>

እውን ይህ ሁሉ ግፍና በደል ይፈጸም የነበረው እዝህች አገር ውስጥ ነበረን!?!...

እውን ይህ ሁሉ ግፍና በደል ይፈጸም የነበረው እዝህች አገር ውስጥ ነበረን!?!…
ስዩም ተሾመ
እንደ አቃቤ ህጉ ገለጻ:-
ሴቶች ይደፈራሉ 
– ወንዶች ግብረ-ሰዶም ይፈፀምባቸዋል 
– ወንዶች ብልታቸዉ ላይ ሀይላንድ ይንጠለጠልባቸዋል
– አይናቸውን ታስረው በጫካ ይጣላሉ ሌላም ሌላም…
 
ላለፉት አመታት በሀገራችን እና ህዝባችን ላይ የተጫነው የጭቆና ቀንበር ለመጣል ጥረት ያደረጋችሁ፣ “የዜጎች ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ይከበር!” በሚል መርህ ዘረኛ የሆነ አምባገነናዊ ስርዓትን የተጋፈጣችሁ የነፃነት ታጋዮች፣… ለዜጎች መብት ስትሉ ሰብዓዊ ክብራችሁ የተነካ፣ ለሞራል ቀውስ የተዳረጋችሁ፣ የሰውነት አካላችሁ የጎደለ፣ በግርፋት የተተለተለ፣ የዘር-ፍሬ አብራካችሁ የመከነ፣… በእስራትና ስደት ፍዳና መከራ የደረሰባችሁ፣ የጭቆና ቀንበርን ለመጣል እንደ ሻማ የቀለጣችሁ፣… ለሀገራችሁ ፍቅር፣ ለራሳችሁ ክብር ያላችሁ የነፃነት ታጋዮች፣ የመብት አቀንቃኞች፣… እነሆ በኢትዮጵያ ፀሐይ ወጣ!!! የጨቋኞች ጭካኔ በይፋ ተነገረ፣ በክፋት የተሞላ እኩይ ምግባራቸው በግልፅ ተነገረ።
 ሰብዓዊ ክብራችንን የገፈፉ፣ የዜግነት መብታችንን የነፈጉን፣ በሀገራችን ላይ ሀገር-አልባ ያደረጉን የጨቋኝ ስርዓት ጠበቆች እና አገልጋዮች ፍርድ ቤት ሊቀርቡ ነው። ዜጎችን በግፍ ሲያስሩና ሲያሸብሩ የነበሩ ጨካኞች በችሎት ፊት ቀርበው ሊፈረድባቸው ነው። እንሆ እኛም ወግ ደርሶን ፍትህን በእውን ልናይ ነው። ይህ እውን እንዲሆን ላስቻለ የኢትዮጵያ አምላክ ክብርና ምስጋና ይገባዋል።
አዲስ አበባ ውስጥ 7 ግፍ የሚፈፀምባቸው ድብቅ እስር ቤቶች አሉ ይሉናል  – ጠ/ አቃቤ ሕጉ
       • « በአዲስ አበባ ዜጎች ከሰባት ወደማያንሱ ስውር ማሰቃያ ስፍራዎች ‘በአምቡላንስ እየተጓጓዙ!’ ኢ- ሰብአዊ ድርጊት ይፈጸምባቸው ነበር »
በእነዚህ እስር ቤቶች ዉስጥ
– ሴቶች ይደፈራሉ
– ወንዶች ግብረሰዶም ይፈፀምባቸዋል
– ወንዶች ብልታቸዉ ላይ ሀይላንድ ይንጠለጠልባቸዋል
– አይናቸውን ታስረው በጫካ ይጣላሉ
***
 ፖሊስ ጣቢያ፣ ማረሚያቤት እና ስውር እስር ቤቶች ውስጥ የነበሩ ተጠርጣሪዎችን በአሌክትሪክ ሾክ ማድረግ፣ ብልትን በፒንሳ መሳብ፣ ዛፍ ላይ ሰቅሎ ለረጅም ጊዜ ማቆየት፣ ጫካ ውስጥ እርቃንን ማሳደር፣ ጥፍር መንቀል፣ በብልት ላይ ውሃ ማንጠልጠል፣ አይናቸው ከታሰረ በኋላ ከከተማ አውጠቶ ጫካ ውስጥ መጣል፣ አልፎ አልፎ ከአውሬ ጋር በማሰር ማሰቃየት ሲደረግ ነበር
***
የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽንን በተመለከተ፦
ከ2004 እስከ 2010 ድረስ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን 37 ቢሊየን ብር የውጭ ግዢ ፈፅሟል።
እነዚህ ግዢዎች ዓለም አቀፍ ጨረታ ሳይፈፀምባቸው የተከናወኑ ናቸው። ግዢዎቹ በጥቅም በተሳሰሩ ግለሰቦችና ተቋማት መካከል የተከናወነ ነው።
የሀገር ውስጥ ግዢም በግልፅ ጨረታ መፈፀም ሲገባው እስካሁን በዚህ መልኩ የተፈፀመ የለም። ከኮርፖሬሽኑ አመራሮች ጋር የዝምድናና የጥቅም ትስስር ካላቸው ሰዎች በብዙ እጥፍ በተጋነነ ዋጋ ይገዛ ነበር። ከአንድ ድርጅት 21 ጊዜ፣ ከሌላው ደግሞ 15 ጊዜ ግጭ ተፈፅሟል። ከአንድ ድርጅት በአንድ ጊዜ ብቻ የ2015 ሚሊዮን ብር ግዢ ያለጨረታ ተፈፅሟል።
***
 ከተቋሙ ተልዕኮ ውጪ የተፈፀሙ ግዥዎችም አሉ። ከዚህም ውስጥ የመርከብ ግዢ ይገኝበታል። በማይመለከተውም ስራ ገብቶ ወደ ንግድ ስራ አስገብቷቸዋል፤
አንዱ አውሮፕላን የት እንደገባ አይታወቅም።
***
“የሰኔ 16 ቱ  የቦምብ ጥቃት የተቀናበረው በብሔራዊ መረጃና ደህንነት ቢሮው ሲሆን መመሪያው የተላለፈው በቀጥታ ከጌታቸው አሰፋ መሆኑ ታውቋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኦሮሞ ስለሆኑ በኦሮሞ ቢገደሉ ተብሎ ነው በሙከራው ኦሮሞዎች እንዲሳተፉ የተደረገው።”
***
በሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀል 36 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል
***
በአጠቃላይ እስካሁን በቁጥጥር ስር የዋሉ የሜቴክና ደህንነት አመራሮች ቁጥር 63 ሲሆን እስካሁንም ያልተያዙ በአገር ውስጥና ከአገር ውጭ የተደበቁ አሉ።
* ከሚቴክ ጋር በተያያዘ የታገዱና ምርመራ እየተደርገባቸው ያሉ ድርጀቶች ስም ዝርዝር
1,ተክለብርሃን አምባየ ኮንስትራክሽን
2,በርሄ ሀጎስ ህንጻ ተቋጭ
3,ሰንራይዝ ሪልስቴት
4.ዛምራ ኮንስትራክሽን
5,ጉላጉል ብርት አስመጭ
6.ፀጋ ትሬዲንግ
7,ተክላይና ቤተሰቡ ንግድ ስራ
8, ፍሊስት ስቶን ሆምስ
9,ሰንሻይን ኮንስትራክሽን
10,ማራቶን ሞተር ኢንጂነሪንግ
11.ገምሹ በየነ ኮንስትራክሽን
12,ፀሀይ ሪል ስቴት
13,ጉኡሽ ማእድን ላኪ
14,ገብርመድን አርያ አስመጪ
በጥቂቱ እነዚህ ናቸው!
በተጨማሪም እንደ አቃቢ ህጉ ሪፖርት:
የዛሬ ሦስት ዓመት የጎንደር ማረሚያ ቤት ተቃጥሎ ነበር። ማረሚያ ቤቱ እንዲቃጠል የተደረገው ሆን ተብሎ ነበር። በቃጠሎው መካከል ሊያመልጡ ነው ተብሎ የተገደሉ ሰዎች ነበሩ። ከእነዚህ ሰዎች መካከል በህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል የታሰረ የጎንደር ከተማ ልጅ ነበር። ቃጠሎው የተካሄደው ይሄን ልጅ በቃጠሎ ሰበብ ሊያመልጥ ነው ብሎ በመግደል ወንጀል ለመደበቅ ነበር።
 ይኼን ሴራ ከአገር ውስጥ ደህንነት ኃላፊው ጀምሮ እስከ ሰሜን ጎንደር የደህንነት ኃላፊ ድረስ ያሉ አሁን እየታሰሩ ያሉ ሰወች የተሳተፉበት ነበር።
የተደበቀው ወንጀል በርካታ ሠዎችን ወደ ሱዳን እና ሊቢያ እናሻግራችኋለን በማለት ከአፈኑ በኋላ እየገደሉ የሰውነት አካላቸውን ኩላሊት ወዘተ በመበለት መሸጥ ነበር።
በማረሚያ ቤት በእስር ያሉ ሰወች፣ በመንገድ ላይ ታፍነው የሚወሰዱ ሰወች፣ እብዶች፣ ለሰሊጥ ቆረጣ ከተለያየ የኢትዮጵያ ክፍል ወደ ሰሜን ጎንደር የሚጓዙ ሸቃዮች ሳይቀር እየታፈኑ እየተገደሉ አካላቸው እየተበለተ ይሸጥ ነበር። የዚህ ጥቅም ተካፋዮች ደግሞ በደህንነት መስሪያ ቤቱ ትናንት የተያዘው የሰሜን ጎነደር ኃላፊው አሸናፊ ተስፋን ጨምሮ እሰከ አገር ውስጥ ደህንነት ኃላፊው ያሬድ ዘሪሁን የተዘረጋ የአረሜዎች ሰንሰለት ነበር። በማረሚያ ቤቱ ውስጥ የተገደለው ወጣትም የእነሱ ተባባሪና የጥቅም ተጋሪ ስለነበር ወንጀል ለመደበቅ ነበር የተገደለው። በሟቹ የባንክ ሂሳብም ከፍተኛ ገንዘብ ተገኝቶ ነበር።
~  ( የአቃቤ ሕግ መግለጫ)
Filed in: Amharic