>
5:13 pm - Wednesday April 20, 6574

"አዴፓ" በእውነት ወይም መሰሎ መኖር አጣብቂኝ (መንገሻ ዘውዱ ተፈራ)

“አዴፓ” በእውነት ወይም መሰሎ መኖር አጣብቂኝ
መንገሻ ዘውዱ ተፈራ 
“አዴፓ” በእውነት ወይም መሰሎ መኖር አጣብቂኝ ሆናችሁ በማይወክለን መልስ ይቁም ማቁሰላችሁ።
አዴፓ፦ እኛ አንኳ ድሮም ከፈጣሪ፣ አጥማቂ፣ አኗሪ የዕለት እንጀራ አባታችሁ ከህወሀት ለመለየት የማትችሉ ስለመሆናችሁ ጥርጣሬው ነበርን። እንዴው ግን ወር ባለሞላው በእራሳችሁ አንደበት በተነፈሳችሁት ድንገት ወደ ስጋዊና መንፈሳዊ ፈጣሪያችሁ አማራነታችሁ ተመልሳችሁ አንደሆን በሚል ትንሽ ተስፋ በመጨረሻ ሰላማዊ ሰልፍ አቋማችሁን ለማረጋገጥ ነበር።
ጠርጥር ይላሉ አባቶች ነግር አላምራቸው ሲል። ድሮም አንደጠረጠርነው አሁን ትላንተ ማታ የአዴፓ የአማራው መንግሥት ቃል አቀባይ የአማራ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ መብቱ በህገ መንግስቱ መሰረት አንዲከበርለት ጠየቅ አሉና። አንድ ነገር ግን ረሱ መልካም አስተዳደር? ጋዜጠኛው ጥያቄውን ቀጠለ። ሰውየውም ቀጠሉ አልፎ አለፎ አንዳንድ ቦታዎች በእርሳቸው አንደበት ከወጣው ቃል ጎረቤቶቻችን እኔ እንደተረዳሁት (ህወሀት) አለቆቻቸውና ጌቶቻቸው ጋር የሚያጋጭ መፈክርም ይዘው የወጡ ነበሩ። እነዚህ ደግሞ የአማራ ህዝብን አይወክሉም በቅርቡ አንደገና ???? አይነት መለስ ሲሰጡ ሰማን።
በእውነቱ ሲሆን የአዴፓን አስተሳሰብ ለውጠው ካልቻሉም እራሳቸውን በመለየት ያታግሉናል ብለን ትልቅ ቦታ ከምንሰጣቸው ግለሰብ እንደዚህ ያለ ከእውነት የራቀ መልዕክት ሲተላለፍ መስማት እጅግ ያሳዝናል ያማል። ለነገሩ ድሮስ ከአዴፓ “ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ” ምን ይጠበቃል። ለነገሩ አንዳንድ ሰዎች ሁልጊዜም የኃይል ሚዛኑን እያዩ አንዱ መጥቶ በጎተተው ጊዜ አንደሚጮኸው የቤ/ክርስቲያን ደወል ወዲያና ወዲህ ማለታቸው የሚደንቅ አይደልም። ለአንሱ ትልቁ ነገር “ሲጭኑት አህያ ሲጋልቡት ፈረስ” ሆኖ መኖረም መኖር ነው። ስህተቱ የእኛ በትክክለ ሳንረዳና ሳናውቅ የምንሰጠው የማይመጥን ዋጋ ነው።
የአማራ ህዝብ አኮ 27 ዓመት አሁንም እየታገለ የሚገኘው ህወሀቶች በእነሱ ተፅፎ ጎሳን መሰረት አድረገው በፈለፈሉአቸው ብአዴን ጋሻ ጃግሬነት ባላፀደቅነው ህገ መንግስት ልንገዛ አይገባም ነው። የአማራ ህዝብ ህገ መንግስቱን ያፀደቀውና የሚያከብረው ከሆነ ለምን ይህ ህይወትና ንብረት ዋጋ አስከፋይ ትግል አስፈለገ?
ከጥያቄዎቹ አንዱም በህግ መንግሥቱ ጥያቄየ ይመለስ የሚል የለበትም። አነ ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምት፣ ራያና፣ መተከል አኮ ከህግ መንግሥቱ መፅደቅ በፊት በወረራ የተወሰዱ መሬቶች ናቸው።
በመሰረቱ የአማራ ክልል መንግስት የአንድን  መንግስት መሰራታዊና ቀዳሚ ኃላፊነቶች ያውቃቸዋልን?
አንድ መንግሥት መንግስት ነኝ ለማለት በእኛ በኢትዮጵያ የአስተዳደር እርከን፤ የሚያስተዳደረውን ሐገር፣ ክልል፣ ዞን፣ ወረዳ፣ ቀበሌ፣አስተዳደር ወሰንና  በዚህ ወሰን ውስጥ የሚገኙ፦ ህዝቦችን፣ አንጡራ ሀብትና፣ ሉዐላዊነትን ደህንነት በማስጠበቅና በማረጋገጥ ከጎረቤት አስተዳደሮችና አገሮች ጋር በበታችነት ሳይሆን በአኩልነት በተመሰረተ በሰላማዊ ሰጠቶ የመቀበል መርህ ማስተዳደር ሲችል ነው።
ታዲያ የድሮው ብአዴን የአሁኑ አዴፓ እኮ በዚህ ሀገሮችና አስተዳደሮች ከሚመሰረቱበት መርህ ውጭ በአስተዳደሩ የሚገኙትን የወልቃይት፣ጠገዴ፣ጠለምት፣ራያና መተከልን ህዝብና አንጡራ ሀብት አስወርሮ ነው ያለው። አንደ ልዑላዊ የክልል መንግሥት በእራሱ የሚወስን ቢሆንማ ኖሮ ይህን ጉዳይ ኃላፊነት ወስዶ ቢቻል በጠሬጴዛ ዙሪያ በክብር ቁጭ ብሎ ባይቻል አነሱ በመጡበት መንገድ እራሱ ማስከበር ነበረበት። ነግር ግን የፈጠሩት አለቆቹ ህወሀቶች እይደለም በክብር በጠሬጴዛ ዙሪያ አስቀምጦ ማናገር በማሰቡ ብቻ አንበርክከው በአርጩሜ እንደሚገረፍ ህፃን በፍርሃት አማራን በማይወክለው ህገ መንግስት ስም. የወልቃይት የራያ አስመላሽ በሚል ኃላፊነት በጎደለው ለህዝቦች ትቶ ቁጭ ብሎ ሀገርን ባላሰወረረና ህዝብ ባላስጨረሰ ነበር።
በመሆኑም የድሮው ብአዴን የአሁኑ አዴፓ የአማራ ክልለ መንግሥት በዚህ አሰፋሪና አሳዛኝ  የሞራል ሰብራት ያለ አዳኝ ወጌሻ አጥቶ ታሞ የሚልፈሰፈስ ነው። ይህ እውነትና በግሃድ ያለ ሀቅ ሀሰት ነው ካለ ነገ ዛሬ ሳይል ይቅርታ በጠየቀውና በገባው ቃል መሰረት ይቅርታ የሰጠውን ትልቅና ሆደ ሰፊ አዳኝ ወጌሻ ህዝብ ሰምቶ ለአማራ ክልልና ህዝብ ተመጣጣኝ ዋጋ ይክፍል።
አለበለዚያ ግን አሁንም ሰው እየተሳደደ ሰው እየተገደለ ጊዜ የማይሰጠውን መሬት ላይ ያለውን ግሃድ ትቶ ከጌቶቹ ህወሀት መንግስት ጋር አየተነጋገርን ነው የሚለው እይናችሁን ጨፈኑ መልስ የሚወስደው እርቀት አጭር ነው።
ስለዚህ የአማራን ህዝብን አለወከልንህም የእራሳህን መንገድ ምረጥ በማለት ከምጥ መገላገል ይቻላል ቢያንስ አሰከዚያው ግን በእውነት ወይም መሰሎ መኖር አጣብቂኝ ሆናችሁ በማይወክለን መልስ ይቁም ማቁሰላችሁ።
 
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር
Filed in: Amharic