>

ፍትህ ለአክሱም ሙስሊሞች - በካባና በትክሊል የሚሸፈን በደል አይኖርም!!!  (ከድር መሀመድ)

ፍትህ ለአክሱም ሙስሊሞች – በካባና በትክሊል የሚሸፈን በደል አይኖርም!!!  
ከድር መሀመድ
 እነ ደብረጽዮን “ገድለናታል ቀብረናታል” ባሏት ቤተክርስቲያን ሲጨንቃቸው ካባዋን ተክሊሏን ከመቅደስ እያስወጡ ለሰው እይታ ማጌጫ ለውስጣቸው ግን የክፉ ቀን መሸሸጊያ እያደረጓት በነውራቸው ከማጌጣቸውም በላይ በክርስቲያኑና በሙስሊሙ ህብረተሰብ መሀከል የጠብ ግድግዳውንም እየገነቡ ነው!!
በአክሱም የሚኖሩ ሙስሊሞች ከዚህ በፊት መስኪድ ሰርተው እምነታቸውን እንዳያካሂዱ ተከልክለው ነበር። መቀበሪያ ቦታ ፍለጋ ረጅም ኪሎሜትር እንደሚጓዙ ሰምተን ነበር። ዛሬ ደግሞ በንግስ ሰበብ በጀማ ሆነው እንዳይሰግዱ መከልከላቸውን ሰማን።
አንዱን በመግፋት አንዱን የማቀፍ የሴራ ፖለቲካን የእድሜያቸው ማራዘሚያ ያደረጉት እነ ደብረጽዮን “…. ገድለናታል ቀብረናታል” ባሏት ቤተክርስቲያን ሲጨንቃቸው ካባዋን ተክሊሏን ከመቅደስ እያስወጡ ለሰው እይታ ማጌጫ ለውስጣቸው ግን የክፉ ቀን መሸሸጊያ እያደረጓት በነውራቸው ከማጌጣቸውም በላይ በክርስቲያኑና በሙስሊሙ ህብረተሰብ መሀከል የጠብ ግድግዳውንም እየገነቡ ነው።
የአክሱም ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች አላህ በሰጣቸው ምድር ላይ የራሳቸው መስኪድ፣ የራሳቸው መቃብር ስፍራ፣ የራሳቸውን መንፈሳዊ ትምህርት ቤት የመስራትና ሃይማኖታቸውን በነፃነት  ማምለክ ሰማያዊም ምድራዊም መብት አላቸው!
 በአክሱም የሚኖረው ሙስሊምም ሆነ ክርስቲያን ወገኔ ነው።  ራሷ አክሱምም የሐገሬ አንዷ ክፍል ነች! አንዱ በነፃነት የሚያካሂደውን ሃይማኖታዊ ስርአት ለሌላው መከልከል ከነውርም በላይ ነው፤ ለአንድ ኢትዮጵያዊ መቃብር ስፍራ ከልክለህ የምታካሂደው ሃይማኖታዊ ተግባርስ ደመናን ይሻገራል ወይ? የአክሱም ሙስሊሞች ጥያቄ በአስቸኳይ ሊደመጥና መልስ ሊሰጥበት ይገባል! ፍትህ ለአክሱም ሙስሊሞች!!!
Filed in: Amharic