>
5:13 pm - Tuesday April 18, 8158

ኦሮሞውና አማራው  "እሳትና ጭድ " ነው  አላልኩም! የሕወሓቱ ጌታቸው ረዳ 

ኦሮሞውና አማራው  “እሳትና ጭድ ” ነው  አላልኩም! የሕወሓቱ ጌታቸው ረዳ 
እንዳለ ኪዳኔ
ሕወሓት ለዘረኞቹ መመሪያ የአይዲዮሎጅ አባት ነው፡፡    ጭራቁን  የፅልመት የሰቆቃ መልአከ ሞት  ጌታቸው አሰፋ      ” ሀገር ወዳድ  ” ሲል ያንቆለጳጵሰዋል፡፡ የትኛዋን ሀገር ለማለት ተፈልጎ ይሆን?
  ሕወሓታውያን የሚናገሩት በአንድ ልሳን ነው፡፡ ይህም መለሲስዝም  ነው፡፡  ሽምጥጥ አድርጎ መዋሸት፡፡  ሙያ ነው፡፡
ሁሉንም ከቴዎድሮስ አድኃኖም በረከት ሥምኦን ወዘተ ጌታቸው ረዳ ይቅርና የቀበሌ የሕወሓት ካድሬ ሽምጥጥ አድርገው ሲዋሹ ስታይ  እንዴት ነው?  ብለህ ስታስብ በስልጠና ወይስ የሆነ ነገር አድሮባቸው ነው ብለህ ታስባለህ?
ስልቻ ቀልቀሎ….ቀልቀሎ ስልቻ!
”አማራና ኦሮሞ እሳትና ጭድ ናቸው” አላልኩም አሉ አቶ ጌታቸው ከቤቲ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፡፡ እኔ ያልኩት አሉ……..አንደኛው ወገን የፌዴራል ስርዓቱ ሀገራችንን ያፈርሳል፣ ያጠፋናል ይላል አሉ….
ልብ በሉ በጀርመንኛ አማራውን ማለታቸው ነው፡፡ ሌላው አካል አይሆንም እገነጠላለሁ የሚል ነው-ይህም በፈረንሳይኛ ኦሮሞውን ማለታቸው ነው፡፡ እነዚህ አመለካከቶች በኛ ድክመት ምክንያት አንድ ሆነው ተሰለፉ አሉ፡፡ አሁንም አመለካከቱን ነው ሲሉ ሊሞግቱ ሞከሩ፡፡ ምን ማለት ነው?……..አመለካከት ካለሰው እንዲሁ በምናብ የሚኖር ነገር ነው እንዴ!……..ፈኒ የቃላት ጨዋታ ነው፡፡  ዞሮ ዞሮ አማራና ኦሮሞ አንድ እንዲሆኑ ክፍተት የፈጠርነው እኛ ነን፡፡ ሁለት የማይስማሙ አመለካከቶች እንዲስማሙ እድል የፈጠርነው እኛ ነን ማለት አማራና ኦሮሞ አንድ እንዲሆኑ መንገዱን ጠረግን ከማለት ውጪ ሌላ ትርጉም ሊኖረው አይችልም፡፡ እናትህ ማናት ሲባል አንድ ሰው አባቴ በቀለ ነው እንደማለት ነው፡፡ እውነት ነው አባቱ በቀለ ሊሆን ይችላል፡፡ መልሱ ግን ትክክል አይደለም፡፡ የቃላት ጨዋታ ይኼ ነው፡፡ስልቻ ቀልቀሎ ቀልቀሎ ስልቻ !
Filed in: Amharic