ሀብታሙ አያሌው
ከእለተ አርብ ጀምሮ አዲስ አበባ በመግባት ቅዳሜና እሁድ ሚስጥራዊ ስብሰባ ሲያደርጉ የነበሩት የአፋር ክልል አመራሮች የኢህአዴግ ተወካይ ባለበት በግምገማ ሲጠዛጡዙ ቆይተዋል።
ተገማጋሚዎቹ ከዶክተር አብይ አመራር የተሰጠውን አቅጣጫ በተገቢ መንገድ ከተወጡ የአመራር ለውጥ በማድረግ ( በቅርቡ የኢፌድሪ መከላከያ ሚኒስትር ) ሆነው የተሾሙትን ወ/ሮ አይሻን ሊቀመንበር አድርገው በመሰየም ያጠናቅቃሉ ተብሎ ይገመታል። ከውስጥ ምንጭ ያገኘሁት መረጃ እንደሚያሳየው የወ/ሮ አይሻ ባለቤት አቶ አወል ኦርቢስ የትራንስፖርትና መገናኛ ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው በመሾም ወደ ሚኒስትሯ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ቢሮ ተልከዋል።
በጥቅሉ ግን የአፋር ክልል ሁኔታ እና ሚስጥራዊ ስብሰባው ከምንም በላይ መቀሌ ላይ ከፍተኛ ድንጋጤና ንዴት ፈጥሯል። ለውጡን እና የእስር ዘመቻውን እንደግፋለን የሚል መግለጫ ካወጡ ሳምንት ሳይሞላ ሌላ ተቃራኒ መግለጫ ለማውጣት ካስገደዱት ገፊ ምክንያቶች አንዱ ይሄው ጉዳይ ሳይሆን እንዳልቀረ የውስጥ ምንጮች ይገልፃሉ
ሰበር ዜና 2
“ለውጡን እንሰብራለን!” የሚል መረጃም ከወደ ሰሜን ደርሶናል!!!
የትግራይ ክልል መንግስት በይፋ ተቃውሞውን እና አቋሙን ግልፅ በማድረግ ለውጡን ለመቀልበስ
እንደሚነሳ ማሰታወቁን የትግራይ ማስሚዲያ ዘግቧል። “የኢትዮጵያ መንግስት በሙስናና የሰብኣዊ መብቶች
ጥሰት ስም የጀመረው እንቅስቃሴ ኣቅጣጫውን ስቶ የትግራይ ህዝብ ለማንበርከክ የሚደረግ ጥረት ስለሆነ አንቀበለውም። ከዚህ በተጨማሪም የውጭ ጣልቃ ገብነት አለው ብለን እናምናለን። “