>

የኢሳያስ ኩራት እና የህወሃት ውርደት! (ቀጥተኛ ትርጉም በአብርሀ በላይ)

የኢሳያስ ኩራት እና የህወሃት ውርደት!
ቀጥተኛ ትርጉም በአብርሀ በላይ
የኤርትራው ኢሳያስ አፈወርቂ ህወህቶችን አጅጉን ይንቃቸዋል። ይህ ባህርዩ ደግሞ ከጥንት ከጥዋቱ ነው። ለምን ቢባል ለካስ ከነሱ ጋር አፍ መክፈት የውርደት ጥግ መሆኑን ካገር በፊት ያውቅ ኑሯል! ለዛ ነው ህወሃት በኃይለማርያም ደሳለኝ በኩል 53 ጊዜ “እባክህ ታረቀን” ብለው መሬት ላይ ቢንከባለሉም፣ ኢሳያስ ግን ሲጠየፋቸው ኑሯል። 
 
ይህ ነው አባይ ፀሀዬ ማለት? ብዬ ራሴን ጠየቅሁ። አዎ! ኢሳያስ ፊት ነሳን ብሎ የሚያለቅስ? ሀፍረት፣ ውርደት የሚባል የማያውቅ ፍጡር? እስቲ ወደ አማርኛ ቃል በቃል የተመለሰውን የአባይ ፀሃዬ ልቅሶ አንብቡትና ፍረዱ! እነዚህ የግፍ ጌቶች እና የውርደት ጠርዞች 27 አመት ገዙን ማለትምኮ እኛኑ መልሶ ያሳፍራል።
                        =    =    =    =    =
“ህወሃት ረስቶታል፣ ኢህአዴግም ረስቶታል፣ ምናለ ፕረዚደንት ኢሳያስም ቢረሱት!” –
አባይ ፀሃዬ
ገና ህወሃት ሲፈጠር፣ የኤርትራ ጥያቄ ታሪኩን አጥንቶ፣ ፖለቲካውን ተንትኖ ተገቢ ፍትሃዊ ጥያቄ በሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ መንገድ መፈታት ያለበት ጥያቄ፣ በህዝበ ውሳኔ መፈታት የሚገባው ጥያቄ ብሎ ደግፎ ነው የተነሳው።
ህወሃት ከኤርትራ ድርጅቶች ጋር ከተቃቃረም በኋላ፣ የኤርትራን ጥያቄ ክዶ አያውቅም። ምን ክዶ አያውቅም ብቻ። በጽናት ቁሞ ታግሎለታል። ኤርትራ መሬት ላይ ሂዶ፣ ከኤርትራውያን ታጋዮች ጋር ከባድ መስዋእትነት ከፍሏል። አብሮ ተዋግቶ አብሮ ተቀብሯል። ይህ የኤርትራ ህዝብ ያውቀዋል፣ የኤርትራ ታጋዮችም ያውቁታል።
የኤርትራ ታጋዮችም በትግራይ መሬት ከህወሃት ጋር አብረው ተዋግተዋል፣ አብረው ተቀብረዋል። እንደዛ ብለን የመጣን ነን። እንደዛ ብለን ለድል በቅተናል።
ኤርትራ መሬት ላይ ሁነህ የደርግ መንግስት ውድቀት አይከሰትም ነበር።
ህወሃት/ኢህአዴግ በሚያደርገው ትግል ብቻም ደርግ በዛ በወደቀበት ጊዜም ቀድሞ ባልወደቀ ነበር። የሁለታችን ድምር ነው ደርግን የጣለው። የኤርትራ ጥያቄም ሊፈታ፣ ኢትዮጵያም ሰላም ዲሞክራሲ ሊመጣ የቻለው።
ስለዚህ ህወሃትና የትግራይ ህዝብ ለኤርትራ ህዝብ እና ትግል ባለውለታዎች እንጂ ባለ ዕዳዎች አይደሉም።
አቶ ኃይለማርያም ጠቅላይ ምኒስትር እያለ፣ የህወሃት ሰዎችም እዛው ጥናት ላይ ነበሩ፣ እነሱም የገፉበት ሀሳብ ነው። ዶ/ር አብይ ከመጣ በኋላ ፀደቀና ተቀላጠፈ እንጂ፣ ከሱ በፊት የተጀመረ ጉዳይ ነው። ህወሃት እዛ ጥናት ላይ በመሳተፍ እንዲሁም የመፍትሄ ሀሳብ በማቅረብ ትልቅ ሚና ተጫውቷል። ይህ ግን አይታወቅም።
ቀደም ብለን ማድረግ ይቻል ነበር፣ መተግበርም ነበረት የሚል ሀሳብ ተገቢ ነው። ለማድረግም ፍላጎቱና ዝግጅቱ ነበር። ግን በውስጣችን ችግር ስለነበር፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ሁከት ስለነበር፣ ኢህአዴግ ጋር ብዙ ብልሽቶች ስለነበሩ፣ ለኤርትራው ጉዳይ ትኩረትና መቀላጠፍ አልተሰጠም። ትልቁ በቂ ምክንያት የሚመስለኝ እሱ ነው። እንጂ ህወሃት ስላልፈለገ አይደለም።
እ…… ይህ አሁን የመጣው [ከኤርትራ ጋር ያለው ወዳጅነት] ደግሞ፣ ሁላችንም በጋራ ያመጣነው፣ ህወሃትም የነበረበት የኢህአዴግ ውሳኔ ነው። ሁለተኛ፣ ተግባራዊ ከሆነም በኋላ፣ ድንበሩ ይከፈት! ዛላምበሳ፣ ራማ፣ በባድመ እና በሁመራ ብሎ ደጋግሞ አብዝቶ የጠየቀ ህወሃት ነው። የትግራይ ክልላዊ አስተዳደር ነው። ሰላም ስለሚፈልግ ነው።
የትግራይ ህዝብም ከወንድሞቻችን ጋር አገናኙን፣ ምን ማለት ነው እኛን አልፎ [ኢሳያስ] ወደ አዲስ አበባ መሄድ? ምን ማለት ነው [ምፅዋ ዘግቶ] አሰብ ወደብ ብቻ መክፈት እያለ ጠይቋል። ለምን ቢባል ሰላም ስለሚፈልግ ነው፣ ወንድማማችነት ስለሚፈልግ ነው። ያቺ የድሯችን ጓደኝነት እንዲመለስ ስለሚፈልግ ነው። እንደሱም እየሆነች ነው፣ ሞልታ ባትሆንም።
ከፊሉ በር ተከፍቷል። ህዝብም ይገናኝበታል። ከፊሉ አልተከፈተም፣ ህዝብም አልተገናኘም። ለምን የባድመና የሁመራ [የኤርትራ በሮች] ኢሳያስ ስላልከፈታቸው።
ስለዚህ የኢትዮ-ኤርትራ ሰላም ቀደም ብለን ማምጣት ተገቢም ነበር፤ መደረገም ነበረበት ግን ኢህአዴግም በውስጡ ችግር ስለነበረበት፣ ህወሃትም በውስጡ ችግር ስለነበረበት ነው ሌላም አይደለም፣ ሰላም ካለመፈለግ አይደለም።
አሁን መምጣቱ ፈልገነው ነው የመጣው። ገፍተነው ነው የመጣው፣ እንዲተገበር ስለፈለግን ነው የተተገበረው። ሙሉውን ለመተግበር ግን ችግር አለ። አንድ – ትግራይን ትተህ፣ ህወሃትና የትግራይ አስተዳደራዊ ክልል ትተህ፣ ከአዲስ አበባ ጋር ብቻ፣ ከጎንደር ባህር ዳር ብቻ መሆን ነበረበት ወይ ያ ግንኙነት?
ኢሳያስ ከጎንደርና ከባህርዳር ጋር ይገናኝ። ጥሩ። ከአዋሳ፣ ድሬ ዳዋ፣ አዳማ ጋርም ይገናኝ። ደስ ይለናል። ከአዲስ አበባ ጋርም ይኑር። እሺ። የኛ ጥያቄ፣ የህወሃት ጥያቄ፣ የትግራይ ክልላዊ አስተዳደር ጥያቄ ግን ከኛም ጋርም ግንኙነት ያድርግ ነው።
ለምንድነው እኛን ዘለው እየሄዱ ያሉት፣ ለምን እኛን ያገላሉ? የትግራይ ህዝብ አይደለም እንዴ በደም ከኤርትራ ህዝብ ጋር የተሳሰረው?ትግራይ አይደለም እንዴ ከኤርትራ ጋር  ሰፊና ረዥም ድንብር የሚጋራው?
ሁለቱ ጎረቤት ህዝቦች [ትግራይ እና ኤርትራ] ሰላም ካልፈጠሩ፣ እንዴት ነው ዘለው ከኢትዮጵያ ጋር ሰላም የሚፈጠረው እየተባለ ነው። ይህ ሰላምን መቃወም አይደለም።
የኤርትራ ህዝብኮ በኛ ላይ ቅሬታ የለውም። ይኸው እያየነውኮነው፣ ድንበር ጥሶ መጥቷል። የኛም ህዝብ ጥሶ ሄዷል። ተደበላልቋል። የነሱና የኛ ወታደሮች ትጥቃቸውን ጥለው አብረው ጨፍረዋል፣ አብረው በልተዋል፣ ተቃቅፈዋል። ችግሩ ያለው መሪዎች ጋር ነው።
ስለዚህ አሁንም ያልተከፈቱ የሁመራና የባድመ በሮች ይከፈቱ። የምጽዋ ወደብም  አገልግሎት መስጠት ይጀመር። ህጋዊና ሥርአት ይያዝ። በድሮ ጊዜ አንኑር። ያለፈ አልፏል፣ እንርሳው። የትግራይ ህዝብ ረስቶታል። ህወሃት ረስቶታል። ኢህአዴግ ረስቶታል። ምናለ ፕረዚደንት ኢሳያስም ቢረሱት? እንደድሮ ወንድማማቾች እንሁን።
እንደዛ አብረን ስንዋጋ፣ ‘ወይን’ ‘ወይን’ እያሉ የኤርትራ ታጋዮች የህወሃት ታጋዮችን ሲወዱና ሲያደንቁ፣ የህወሃት ታጋዮች የኤርትራ ታጋዮች እስክስታ “ተጎምፀጽ” ሲሉ፣ ምናለ ወደዛ ብንመለስ! እንደዛ የኤርትራ ህዝብ ድንበር ጥሶ እዚህ መቶ ድብልቅልቅ እንዳለው፣ የኢትዮጵያ ህዝብም አስመራ ሂዶ እንደተደባለቀው፣ እኛ መሪዎችም እንደባለቅ እንጂ! ይኸው ከጎንደር፣ ባህር ዳር፣ አዲስ አበባ ጋር ድብልቅልቅ እያሉ ናቸው። ከመቀሌ፣ አክሱምና አድዋም ይደባለቁ እንጂ። ወንድም ህዝብ እኮ ነው፣ ምን በደላቸው? ይደበላለቁ እንጂ ከአዲግራት ሽሬና ሁመራም ጋር።”
ከመይነበብ ለቅሶ ጋር
Filed in: Amharic