>

የሟቹ የአቶ መለስ ዜናዊ ሕገ መንግሥት አጻጻፍ አጭር ታሪክ፤ (ዉብሸት ሙላት)

የሟቹ የአቶ መለስ ዜናዊ ሕገ መንግሥት አጻጻፍ አጭር ታሪክ፤
ዉብሸት ሙላት
በመጀመሪያ ሰንአፌ ላይ መለስ ዜናዊ እና ሌንጮ ለታ (ኢሳይያስ አፈወርቂም አለበት የሚሉ አሉ) የሽግግር መንግሥት ቻርተሩን ጻፉ፡፡
ይህ የእነ መለስ ዜናዊን ቻርተር መልሰዉ እነ መለስ በመረጧቸዉ እና ባጸደቁት ከሰኔ 24-28/1984 ዓ.ም. በተደረገዉ ሰላም ጉባኤ ተሳታፊ ጸደቀ፡፡ በዚህ ጉባኤ 24 የብሔር ፓርቲ ተወካዮች ተሳትፈዋል፡፡ ቻርተሩ እንደጸደቀ 87 አባላት ያሉት የተወካዮች ምክር ቤት ተቋቋመ፡፡ እድሜዉ 2 ዓመት ካልሆነ ግን 2 ዓመት ተኩል እንዲሆን ተወሰነ፡፡ ነገር ግን በሟቹ በመለስ ዜናዊ ማንአለብኘነት እስከ 1987 ሕዳር 29 ቀን ድረስ ቆዬ፡፡ ከዘጠኝ ወራት በላይ ሕጋዊ መሠረት ሳይኖረዉ በመለስ ዜናዊ መሠረትነት ብቻ ቆየ፡፡
የሰላም ጉበኤዉ ሲጠናቀቅ የአገሪቱ ፕሬዚዳንትና የተወካዮች ምክር ቤት ሊቀመንበር (ሥልጣኑ ከሁሉም በላይ ነዉ) አቶ መለስ ዜናዊ ሆነ፡፡
አቶ መለስ አገሪቱ ፕሬዚዳንትም የምክርቤቱም አፈጉበኤ ሆኖ የሕገ መንግሥት አርቃቄ ኮሜሽን አዋጅ ቁጥር 24/1984ን አጸደቀ፡፡ ወይም አስጸደቀ፡፡ በእሱ ስም ነሃሴ 12 ቀን 1984 ዓ.ም. ታወጀ፡፡ የኮሚሽኑ ተጠሪነትም አቶ መለስ አፈጉባኤ ለሆነበት ምክር ቤት ነበር፡፡
ሟቹ መለስ፤ የሕገ መንግሥት አርቃቂ ኮሚሽኑ በሽግግር መንግሥቱ ቻርተር መንፈስ የተቃኘ ሕገመንግሥት አዘጋጅተዉ እንዲያቀርቡ አስወሰነ፡፡
በአዋጅ ቁጥር 24/1984 መሠረት የሚቋቋመዉ የሕገ መንግሥት ኮሚሽን አርቅቆ ያመጣዉን ሕገመንግሥት የሚጸድቀው ሟቹ መለስ በአፈጉባኤነት የሚመራዉ ምክር ቤት ነዉ፡፡ ምክር ቤቱ ካጸደቀው በኋላ ለውይይት ወደ ሕዝብ እንደሚላክ በተደነገገዉ መሠረት 72 አንቀጾች ያሉትን ረቀቂ መጋቢት 29 ቀን 1986 ለመለስ ምክር ቤት አስረከበ፡፡ የመለስ ምክር ቤት 35 አንቀጸችን ጨምር 107 አንቀጽ ያለዉ ሕገ መንግሥት ጥቅምት 19 ቀን 1987 ለሕገ መንግሥት አጽደቂ ጉባኤያተኞች አስረከበ፡፡
እነ ሟቹ መለስ ለዚህ 107 አንቀጽ ለነበረዉ (ኋላ ላይ የአንቀጹ ብዛት 106 ሆኗል) ሕገ መንግሥት ራሳቸዉ ማብራሪያ ጻፉለት፡፡ በማብራሪያዉ መሠረት ሕዝባዊ ዉይይት ተደረገ ተባለ፡፡ ሕዝብም ተቀበለዉ አስባሉ፡፡
 ሟቹ መለስ፣ አፈጉባኤ ሆኖ (ፕሬዚዳንትም ጭምር) የሕገ መንግሥት አጽዳቂዎች የሚመረጡበትን አዋጅ አ(ስ)ጸደቀ፡፡ በዚሁም መሠረት የአሁኑ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጋር የሚጠጋጉ ብዙዎቹ ስለ ሕገመንግሥት ሰምተዉ የማያዉቁ ሰዎች ከጥቅም 19 እስከ ህዳር 29 ቀን 1987 ዓ.ም.  (ለአርባ ቀናት) ተሰብስበዉ እነ ሻለቃ አድማሴንና የአማራ ሕዝብን ሲሳደቡ ከርመዉ ሕገ መንግሥት የተባለዉን ሰነድ አጽደቀዉ መልስዉ በዶ/ር ነጋሶ አማካይነት ለሟቹ መለስ አስረከቡት፡፡
ሰንኣፌ ቻርተሩ ተጻፈ፡፡ አዲስ አበባ በመለስ ሊቀመንበርነት ጸደቀ፡፡ መለስ አፈጉባኤም ፕሬዚዳንትም ሆነ፡፡ አፈጉባኤ መለስ አርቃቂ ኮሚሽን አዋጅ ፈርሞ አጸደቀ፡፡ የኮሚሽኑ ተጠሪነትም ለእሱዉ ምክር ቤት ሆነ፡፡ ኮሚሽኑም ሰንአፌዉን ቻርተር መንፈስ የተላበሰ ሕገመንግሥት እንዲጽፍ ታዘዘ፡፡ ኮሚሽኑ ሕገ መንግሥት ጽፎ ሲጨርስ የመለስ ምክር ቤት 35 አንቀጾች ጨምሮ አጸደቀው፡፡ ማብራሪያም ጻፈለት፡፡ የመለስ ምክር ቤት የሕገመንግሥት አጽዳቂ ጉባኤ አስመርጦ ለአርባ ቀን አማራን እንዲሰድብ አስደርጎ ሕዳር 29 ቀን ሕገ መንግሥት ተቀበለ፡፡ አለቀ፡፡
ሕገ መንግሥቱ የሟቹ የመለስ ነዉ፡፡ መለስ ደግሞ ጽንፈኛ ሕወሃት ነዉ፡፡ ህወሃት ደግሞ ለመፈጠሯ ምክንያቷ አማራን መጥላት ነዉ፡፡
(የሱፍ ኢብራሂም በኤልቲቪ የተናገረዉን ዘርዘር አድርጌ በጽሑፍ ሳቀርበዉ እንጂ አድስ ነገር የለዉም፡፡ ሐጂ ነስራላህ የተናገሩት ሙሉ በሙሉ እዉነት ነዉ ለማለት ነዉ፡፡)
Filed in: Amharic