>

ለምን ይዋሻል እስክንድርንማ ቄሮ ነጻ አላወጣውም!!! (እሸቴ ካሳ)

ለምን ይዋሻል እስክንድርንማ ቄሮ ነጻ አላወጣውም!!!
እሸቴ ካሳ
*… የትኛውም ሰልፍ ላይ ‘ እስክንድር ይፈታ !’ ሲል የወጣ ቄሮ የለም። ቄሮም ለመብቱ ፣ እስክንድርም ለነጻነቱ ታግለዋል የኢትዮጵያ ህዝብ ድምር ትግል ነጻ አውጥቷቸዋል!
 
የኢትዮጲስን ቄሮ ተኮር ርዕሰ አንቀጽ መሰረት አድርጎ ውይይትም ውግዘትም ስንሰማ ውለናል። ከ 8 ጊዜያት በላይ በወያኔ ማጎሪያ ካምፕ ለመናገርና መጻፍ ነጻነት ሲታሰር ሲፈታ የኖረውን እስክንድር ‘ከእስር ያስፈታህን ቄሮ ኮነንክ’ የሚል አስቂኝ ክስና ዘለፋዎችም አንብበናል።
ትንሽ እንድናስታውስ ይፈቀድልን ! እስክንድር የቄሮን ካልኩሌተር ሰራነው እንዳሉት ሰዎች በምስኪኖች ህይወት ስልጣን ለመያዝ የሪሞት ኮንትሮል ፓለቲካ አላካሄደም። በፈቀደው ጊዜ አሜሪካ መሄድና መኖር እየቻለ እምቢኝ ያለ ወያኔን አፍንጫው ስር ሆኖ የሞገተ ትንታግ ነው።
ሌላም እናስታውስዎ የትኛውም ሰልፍ ላይ ‘ እስክንድር ይፈታ !’ ሲል የወጣ ቄሮ የለም። ቄሮም ለመብቱ ፣ እስክንድርም ለነጻነቱ ታግለዋል የኢትዮጵያ ህዝብ ድምር ትግል ነጻ አውጥቷቸዋል። ትግሉ የአንድ ስብስብ ብቸኛ ውጤት ነው ማለት አጉል እብሪት ብቻ ነው የሚሆነው።
እንጨምርልዎ ! እስክንድር ‘ የትግሬ ጠላት’ ተብሎ ነው ፍዳ ውን የበላው። ዛሬ ባለጊዜ ነን ባዮች በሀሳብ የተለያቸውን ሁሉ ‘ የኦሮሞ ህዝብ ጠላት ‘ እያሉ የመደፍጠጥ ፓለቲካ ውስጥ ገብተዋል። አያዋጣችሁም -ከእናንተ የተለየ ሀሳብ ያለው ሁሉ የኦሮሞ ጠላት አይደለም የህወሃትን መንገድ አትሂዱበት !!!
መፍትሄው አንድ ብቻ ነው። OMN አዲስአበባ ውስጥ ቢሮ ከፍቷል እስክንድር ቢሮ ሄዶ ቃለመጠይቅ ለማድረግ የደቂቃዎች መንገድ ነው። በሀሳብ ተሟገቱት ፣ የጥላቻ ፓለቲካና የመንጋ ስድብ የትም አያደርስም !!!
ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ይከበር !
እውን እስከንድርን ነፃ ያወጣው ቄሮ ነው?
ሳምሶን ሚሀይሎቪች
እስከንድርን ነፃ ያወጣው የኦሮሞው ቄሮ  የአማራው ፋኖ ከምንል የሁላችንም ጣምራ የትግል ውጤት ነው ብንለው የተሻለ ነው!!!
 
  እናስታውስ  ከሀምሌ 5/2008 በፊት የነበሩትን  10 ወራቶች  እጅን ብቻ በማጣመር  በየጊዜው የኦሮሞ ወጣቶች  ለሰልፍ ሲወጡ በአግዓዚ ጦር  በአለሞ ተኳሾች ደረትና ግንባራሳቸውን እየተመቱ ብዙዎቹ ይወድቁ ነበር ሆኖም ግን በአንድ የአግዓዚ ጦር ላይ ጥቃት የሰነዘረ ማንም አካል አልነበረም። ኦነግ የሚባል ነገር  ሥሙም የተረሳ ከነመኖሩ እናኳ  የሚያስተውስው  ባልነበረበት ወቅት ሀምሌ 5/2008  እብሪተኛው ህወሀት እንደልማዷ በኮ/ ሎ ደመቀ ዘውዴ ላይ አፈና ለማድረግ  በምመሞከሯ የተጫረው እሳት የጎንደር ሕዝብ ቁጣው ገንፍሎ በወጣበት ጊዜ ነበር “የኦሮሞው ደም ደሜ  ነው” ብሎ ሲነሳ እንዲሁ በባዶ እጅ አልነበረም።
 የዓግዚ ጥይት  ማብረጃ የተኩስ መለማመጃም አልነበረም ጎንደር  ሲወድቅ እየጣለ ነበር የትግራይን አፋኝ እስኳድን ሁሌ መግደል ብቻ ሳይሆን መሞትም እንዳለ ለማሳየት በመጡበት መንገድ በመሄድ በሚገባቸው ቋንቋ በማናገር ወደማይመሉሱበት ዓለም የሸኛቸው።
  ከዛች ዕለት ጀምሮ በኦሮሞ ወጣቶች ላይ ዓግአዚ አፈመዙ ከማዞሩ በፊት ደጋግሞ  ማሰበ ጀመረ። የሕወሓት አከርካሪ ተሰበረበት ጎማውም ተነፈሰበት ፍርሃት ዳግም በኢትዮጵያውያን ላይ ላትነግሥ ላንዴና ለመጨረሻ የተወገደችበት ቄሮ የሚለው ሥያሜው ገኖ የወጣውም ሕወሓታውያን የሚያዙት አግዓዚ የተሸማቀቀበት ወቅት ነበር  ያን ጊዜ እናስብ ቄሮም አይደለም የአማራ ፋኖም አይደለም
የሁሉም ትብብር  ብንለው የተሻለ ነው
Filed in: Amharic