን ቅጥርም አንዱ መስፈርት ትውልድ ደም ዘር ከሆነ ከራርሟል:: በአብዛኛው ዩንቨስቲዎች የብቃት መመዘኛ የፖለቲካ ታማኝነት እንጂ አካዳሚያዊ ብቃት አይደለም::
እናም በቅጥረኞቹ እንደታለመው እንደታቀደው – ዩንቨስርቲ ለመማር ሄዶ እርስ በርሱ በደንጋይ የሚጋደል- ሀገሬን ለቀህ ውጣልኝ .. የሚል ትውልድ አፈራን:: you reap what you sow!!!
የነፕሮፌሰር ምንዳር ያለው አይነት ምሁራን መመለስ ለኢትዮጵያ ትንሳኤ ተስፋ ነው::
 As a concluding remark, thank  you Dr. Abiy !
“ሰው የባርነት ምቾትን ከመረጠ ለውሻ አሟሟት መፈረሙ የተረጋገጠ ነገር ነው፡፡ በባርነት ደልቶት የኖረ ኑሮው የአሳማ ነው ሞቱ የውሻ ነው፡፡ በነጻነት ተንገላቶ የኖረ ሕይወቱ ኑሮው የጀግና ነው ሞቱ የሰምዓት ነው፡፡ በሌላ አነጋገር የሰው ልጅ እግዚአብሔር የፈጠረለት ግብ እንዲያስብ ነው፡፡ ማሰብህን በሆድህ ተክተህ ከዛ በሁዋላ ከአሳማ የምትለየው በሁለት እግርህ መሄድህ ብቻ ከሆነ እንዲህ ዓይነቱ ፍጡር እንዲህ ዓይነቱ ኑባሬ ሁሉን ነገር የሸጠ ነው ነጻነትን ጨምሮ፡፡ አንድ ጊዜ ነጻነትህን ለአምባገነን አሳልፈህ ከሰጠህ ሌላ ግዜ ልጠቀም ብትል ከሱ ልትበደር ይገባሃል፡፡ ነጻነትን ከአምባገነን እየተበደሩ ከመኖር የባሰ በዚህ ምድር ላይ ያለ ትልቅ ምሬት (tragedy) የለም፡፡ በሕይወት ውስጥ ያለው የመጨረሻው ትራጄዲ የራስን ነጻነትህን ከአምባገነኖች እየተበደርክ መኖር ነው፡፡ ለምን ትበደራለህ? መጀመሪያውኑ አሳልፈህ ባትሰጥ ኖሮ፤ ለምን መጀመሪያ አሳልፈህ ትሰጣለህ? ለሆድህ ቅድያማ ባትሰጥ ኖሮ፤ ለምን ለሆድህ ቅድሚያ ትሰጣለህ? መጀመሪያውኑ የአሳማነትን ሕይወትና የአሳማን አሟሟት ባትመርጥ ኖሮ፡፡ “
Filed in: Amharic