>

ቀድሞ የተሸነፈው የኢትጵያ ጦር ሰራዊት!!! ክፍል ፬ (ሻለቃ ላቀው መንግስቴ)

ቀድሞ የተሸነፈው የኢትጵያ ጦር ሰራዊት!!!
ከሻለቃ ላቀው መንግስቴ
 ክፍል ፬
 
ትንቢተኛዋ መነኩሲት
የደብረ ብርሀን አሥተዳዳሪ የሆኑት አቶ ጌታቸው ከቤተሠብ ራቅ ብለን ሐገርን ለወያኔ አሣልፎ ላለመሥጠት በነበረ ትንንቅ በአሉን እንደ ክርሥትና እምነት ተከታዮች የማክበር እድሉን ላጣን ወታደሮች ያመጡልንን አገልግል በየሣህኑ ተደርጎ እንደ ወታደራዊ ቅደም ተከተል ሢታደል ለእማሆይ እህተ ማሪያም ቅድሚያ ተሠጠ፡፡
‘አምቦ ውሀና ለሥላሣም የነበረ ይመሥለኛል፡፡ገበታው ከአዛዣችን ጋር፡የኮሩ ድርጅት መኮንን ኮ/ግርማ ተካ፡አሥተዳደር መኮንኑ ሌ/ኮ ዘርይሁን ፈረደ፡አዲሥ የነበሩት የኮሩ ፖለቲካ ሀላፊ ሻለቃ ተፈሪ መኮንን ፡የዘመቻ አሥተባባሪ በሁዋላ ለወያኔ እጁን ሠጥቶ ፊቱን በጠላትነት ወደ እኛ ያዞረ/ይቅርታ ሥሙን ዘንግቼ ሥለሆነ ነው/እኔ የዚህ ገድል አቅራቢ ሌሎችም ነበሩ፡፡
መመገብ ጀምረን አልፎ አለፎ ጀነራል በእድሜ የገፉትን መነኩሤ በእዚህ ሠላም በታጣበት ጊዜ ወዴት እየሄዱ ነው እማሆይ ሢሏቸው እሡን ፈጣሪዬንና እናቱን አምኜ ወደ ደብረሊባኖሥ ገዳም እየሄድኩ ነው፡፡
እኔማ ምንአለብኝ ለእናንተ ለልጆቼ እፀልያለሁ እንጂ እኔማ ዛሬሥ ወደ እሡ ቢወሥደኝ ምን ይከፋኛል፡ብለው በለበሡት ቢጫ የተነከረ፡ከጋቢ መለሥ ያለ ኩታ ጫፍ አይኖቻቸውን ጠረጉ፡፡እድሜያቸው ከ70 በላይ መሆኑ በጀ እንጂ ወያኔ መረጃ ለማግኘት ሢል፡እብድ አሥመሥሎ፡ቄሥ፡አካለ ሥንኩል ብቻ በተለያየ መልክ ሠላዮቹን ያሠማራል፡፡
እኝህ ግን አለም በቃኝ ብለው ለነፍሣቸው አድረው ወደ ፅድቅቦታ የሚያመሩ የእድሜ ባለፀጋ ነበሩ፡፡ ያ በከፍተኛ የመድፍና የመትረየሦች ተኩሥ ሥትናጥ የነበረችው ጣርማ በር ፀጥ ረጭ ብላ ወደ ሠላማዊ ሁኔታ ግርም ይላል፡፡መነኩሤዋ ያገኙዋትን እህል ውሀ ቀማምሠው ሊመርቁን ተነሡ፡፡
የሚገባውን የእናትነት ምርቃት ከሠጡን በሁዋላ ልጆቼ ድካማችሁ ሁሉ ዋጋ የለውም ፈጣሪ ፊቱን አዙሮባችሁዋል ፡ራሣችሁን ጠብቁ ልጆቼ ፡፡በህይወታችሁ የሚመጣ ምንም ነገርየለም፡፡ወደ ጀነራል ዞሩና እርሥዎ እዚች አገር አይኖሩም ባህር ማዶ ኑሮዎትን ያደርጋሉ ፡፡ወደ ሻለቃ ተፈሪ ዞር አሉና አንተ ቢመሽብህ እንኳን ውጪ እንዳታድር ፡ለማደር የተዘጋጀልህን ቦታ በፍፁም አትተው ካሉ በሁዋላ እኔን አንተ የተወሠነ እሥር ይኖርብሀል በተረፈ ልጆች ወልደህ ትኖራለህ ፡፡አሉንና መርቀውን መንገዳቸውን ቀጠሉ፡፡
ከሁሉም የሚገርመው ጥር 1983ሻለቃ ተፈሪ መኮንነ ሻለቃ ንጉሤ ብሩክ ፡ሻለቃ ሢሣይ ከደብረ ብርሀን ሢቢል የአሥተዳደሩ ሠራተኞች ጋር አጣየ አካባቢ በጦሩና በሕዝቡ መካከል የተፈጠረ አለመግባባት ለመፍታት በኮሚቴ ተዋቅረው ሥራቸውን ከጨረሡ በሁዋላ ወደየቦታቸው መመለሥ ሢገባቸው ሸዋ ሮቢት ከተማ ሢዝናኑ ያመሻሉ፡፡አንድ ቡና ቤት ከጓዳ አዘግተው እየተዝናኑ እያለ አንድ መ/አለቃ ክላሽ ይዞ ከገባ በሁዋላ አውቶማቲክ ተኩሦ ተፈሪና ንጉሤ ብሩክ ወዲያው ህይወታቸው ሢያልፍ ሢሣይ ወንበር ሥር ገብቶ ህይወቱን አትርፏል፡፡ሬሣቸውን በብዙ ትግል እንደ ቁሥለኛ አዲሥ አባ ልኬ ዮሤፍ ቤ/ከ እንዲቀበሩ ሆኗል፡፡
የመነኩሤዋ ትንቢት እውነት ሆነጀነራል ጥላሁን ሁኔታዎች ከተበላሹ በሁዋላ በሥተመጨረሻ አሠብ ተመድበው ሥለነበር ወደ ጂቡቲ ከወጡ በሁዋላ ዛሬ አሜሪካ ውሥጥ ይኖራሉ፡፡እኔም የተወሠኑ እሥሮች ደሤ አዲሥ አበባ ከገጠሙኝ ውጭ ዛሬ እንዳሉትም ልጆች አፍርቼ አሁን ያለሁበት ሁኔታ ላይ እገኛለሁ፡፡፡፡፡ጠብቁኝ
( ወደ ሠላማዊ ሁኔታዋ መመለሡ ተብሎ ይነበብ )
Filed in: Amharic