>

መቀሌ የራሷን ሌባ ለመደበቅ ሰልፍ እንደወጣችው ሁሉ የሌላውን ሌባ ልትደብቅ ሌላ ሰልፍ ትጠራ ይሆን ? (ኢትኦጲስ ዜና)

መቀሌ የራሷን ሌባ ለመደበቅ ሰልፍ እንደወጣችው ሁሉ የሌላውን ሌባ ልትደብቅ ሌላ ሰልፍ ትጠራ ይሆን ?
ኢትኦጲስ እለታዊ ዜና (ዩ ቲዩብ) 
* ቢጫዋ በረከት ስምዖን እና ታደሰ ካሳን ለማምጣት መቀሌ መሄዷ የማይቀር ሆኗል !!
* ጥረት ካሉት 20 ኩባንያዎች በሰባቱ በየዓመቱ 100 ሚሊዮን ብር ይከስራል ፤ 2 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ደግሞ የባንክ ዕዳ አለበት !!
“በቀድሞው ኢህዴን (በአሁኑ አዴፓ ) በዘላቂ በጎ አድራጎት ወይም ኢንዶውመንት ቁመና ይዞ የተመሠረተው ጥረት ኮርፖሬት 20 ኩባንያዎች አሉት:: ከእነዚህ ውስጥ ከሰባቱ በየዓመቱ 100 ሚሊየን ብር አካባቢ ይከስራል፡፡
የጥረት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር አምላኩ አስረስ እንደሚሉት በቀደመው አመራር ጥረት 11 ቢሊዮን ብር ጥሬ ሀብት አለው ተብሎ ሪፖርት የተደረገውም ስህተት ነው፡፡ የጥረት በአሁኑ ወቅት ያለው ጥሬ ሀብት 5 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር ሲሆን 2 ነጥብ 7 ቢሊዮን አካባቢ የባንክ ዕዳ አለበት:: ከዚህም በተጨማሪ ካሉት 20 ኩባንያዎች በሰባት ኩባንያዎች በየዓመቱ 100 ሚሊዮን ብር ይከስራል፡፡
ጥረት በትራንስፖርት ዘርፉ የተሠማሩ 500 ተሽከርካሪዎች አሉት እየተባለ ሪፖርት ሲደረግ ቢቆይም በተግባር ያሉት ተሸከርካሪዎች ግን 348 ናቸው፡፡ ከዚህ ውስጥ 48ቱ ብቻ ዓመት እስከ ዓመት ይሠራሉ፤ ሌሎቹ የተበላሹ ናቸው፡፡ ጥረት ከኪሳራው ለመውጣት አዲስ ፍኖተ ካርታ እያዘጋጀ ሲሆን፤ የመዋቅር እና የአመራር ለውጥም እያደረገ እንደሆነ ዶክተር አምላኩ አስረድተዋል፡፡ አጥፊዎችም በሕግ የሚጠየቁ ይሆናል ብለዋል ሲል ያስነበበው አብመድ ነው፡፡”
Filed in: Amharic