>
5:13 pm - Thursday April 19, 8666

ደግሞ እንደሱ አሉን? “አፍሪካይቱ ቻይና!”- (የዛሬው ስብሰባ) ደረጄ ደስታ

ደግሞ እንደሱ አሉን? “አፍሪካይቱ ቻይና!”- (የዛሬው ስብሰባ)
ደረጄ ደስታ
አሁን ዛሬ 60 የሚደርሱ የቻይና ታላላቅ ኩባንያ ኃላፊዎችን ጨምሮ 100 የሚደርሱ የቻይና ቢዝነስ የልዑካን ቡድን አዲስ አበባ ገብተዋል። በቻይና ኢትዮ- ቻይና የቢዝነስ ፎረም በአዲስ አበባው ሔልተን እየተካሄደ ነው። ቻይናውያኑ በ2018 ኢትዮጵያ ላይ ያላቸው ኢንቨስትመንት $4 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል።
ቻይና $424 ሚልዮን ዶላር ዕቃ ሸጠንላት (ልከን) የ$5.46 ቢሊዮን  ዶላር ሸቀጥ እንገዛታለን (እናስመጣለን)። ክፍተቱን ማሰብ ነው። ቢሆንም በአንዳንዶቹ “አፍሪካዊቱ ቻይና” መባል የጀመረችው ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር በፍቅር እና በእዳ የወደቀች መስላለች። ሸቀጦቻቸውን ለኢትዮጵያ በመሸጥ ከቻይና ቀጥለው አሜሪካ በ1.5 ቢሊዮን ዶላርና ህንድ በ1.3 ቢሊዮን ዶላር ይከተላሉ። ቻይና ቢያንስ በሶስት ቢሊዮን ዶላር ትበልጣቸዋለች። ልዑካኑ ለኢንደስትሪ ተከልለው የተሰናዱ መሬቶችን (ዞን) ይጎበኛሉ ተብሏል። ከዚያ ሁሉ ኩባንያ መቸም ጥቂቶችን አናጣም። በነገራችን ላይ ልጆቻችንም ቻይናኛውን እያቀላጠፉት ነው። ተማሪ ቤት የሄዱም ብዙ ናቸው። አሁን አራት ሺህ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ሳይንስ እና ቴክኖሎጂን ጨምሮ በተለያዩ የትምህርት መስኮች በቻይና በመማር ላይ ይገኛሉ። አንዳንድ የአገራችን ዩኒቨርስቲዎችም ቻይንኛን እንደ አንድ ቋንቋ ማስተማር ጀምረዋል። ወደ ኃይስኩልም ወረድ ይበል የሚል ነገር ነበር ልበል- አይ ቻይና!
Filed in: Amharic