>

ዛሬም አልተግባባንም ማለት ነው? (ቹቹ አለባቸው)

ዛሬም አልተግባባንም ማለት ነው?
ቹቹ አለባቸው
በዛሬው  ምሽት የ VOA የአማርኛ ክፍል ፕሮግራም ላይ፤ እኔ፤ዶ/ር ሲሳይ፤አቶ ምግባሩና አቶ ቻላቸው( ከባ/ዳር ዩኒቭርስቲ መሰለኝ) የተባልን ግከሰቦች፤ ወልቃይትና ራያን በተመለከተ ቃለ መጠይቅ ተደርጎልን ማብራሪያ ስንሰጥ ሰማሁ፡፡ እኔ በበኩሌ ይህንን ቃለ መጠይቅ ያደረግኩ መሆኔን ባስተውስም ፤ቆየት ያለ ግን መሰለኝ( ምን አልባት በክረምቱ)፡፡ የሌሎቹን አላወቅኩም፡፡ ቁም ነገሩ  ዛሬ ከሰማኋቸው አንዳንድ ነገሮች ተነስቸ፤አሁንም በደንብ ያልተግባብንባቸው ነገሮች እንዳሉ ስለገመትኩ ፡፡ ይሄውም፡-
1.ከአቶ ምግባሩ፤ አነጋገር እንደተረዳሁት ፤ ብአዴን/ አዴፓ የወልቃይትና ራያን ጉዳይ እንደገና ይታይ ወደሚል አቋም የመጣው፤ ክለላው የተካሄደው ፤አሁን በስራ ላይ ያለው ህገ መንግስት ከመጽደቁ በፊት፤በ1984 ዓ.ም በመሆኑ፤ እንዲሁም  በወቅቱ ክለላው ሲካሄድ የየአካባቢዎቹ ህዝቦች በወቅቱ በተገቢው ሳይወያዩ የተካሄደ ክለላ ስለሆነ ነው የሚል መንፈስ ያለው ነው፡፡ ቀጥለውም አቶ ምግባሩ፤በአሁኑ ወቅት ችግሩ እንዲፈታ የምንታገለው፤ አሁን ባለው ህገ መንግስት መሰረት የተቀመጡትን የአከላለል መስፈርቶች በመከተል ነው፡- ማለትም  በህዝብ አሰፋፈር፤ ቋንቋን፤ ማንነትናፍቃድ ላይ በመመስረት( አንቀጽ 46 )፡፡
እዚህ ላይ አዴፓ፤ሁለት ነገሮችን ሳይስት አልቀረህም፤እንደገና ማስተዋል አለበት፡-
1. 1). ወልቃይትም ይሁን ራያ ወደ አማራ ይመለሱ የምንልበት ዋነኛው እና ቁልፉ ምክንያታችን፤  አካባዎቹ ወደ ትግራይ በተካለሉበት ወቅት፤ ህዝቡ  በጉዳዩ ላይ በተገቢው አልመከረም በሚል ብቻ  አይደለም፡፡ ዋናው ነጥባችን አካባቢዎቹ በወረራ እንደተያዙ ቀርተዋል ነው፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን፤ በ1984 ዓ.ም ጎንደር ከተማ ላይ ከፍ/ፍ/ቤቱ  ውስጥ ፤ስለ ክለላ ውይይት በተካሄደበት ወቅት፤ልዩነት አንስተው የታገሉ የኢህዴን ካድሬዎች፤በክለላው ካልተሰማሙ በህወሀት የጦር መሪዎች ሂዎታቸውን እንደሚያጡ ጭምር ተስፈራርተዋል ፤ይሄ እንዲሳካም በወቅቱ የነበሩ የኢህዴን  ከፍተኛ አመራሮች ቁልፍ ሚና ተጫውተዋል ብለን ካሁን ቀደም መረጃ ሰጥተናል፡፡  አዴፓ ይህን መረጃ መጠቀም ሲገባው አግድሞ ይሄዳል፡፡ አሁን አዴፓ ቀልብህን ወደነዚህ ነጥቦች መልስ፡፡
1. 2). ሌላው አዴፓ መጠንቀቅ ያለበት፤ችግሩ አሁን ባለው ህገ መንግስት መሰረት፤ አራቱን መስፈርቶች መሰረት አድርጎ እንዲፈታ እንታገላለን የሚለው ነው፡፡ ይህ ፍጹም ስህተትና የማያስኬድ አባባል ነው፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ፤ክለላው ህገ-መንግስቱ ከመጽደቁ በፊት የተከወነ ስለሆነ፤በዚህ አንገዛም ይላል፤ ቆየት ብሎ ደግሞ፤ ችግሩ በህገ መንግስቱ መሰረት እንዲፈታ እንታገላለን ይላል፡፡ እንዴት ያለ ነገር ነው? እዚህ ላይ መደበላለቅ ያለ መሰለኝ፡፡ መሆን ያለበት፤ይህ ህገ መንግስት ሲጸድቅ አማራ ወኪል ስላልነበረው፤እንዲሁም አነዚህ መስፈርቶችም  የወጡት አማራ ባልተሳተፈበት ህገ-መንግስት ስለሆነ፤ ነገሩ አይመለከተንም ነው፡፡ አዴፓ የነወልቃይትን ችግር የማስፈታው አሁን ባለው ህገ-መንግስት መሰረት ነው ካለ፤ እራሱ ጉድ ሆኖ እኛንም ጉድ እንዳያደርገን ፈራሁ፡፡ ስለሆነም፤አዴፓ፤ባክህን ቢያንስ የሰጠነህን መረጃ ተጠቀምበት፤ እሽ! እኔንና መሰሎቸንስ አትመናቸው፤ በቃ መሳፍንት በውቀቱን ከእስራኤል አገር አስመጥተህ ዝርዝር መረጃ ውሰድ፡፡ መረጃ ሳያጥር ይህንን ያክል መደናገር ለምን?
2.ሌላውና  ቢስተካከል ጥሩ ነው ብየ ያሰብኩት አቶ ቻላቸው ካቀረቧቸው ጥሩ-ጥሩ ሃሳቦች መካከል በአንዷ ላይ ብቻ ነው፡፡ አቶ ቻላቸው ችግሩ አሁን ባለው ህገ-መንግስት መሰረት  እንደማይፈታ ያስቀመጡት ነገር ተገቢ ነው፡፡ ነገር ግን ታሪክ ማጣቀስ የገቡበት ነገር ቢቆይ ጥሩ ነው ባይ ነኝ፡፡ ምክንያቱም አሁን ያለንበት ጊዜ ስለ ወልቃይትና እራያ ታሪክ ጠቅሰን የምንሟገትበት ወቅት አይደለም፡፡ ታሪክ ጠቅሰን ምንከራከረው አገር አማን ከሆነና፤ በ ጉልበት የተወሰዱት  መሬቶቻችንና ህዝባችን በሰላማዊ መንገድ ከተመለሱ በኋላ ነው፡፡ ከዚህ ውጭ ካሁን በኋላ፤ታሪክን እያጣቀስን ጊዜ ባናጠፋ ጥሩ ነው እላሁ፡፡ ይሄን የማነሳው ነገሩን ለመቃወም ሳይሆን፤ቅድሚያ የሚሰጠው አይደለም ለማለት ነው፤ ታሪክ ጠቅሰን የምንከራከረው፤ሁሉም ነገር ወደነበረበት ከተመለሰ በኋላ ነው ለማለት ነው፡፡
ያች የትግራይ ኮሙኒኬሽን ኋላፊ ናት የተባለችው ሴት ደግሞ ምንድን ነው ያለችው?  አለ የሚባለውን የማንነት ጥያቄ በሩቁ ሲወራ እንሰማለን እንጅ፤ለኛ (ለትግራይ መንግስት) በህጋዊ መንገድ የቀረበ ህጋዊ ጥያቄ የለም ስትል ሰማኋት ልበል? ለነገሩ ዶ/ር ደ/ፂወንም ተመሳሳይ ነገር ሲናገር ሰምቸዋለሁ፡፡ ወይ መከራችን፤ ምን የታመመ ሰፈር ነው እናንተየ!
አንች የኮሙኒኬሽን ኋላፊዋ እህቴ፤ ስለ እውነት የወልቃይት ማንት ኮሚቴ መቀሌ ድረስ መጥቶ ለህወሀት ጽ/ቤት፤ለክልላችሁ ም/ቤትና ለፕ/ጽቤት  ያስገባው  ህጋዊ አቤቱታ የለም ? ይሄንን  አቤቱታ ስለመቀበላችሁስ  በፊርማችሁ አላረጋገጣችሁም? እንዴው ዘመዶቸ፤  ከክህደት ፐፖለቲካ  ብትላቀቁ ?
ለሁሉም እነዚህ ሰነዶች በጃችን ናቸውና፤ክህደት ባትናገሩ ጥሩ ነው ለማለት ነው፡፡
Filed in: Amharic