>

በትግራይ ክልል የተደረገው ሰልፍ ለሰሚውም ሆነ ለሚመለከተው ግራ አጋቢ ነው!!! (ቬሮኒካ መላኩ)

በትግራይ ክልል የተደረገው ሰልፍ ለሰሚውም ሆነ ለሚመለከተው ግራ አጋቢ ነው!!!
ቬሮኒካ መላኩ
 
 << ሰልፉ ሌብነት ስራ ስለሆነ ልጆቻችን ነፃ ይውጡልን ፣ ሌብነት ይፈቀድልን ” የሚል በመሆኑ ግራ የሚያጋባው ኢትዮጵያውያንን ብቻ ሳይሆን  አለምንም ጭምር ነው። ለነገሩ ” እስካልተያዝክ ድረስ ሌብነት ጥሩ ስራ ነው ” በማለት ለመጀመሪያ ጊዜ  በአገሪቱ ፓርላማ የተናገረው የቀድሞው ጠ/ሚራቸው መለስ ዜናዊ ነው!!
 
በ130 አመታት የኢትዮጵያ  ታሪክ ” ሌብነት ይፈቀድ ” በማለት ሰላማዊ ሰልፍ  የመውጣት ታሪክ ይሄ ሁለተኛው ነው።
እውቁ የታሪክ ባለሙያ ተክለፃድቅ መኩሪያ መዝግበው እንዳለፉት
አፄ ቴዎድሮስ ወደ ስልጣን እንደመጣ የመጀመሪያ አዋጁ << ሁሉም በሙያው ይሰማራ ፣ ገበሬም ወደ እርሻህ ግባ ፣ ነጋዴም ንግድህን አጧጡፍ ፣ የቀረውም ሰው ወደየስራው አንድመለስ ታውጇል ” በማለት አዋጅ ያስነግራሉ።
በዚህ ጊዜ ተከዜን ተሻግረው ደብረታቦር  ከተማ የመጡ ጥቂት ሰዎች  ወደ አፄ ቴዎድሮስ በቀጥታ ሰልፍ አደግድገው በመግባት << ጃንሆይ ሰውን ሁሉ በየስራህ ግባ ካሉት እኛም ከሌብነትና ከሽፍትነት በቀር ሌላ ስራ የለንምና ይህንኑ ይፍቀዱልን> > ሲሉ አመለከቷቸው።
አፄ ቴዎድሮስም ለሰልፈኞቹ << እኔም ለራሴ ታማኝ ዘበኛ ለመቅጠር የእናንተ አይነት ልማድ ያለው ጠንካራ ሰው ስለምፈልግ ሌላ ባእድ ሳትጨምሩ የእናንተ አይነት ስራ የሚሰሩትን ሰብስባችሁ ይዛችሁ  ኑ ” በማለት በቀጠሮ ያሰናብቷቸዋል። በቀጠሮውም ቀን ሌቦቹ ተሰብስበው ሲመጡ አፄ ቴዎድሮስ አንድ እጃቸው ላይ ፈረዱባቸው ከዛን ጊዜ በኋላ ሌብነት ለብዙ አመታት በኢትዮጵያ ጠፍቶ በሰላም ህዝቡ መኖር ጀመረ ።>> በማለት እውቁ ምሁር ተክለፃድቅ መኩሪያ “አፄ ቴዎድሮስ ” በሚለው መፅሃፉ ገፅ 193 ላይ ፅፏል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ እጅግ ሩህሩህ በመሆኑ እንጅ መርከብና አውሮፕላን የሰረቀ ሌባ እንደ ቴዎድሮስ መረር ያለ ቅጣት ቢቀጣ ኖሮ የዛሬውን የድፍረት “ሌባ ይለቀቅልኝ የሚል ሰልፍ ባልተመለከትን ነበር።
ሙሰኛ በየትም አገር  ቅጣቱ ከባድ ነው ። በቻይና እንኳን መርከብ ይቅርና የህዝብ የሆነን መቶ ብር የሰረቀ በስቅላት አንጠልጥለው ይቀጡታል ። በአረብ አገሮች ሌባ እጁ ይቆረጣል ፣በአውሮፓና አሜሪካ በስልጣን ላይ ሆኖ የህዝብ ንብረት የሰረቀ እስከ እድሜ ልክ እስራት ይጠብቀዋል። ከአፍሪካ ውጭ ሌብነት በየትኛውም አገር ፀያፍ ነው። ጆርጅ በርናንድሾው ” There is no little pregnancy ” ( ትንሽ የሚባል እርግዝና  የለም)  እንዳለው ትንሽና ትልቅ የሚባል ሌባ የለም ። ሁሉም ሌባ ነው ። ሌባ ከአገር እንድጠፋ ከተፈለገ በሰላማዊ ሰልፍ ሌብነትን ማበረታታት ሳይሆን ተገቢውን ቅጣት መስጠት ያስፈልጋል።
Filed in: Amharic