>
5:13 pm - Monday April 19, 7852

ልዑል አልጋ ወራሽ አስፋው ወሰን በታህሳስ 1953ቱ ግርግር ለሕዝብ ያሰሙት ዱስኩር. . (አቻምየለህ ታምሩ)

ልዑል አልጋ ወራሽ አስፋው ወሰን በታህሳስ 1953ቱ ግርግር ለሕዝብ ያሰሙት ዱስኩር. . . 
አቻምየለህ ታምሩ
ከዛሬ ሀምሳ ስምንት አመታት በፊት ግርማሜ ንዋይ የተባለ ደም የተጠማ ወሮበላ ከወንድሙ ጋር በመሆን «ግብስብሶችን መፍጀት» የሚለውን የለውጥ መርሁን  ተግባራዊ ለማድረግ  ለእርድ ያሰቧቸውን  የኢትዮጵያ አርበኞች ወደሚታረዱበት ቄራ ከቤታቸው እየጠሩ ያስገቡበት ቀን ነው። ይህ ክስተት «የታህሣሥ ግርግር»  ወይንም በንጉሠ ነገሥቱ ላይ «የተቃጠ ስዒረ መንግሥት»  እየተባለ ይጠራል።
ኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ ለማምጣት ተነሳን ያሉን  እነ መንግሥቱ ንዋይ ውንብድናቸው ሲከሽፍ መንግሥቱ ንዋይ ራሱ  አስቀድሞ ተኩሶ  ያለፍርድ የገደላቸው  የኢትዮጵያን የለውጥ አባትና የመጀመሪያዉን የሕዝባዊ ኑሮ እድገት ሚንስትር የነበሩትን የአገር አድባሩን  ጀኔራል ሙሉጌታ ቡሊን ነበር።  ትምርታቸውን  ያልጨረሱት እነ ዋለልኝ መኮነን እንደሚወሩት ሳይሆን  የያኔዋ ኢትዮጵያ ጀኔራል ሙሉጌታ ቡሊ ይመሩት በነበረው የሕዝባዊ ኑሮ እድገት ሚኒስቴር በእድገት ወደኋላ የቀሩ [እንደ ኩናማ፣ ሻንጉላ፣ ጋምቤላ፣ ከረዩ፣ ሐመር፣ ወዘተ. . .] ነገዶች  ሳይቀር በልዩ ሁኔታ እንዲያድጉ በዳይሬክተር የሚመራ ተቋም ተፈጥሮ በዘለቂነት የሚለሙበትን እና ፍትሐዊ ተጠቃሚ የሚሆኑበት ስርዓት ተዘርግቶ ነበር። ይህ የኢትዮጵያ የመጀመሪያው የተቀናጀ የልማት ጅምር የተስተጓጎለው ለለው ተነሳሁ ያለውን ሚንስትሩን ጀኔራል ሙሉጌታ ቡሉን ሲገድል ነበር። በዚህ ጉዳይ በሌላ ጊዜ በሰፊው እንመለስበታለን።
ከታች የታተመው ድምጽ አልጋወራሽ አስፋወሰን ኃይለ ሥላሴ  ከ58 ዓመታት በፊት ልክ በዛሬ እለት ለሕዝብ በሬዲዮ ያሰሙት ዲስኩር ነው። ዲስኩራቸውን ያሰሙት በነመንግሥቱ ንዋይ ተገደው እንደሆነ የሚያትቱ ብዙዎች ቢሆኑም እኔ ሆኖም ግን አልጋወራሽ ንግግሩ ያደረጉት  በፍላጎታቸው ነው። ይህንንም እሳቸው ራሳቸው በ1967 ዓ.ም. ለሕክምና ውጭ አገር በነበሩበት ወቅት ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ አመላክተዋል። እነሆን ታሪካዊን የአልጋወራሽ ዲስኩር. . .
Filed in: Amharic