>

አዲስ አበቤነት እየተፈተነ ነው (ብርሀኑ ተክለያሬድ)

አዲስ አበቤነት እየተፈተነ ነው
ብርሀኑ ተክለያሬድ
አንዳንዶች በአዲስ አበባ ላይ ም/ከንቲባው  የሰራቸውን ስህተቶችን በጠቆምን ቁጥር “ታከለ የለውጡ አካል ነው አታደናቅፉት”አይነት አስተያየቶች ይሰጡናል የለውጥ አካል ማለት በስም ሳይሆን በተግባር የሚገለፅ ሆኖ ሳለ ታከለን መቃወም ሿሚዎቹን የለውጥ አካላት መቃወም ነው ሊሉን ይፈልጋሉ (አረመኔውና አንገት ደፊው ያሬድ ዘሪሁን በለውጡ መሪዎች ፖሊስ ኮሚሽነር ተደርጎ ተሾሞ ያልነበረ ይመስል) በእርግጥም ታከለ ኡማ አዲስ አበባንና አዲስ አበቤነትን ፈተና ውስጥ ከቷቸዋል  ለዚያውም በግዙፋን አይን ያወጡ ድፍረቶች
  እውነቱን እንነጋር “የአዲስ አበባ አርሶ አደሮች” ማለት ምን ማለት ነው?የትስ ነው ያሉት?አዲስ አበባን ለማልማት ሲባል የአዲስ አበባ የኮንዶሚኒየም ህንፃዎች የኦሮሚያን ወሰን አልፈው ገብተዋል እየተባለ አገር ይያዝ በሚባልበት ጊዜ የገበሬዎቹ የእርሻ መሬት የት ነው? ምናልባት ጓሮው ችግኝ የሚያፈላ ሁሉ አርሶ አደር ሊባል ይችል ይሆን? እውነቱን እንነጋገር አዲስ አበባ አዳራሽ የሚሞላ ቀርቶ ደርዘን የሚሞላ አርሶ አደር የላትም!!!
ልዩ መታወቂያ ማለትስ ምንድነው? አንድ ሰው መታወቂያ የሚይዝበት ምክንያት ቋሚ አድራሻ ያለው መሆኑን ለማሳወቅ ነው ቋሚ አድራሻ የሌለው ሰው አልያም ከቋሚ አድራሻው መሸኛ ያላመጣ ሰው መታወቂያ ሊሰጠው አይችልም ማንነቱ በምን ታውቆ? በየትኛው የክትትል ማእቀፍ ውስጥስ ሊገባ? ደግሞስ አንዱን ህገወጥ ብሎ ቤቱን አፍርሶና ቤት አልባ አድርጎ ቤተክርስቲያን አፀድ ውስጥ እንዲወድቅ ካደረጉ በኋላ ለሌላው ደሞ የህጋዊነት መታወቂያ መስጠት ምን ይሉት “የዋህነት” ነው?
ለውጡን በመደገፍም ሆነ ሰላምና ማረጋጋትን በማምጣት የአዲስ አበባ ህዝብ ቀዳሚው ተሰላፊ ነው በለውጥ ስም ለሚደረግ ህገወጥነትና የማንነት ዝርፊያ ግን ህጋዊ ሽፋን ሊሰጥ አይችልም የዘረኞችን ሀጢአት ለመሸፈን እርሱ ጦላይ ሄዶ በወባ ሲያልቅ በነበረ የአዲስ አበባ ወጣት ስም የሚደረግ ደባ መቆም አለበት መነጋገር መጀመር አለብን “ለውጡን አትንኩብን”የምትሉ ቲፎዞዎች አትመፃደቁ ለውጥ የሚዳብረው በመነጋገርና በመተቻቸት  እንጂ በጭፍን ድጋፍ አይደለም ማጨብጨብ አለመደብንም እናም ስህተቶች አይተን ዝም አንልም!!!
Filed in: Amharic