>

‘ደሞዜ አነስተኛ ስለሆነ ፍርድ ቤቱ ጠበቃ እንዲያቆምልኝ እጠይቃለሁ!!!’’ (ሜጄር ጀነራል ክንፈ ለዕለቱ ዳኛ ከተናገሩት)

‘’ደሞዜ አነስተኛ ስለሆነ ፍርድ ቤቱ ጠበቃ እንዲያቆምልኝ እጠይቃለሁ!!!’’ 
ሜጄር ጀነራል ክንፈ ለዕለቱ ዳኛ ከተናገሩት
እየሩሳሌም ተስፋው
 
ሜጄር ጀነራል ክንፈ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 10ኛ የወንጀል ችሎት ቀርበዋል።
ዛሬ በነ ሜጄር ጄነራል ክንፈ ፖሊስ የጠየቀዉ የ14 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ላይ ጄነራሉ ሀሳብ እንዲሠጡ ሲጠየቁ “…ጠበቃ ለማቆም አቅም የሌለኝ የጡረታ ደሞዜም 4,000 መሆኑን በእግዚያብሄር ስም ምያለሁ” በማለት መንግስት ተከላካይ ጠበቃ እንዲያቆምላቸው ጠይቀዋል።
ሜጀር ጀነራሉን ጨምሮ ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡት የተጠርጣሪዎች ቁጥር 8  ሲሆን፤ ከእነዚህም መካከል ስድስቱ በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ ናቸው።
ሁለቱ ደግሞ በሰብዓዊ መብት ጥሰት ተጠርጥረው ፍርድ ቤት የቀረቡ ናቸው።
ከሙስና ወንጀል ጋር በተያያዘ ዛሬ ፍርድ ቤት ከቀረቡት መካከል የቀድሞዋ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ ፍጹም የሺጥላ እና የሜጄር ጀነራል ክንፈ ዳኘው ወንድም ኢሳያስ ዳኘው ይገኙበታል። በተመሳሳይ መልኩ አቶ ኢሳያስ ዳኘውም ገንዘብ ከፍለው ጠበቃ ማቆም እንደማይችሉ በመጥቀስ፤ መንግሥት ጠበቃ እንዲያቆምላቸው ጠይቀዋል።
Filed in: Amharic