>

የደብረጽዮን ፖለቲካ!!! (ሚኪ አምሀራ)

የደብረጽዮን ፖለቲካ!!!
ሚኪ አምሀራ

* ሰሞኑን ጌታቸዉ ደብረጽዮንን አጠፋሃለሁ ብሎታል፡፡ አሁን የሚያወሩት በሶስተኛ ወገን እንጅ ፊት ለፊት አይን ለአይን አይተያዩም፡፡ ሆኖም ግን ደብረጽዮን እየተሳካለት ይመስላል!
ህወሃትን የበላይ ሁኖ ለመቆጣጠር በባለፉት 3 አመታት ብዙ ቡድን ሞክሯል፡፡ የመጀመሪያዉ ቡድን የእነ አባይ ወልዱ ቡድን ነበር፡፡ከዛም በእነ አቦይ ስብሃት እና ጌታቸዉ አሰፋ ቡድን ተሸነፈ፡፡ በባለፉት ሁለት አመታት ደግሞ በደህንነቱ እና በወታደሩ በኩል ተከፋፍለዉ ሲነታረኩ ነበር፡፡ በደህንነቱ በኩል ጌታቸዉ አስፋ ሲሆን በወታደሩ በኩል የሳሞራ የኑስ ቡድን (እነ አዜብን የያዘ) ሁነዉ ሲጠዛጠዙ ከርመዋል፡፡ እኒህ ሁለት ቡድኖች በስላዮቻቸዉ አማካኝነት ሁሉ ጦርነት በሚመስል ሁኔታ እርስ በእርስ ይገዳደሉ ነበር፡፡ብዙም ገሃድ ያለወጡ በሁለቱ ቡድኖች መካከል ግድያወች ሁሉ ነበሩ፡፡በነገራችን ላይ ይህ የህወሃት የዉስጥ ፍትጊያ ለራሱ መዳከም አንዱ ምክንያት ነበር::
ያም ሆነ ይህ ግን ከአባይ ወልዱ በኋላ ጌታቸዉ አሰፋ በህወሃት ላይ የመሪነት ሚና ነበረዉ፡፡ እሱ ካለዉ ዉጭ የሚሰራ ስራ አልነበረም፡፡ እስከ ባለፈዉ ሳምንት ድረስ ለስሙ ደብረጺዎን ይሁን እንጂ የህወሃት መሪ የነበረዉ እና ዘዋሪዉ ጌታቸዉ አሰፋ ነበር፡፡ ደብረጺዎን በዛ መንደር እንደ ደካማ እና ተናግሮ የማያሳምን አይነት ፖለቲከኛ አድርገዉ ነዉ የሚያዩት፡፡ ለዚህም ነዉ የትግራይ ኢሊቶች በሙሉ የጌታቸዉ አሰፋ ደጋፊወች የሆኑት፡፡ ጌታቸዉ አሰፋ ያለ ደብረጺዎን ፈቃድ ነዉ እራሱን የትግራይ ጸጥታ አማካሪ አድርጎ የሾመ፡፡
አሁን ላይ ደብረጽዮን ህወሃትን ለመቆጣጠር ሲል እንኳን ጌታቸዉን ሚስቱን አሳልፎ ለመስጠት ተዘጋጅቷል፡፡ ደብረጽዮን ከዶ/ር አብይ ባገኘዉ ድጋፍ መሰረት አሁን ላይ ሁሉንም እሱን የሚቃወሙትን አሳልፎ በመስጠት ህወሃትን እስከዉዲያኛዉ ለመቆጣጠር አስቧል፡፡
ስለዚህም የዶ/ር ደብረጽዮን ፈቃደኛ መሆን የመደመር አለመደመር ጉዳይ ሳይሆን እራሱን የማዳን እና ያለማዳን ጉዳይ ነዉ፡፡ ጌታቸዉ አሰፋ ደብረጺዎንን ከህወሃት ገለል ለማድረግ ፈልጎም ነበር፡፡ ለምሳሌ የደብረጺዎን የኢሜል ኮሚኒኬሽን የክንፈ አብርሃን ገንዝብ ከእንግሊዝ ባንክ እንዴት ሊያወጣዉ እንደነበር እና መሰል መረጃቸው ሲወጡ የነበረዉ በእነ ጌታቸዉ አሰፋ ቡድን ነበር፡፡
ሰሞኑን ጌታቸዉ ደብረጽዮንን አጠፋሃለዉ ብሎታል፡፡ አሁን የሚያወሩት በሶስተኛ ወገን እንጅ ፊት ለፊት አይን ለአይን አይተያዩም፡፡ ሆኖም ግን ደብረጽዮን እየተሳካለት ይመስላል፡፡ የህወሃት አክቲቪስቶችም ግራ ተጋብተዋል፡፡ ጌታቸዉ እንደተሸነፈ ገብቷለቸዋል፡፡ በመሆኑም ደብረጺወንን ደፈር ብለዉ ሊያወግዙት አልፈለጉም፡፡ ምክንያቱም ቀጣይ የሚገናኙት ከእርሱ ጋር ነዉና፡፡
እናንተስ እንዴት ናችሁ፡፡ ሰፊዉ የአማራዉ ህዝብ እንዴት ነዉ? ይሄን ሁለት ቀን ለአንዳንድ ወዳጆቻችን ጊዜ ለመስጠት ያህል ሳይበሩን ቀነስ አደድርጌዉ ነበር፡፡
Filed in: Amharic