>

ሀገር ሲዘርፍ የኖረ የፍርድ ቀን ሲመጣ ሀገር ሊያፈርስ ይነሳል!  (ስዩም ተሾመ)

ሀገር ሲዘርፍ የኖረ የፍርድ ቀን ሲመጣ ሀገር ሊያፈርስ ይነሳል! 

 
ስዩም መስፍን
በእርግጥ ብዙዎቻችን ባለፉት አመታት ከፍተኛ ዘረፋና ሌብነት ሲፈፅሙ የነበሩት ሰዎች ከፍተኛ የህወሓት አመራሮች እና ጄኔራሎች ይመስሉናል። በዚህ የወንጀል ተግባር የተሰማሩት አመራሩ ብቻ ሳይሆን ብዛት ያላቸው የህወሓት አባልና ደጋፊ የሆኑ የትግራይ ተወላጆች ናቸው። በዛሬው ዕለት በተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ተወልደው ሱዳን የሚቀላውጡት፣ በተግባር የማያውቁትን ሕገ-መንግስት ይከበር የሚሉት፣ እንዲሁም ከዘረፏት ሀገር ክብርና ውዳሴ የሚሹት እነዚህ ሌቦች ናቸው።
ባሳለፍነው ሳምንት በአፋር ክልል “አብዓላ” በትምባል 2000 ሰዎች በሚኖሩባት ከተማ 55 ኢንተርናሽናል ሆቴሎች ለመገንባት በሚል ሰበብ ብረታ ብረትና ሌሎች የግንባታ ዕቃዎች ከቀረጥ ነፃ ወደ ሀገር ውስጥ ካስገቡ በኃላ አንድም ሆቴል አለመገንባታቸውን የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ አዳነች አቤቤ መግለፃቸው ይታወሳል። በዚህ መልኩ ባለ አመስት ኮኮብ ሆቴል ለመገንባት የሚያስፈልጉትን የግንባታ ዕቃዎች ከቀረጥ ነፃ ወደ ሀገር ካስገቡ በኋላ ያስገቡትን ዕቃዎች በህገወጥ መንገድ በመሸጥ በሀገርና ህዝብ ላይ ዘረፋ ሲፈፅሙ የነበሩት እና ከእነሱ ጋር የጥቅም ትስስር ያላቸው ሰዎች የዛሬውን የተቃውሞ ሰልፍ በማስተባበርና በመምራት ረገድ ግንባር ቀደሙን ድርሻ እንደተወጡ ጥርጥር የለኝም።
ከውስጥ አዋቂዎቸ በደረሰኝ የሰነድ ማስረጃ መሰረት ከላይ በተጠቀሰው የዘረፋ ተግባር የተሰማሩት ሰዎች በሙሉ የትግራይ ተወላጆች ናቸው። ከታች ያለው በአፋር ክልል የአብዓላ ወረዳ የኢንቨስትመንት ፍቃድ በማውጣት የግንባታ ዕቃዎችን ከቀረጥ ነፃ በማስገባት የህገወጥ ንግድ ሲያከናውኑ የነበሩ ባለሃብቶች/ድርጅቶች ስም ዝርዝር ነው።
በዝርዝሩ ውስጥ የተጠቀሱት 40 ሰዎች በሙሉ የትግራይ ክልል ተወለጆች ናቸው። ከእነዚህ ውስጥ 32አቱ የኢንቨስትመንት ፍቃድ ያላቸው ሲሆን 19 ደግሞ “TIN Number” አላቸው። ስለዚህ 21 ሰዎች ያለ “TIN Number” እንዲሁም 8 ሰዎች ያለ ኢንቨስትመንት ፍቃድ፣ 3 ሰዎች ደግሞ TIN Number ሆነ የኢንቨስትመንት ፍቃድ ሳይኖራቸው በአብዓላ ወረዳ ኢንተርናሽናል ሆቴል እንገነባለን በሚል ከቀረጥ ነፃ ብረታ ብረትና የግንባታ ዕቃዎች ከቀረጥ ነፃ እያስገቡ ሲነግዱ የነበሩ ሰዎች ናቸው። ዛሬ በመቀሌ የተቃውሞ ሰልፍ ያካሄዱት እንዲህ ያሉ ሀገር ሲዘርፉ የነበሩና ከእነሱ ጋር የጥቅም ትስስር የነበራቸው ሰዎች ናቸው። በእርግጥ ሀገር ሲዘርፉ የነበሩ ሌቦች ፍትህና ተጠያቂነት ሲመጣ ሀገር ለማፍረስ ይሞክራሉ። ይህንንም በዛሬው ዕለት በተግባር አረጋግጠዋል።
Filed in: Amharic