>

ብንሸሽም ጦርነቱ አይቀሬ መሆኑ ተረጋግጧል!!! (ለማ ቦራ)

ብንሸሽም ጦርነቱ አይቀሬ መሆኑ ተረጋግጧል!!!
ለማ ቦራ
ጀኔራል ፃድቃን እንዳለው ”  ፅንፈኛው አማራ ህዝብ የወቅቱ ጥያቄ የተስፋፊነት ነው ። አዳራሹ በጭብጨባ ቁለጠ። ደገመ ጀነራል ” ጦርነቱ ከተጀመረ የትግራይ ህዝብን ጠንቅቄ ስለማውቀው በአሸናፊነት ስለመደምደሙ ቅንጣት ያክል አያሳስበኝም ”  ሌላ ጭብጨባ!!!
—-
ታሪካዊ ሀላፊነት የሚጠይቅ ግዜ የማይሰጥ ግዜ ላይ እንዳላችሁ አውቃችሁ ስራችሁን ሳትተኙና ሳትሰለች ልትጠቀሙ ይገባል። ተሸናፊነትና ግጭትን መሸሽ ብቻውን ከጦርነት አይከላከልም። ጠንቅቀን የምናውቀው ግን አብዝተን የማንፈልገው ጦርነት ላይመለስ እየመጣ እንደሆነ ግድ ሊላችሁ ይገባል። ነገሮችን አደባባይ ላይ ማስጣት ባያስፈልግም እንኳን ስራዎችን ግን በሁሉም ዘርፍ ሳይታክቱ መስራትና ህዝባችንን ከጫፍ ጫፍ ግንዛቤ ፈጥሮ ማንቀሳቀስ ላይ በፍጥነት ተሰርቶ ሊጠናቀቅ ይገባል።
ትላንት መቀሌ ከተደረገው ህወሀት መራሽ ስብሰባ ባብዛኛው አማራ ህዝብ ላይ ለመዝመት ያጠናቀቁት ዝግጅት ተስተጋብቷል። በተለይ optimistic Thinker የተባለውንና በነመለስ ዜናዊ በ1994 አም አንጃ ተብሎ ከጦር ሀይሎች ኢታማዦር ስልጣኑ ተባርሮ በመሀይሙ ሳሞራ የኑስ የተተካው ፃድቃን ገብረተንሳይ በስብሰባው ላይ ከተናገረው ጦርነቱ አይቀሬነቱን ብቻ ሳይሆን አማራው ህዝብ ላይ ውጊያ ለመክፈት ዝግጅታቸውን አጠናቀው የማስጀመሪያ ደወል ብቻ እንደሚጠብቁ መገንዘብ ቀላል ነው።
ጀኔራል ፃድቃን እንዳለው ”  ፅንፈኛው አማራ ህዝብ የወቅቱ ጥያቄ የተስፋፊነት ነው ። አዳራሹ በጭብጨባ ቁለጠ። ደገመ ጀነራል ” ጦርነቱ ከተጀመረ የትግራይ ህዝብን ጠንቅቄ ስለማውቀው በአሸናፊነት ስለመደምደሙ ቅንጣት ያክል አያሳስበኝም ”  ሌላ ጭብጨባ ከአዳራሹ።
ከዚህ በላይ በሁሉም የወያኔ ታዳሚወችና ጭፍሮቻቸው አቶ በረከትን ጨምሮ በአማራው ህዝብ ላይ ጦርነት ሲያውጁ ተስተውለዋል። ይገርማል ይህ ህዝብ አምላኩን አመስግኖና መጠጊያ አድርጎ ሀብት ንብረቱን እየተዘረፈ ፡ ዘሩ እየጠፋ ፡ ከማንኛውም አገራዊ ጉዳይ እንዲገለል ፖለቲካዊ ሴራ ሲፈፀምበት ሁሉ ችሎ በኖረ ዛሬም አምቡላችሁ ገነፈለባችሁና ለፈፅሞ ማጥፋት በአደባባይና በየአዳራሹ ጦርነት ልትከፍቱበት በግልፅ ተሰብስባችሁ ትማማላላችሁ። ሞክሩት ካዋጣችሁ ሂዱ መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ ።
Filed in: Amharic