>

ዶክተር አብይ እና ለጀነራል ሰዓረ ዜጋ ለሂወቱ ዋስትና አጥቶ ዝምታችሁ እስከመቼ ይሆን ?!? (ሀብታሙ አያሌው)

ዶክተር አብይ እና ለጀነራል ሰዓረ ዜጋ ለሂወቱ ዋስትና አጥቶ ዝምታችሁ እስከመቼ ይሆን ?!?
ሀብታሙ አያሌው
እነዚህ የኦነግ የእጅ ስራዎች የሰው ልጅ አውሬ ሊሆን እንደሚችል ማሳያ ይሆናሉ !!  ወንድሞቻቸውን ገድለው እንዲህ መሬት ለመሬት በአደባባይ ይጎትታሉ። ዜጋ ለሂወቱ ዋስትና አጥቶ በወጣበት ይቀራል የመከላከያ ሚኒስቴር ስለ ሪፎርም እና አደረጃጀት ዜና ያስነግራል፤ የኦሮሚያ ክልል አስተዳደር የህግ የበላይነት በማስከበር ለዜጎች ዋስትና መስጠት አልቻልኩም የፌደራል መንግስት ጣልቃ ይጋባ ብሎ ፈቃድ ሰጥቷል።  ታዲያ እነዚህ ከመከላከያ አቅም በላይ ሁነው በየቀኑ ታጥቀው ህዝብ የሚፈጁት እነማን ናቸው ?  በኦሮሚያ ኦነግን ጨምሮ ሁሉም የፖለቲካ ኃይሎች በጋራ ለመስራት ተስማሙ የሚል ዜና የተነገረው በቅርቡ ነው። ታዲያ ይሄ ኃይል ማን ነው ?  ጀነራል ሰዓረ ለዚህ አስቸኳይ መልስ ይስጡን። ዶክተር አብይ የጦር ጠቅላይ አዛዥነት ስልጣንዎ በነዚህ ላይ የደቂቃ ትዕግስት ሊኖረው አይገባም። እያንዳንዱ ትዕግስትዎ በየቀኑ የንፁሃን ዜጎቻችንን ነፍስ ከቀጠፈ ትግስትዎ ልክ ኑሮት እዚህ ጋር እንደ መሪ ቁጣዎ ያስፈልጋል።   የሚያምኑበት መፅሐፍ ቅዱስም “ተቆጡ ነገር ግን በቁጣችሁ ላይ ፀሐይ አይግባ” ይላል። ቁጣ በቦታው መልካም ነው፤ ክርስቶስም በቤተመቅደስ ወንበዴዎችን ከተቆጣ በኋላ ጅራፍ ማንሳቱን የታወቀ ነው።  እነዚህ የተደራጁ ጨካኝ ወንበዴዎች ጅራፍ ያስፈልጋቸዋል።
Filed in: Amharic