>
5:13 pm - Sunday April 18, 4438

ትግራይ ብትገነጠል... (አበበ ቶላ ፈይሳ)

ትግራይ ብትገነጠል…
አበበ ቶላ ፈይሳ
ህውሃት በብቸኝነት እንደልቡ የሚፈነጭባት ትግራይ ልገንጠል ብላ ብትል ማንም ይዞ የሚያስቀራት ያለ አይመስለኝም… ሌሎች አካባቢዎች አንዱ ፓርቲ ሲያብድ ሌላው ፓርቲ ዱኣ እያደረገ እና ፀበል እየረጨ ከእብደቱ እንዲያገግም ያደርገዋል። ትግራይ ግን ምስኪን ናት ያለው ህውሃት ነው… ህውሃት ተሰለፊ ሲላት ትሰለፋለች ተሰየፊ ሲላት ትሰየፋለች… ህውሃት በዚህ አያያዙ ህዝቡ ከኢትዮጵያ እንዲነጠል ሊሰራ ይችላል… ቢሰራ ሊሳካለት ይችላል። የማይሳካለት በሰላም መኖሩ ነው…
አንድ… ከኢትዮጵያ ጋር ያልተወራረደ ብዙ ሂሳብ አለ… ለምሳሌ ወልቃይት ራያ እና ሎሎችም ቦታዎች እኛ “ኢትዮጵያ እስከሆነ ድረስ ማንስ ቢያስተዳድረው” ብለን የተውነው ብዙ ቦታ አለን… ትግራይ ልገንጠል ብትል ሙልጭ አድርገን ፈትሸን ነው የምንሸኛት እና ምን ይዛ እንደምትገነጠል ራሱ እግዜር ይወቅላት…
ሁለት… ከኤርትራ ጋር ሰላም የወረደው በዶክተር አብይ የተነሳ ነው እንጂ ትግራይ እና ኤርትራ በብዙ ነገር ፈፅሞ የማይታረቁ ሃገሮች ነው የሚሆኑት…
ሶስት… ትግራይ ሃገር ሆና ከሁላችን ጋ ሰላም ብትሆን እንኳ ራስ በራስ እየተጣሉ አስታርቁን የሚሉ ህዝቦች ነው የሚሆኑት። ከወደ አዲግራት ያለው ትግሬ እና ከወደ መቀሌ ያለው ትግሬ አንድ አድርጎ ያኖረው ኢትዮጵያዊነት ነው እንጂ እብሮ የሚኖር አይነት አይደለም… ይሄንን ለማረሃገጥ የአዲግራቱ ወልዋሎ እና መቀሌ ከነማ ኳስ ሲጫወቱ ተመልከትልኝ…
(በነገራችን ላይ ይቺኛዋ ነገር ለሁሉም አካባቢዎች ትሰራለች፤ አማራ አንድ ነኝ ብሎ ቢያስብ እና ቢናገር ከውጪ ለሚያየው አንድ ይመስላል እንጂ ጠጋ ስትል ጎንደሬ ጎጃሜ እያለ ሁሉም ራሱን አንደኛ ማድረግ ሲባትት ታየዋለህ። ኦሮሞውም ከላይ ስታየው፤ ኦሮሚያ በሚል አስተሳሰብ የተሳሰረ ይመስላል እንጂ ወለጋ፤ አርሲ… ሸዋ፤ ቦረና እያለ ሁሉም አንደኛ ለመሆን እርስ በርስ ሲተናነቅ ታየዋለህ!) ኢትዮጵያዊነት አንድ ካላደረገን ሁላችንም ብንሆን ተነጣጥለን ጸንተን የምንቆም ከመሰለን ተሳስተናል።
እና ትግራይ ብትገነጠል ሰው ትሆናለች ብሎ ማሰብ ይከብደኛል! 
ለትግራይ አክቲቪስቶች የምመክረው ሰከን ብለው መንግስታቸው ሰከን እንዲል እንዲመክሩት ህዝቡንም በስሜት ከመጋለብ ገታ እንዲል ቢያደርጉት ነው!
Filed in: Amharic