ኣብርሃ ደስታ የኣረና ፓርቲ ስራ ኣስፈጻሚ በመቀሌ ዩኒቨርስቲ መምህር የሆነውና በተለይም በማህበራዊ ድረ-ገጾች (ትዊተርና ፌስ ቡክ) የስርዓቱን መበስበስ በተጨማጭ መረጃ በማጋለጥ የሚታወቀው በዛሬው ዕለት በታጣቂዎች እየተደበደበ ወደኣልታወቀ ስፍራ መወሰዱን በኣካባቢው የነበሩ ሰዎች ለኣረና ጽህፈት ቤት እንደገለጹላቸው ከፓርቲው ኣባላቶች ለማወቅ ችለናል።
የኣረና ፓርቲ ኣባላቶች የኣብርሃ ደስታን ሁኔታና በየት እስር ቤት እንደሚገኝ ለማወቅ ያደረጉት ሙክራ እስካሁን ኣልተሳካላቸውም። ተጨማሪ መረጃ እንዳገኘን እናቀርባለን።