>

የማንቂያ ደውል!!! (ሀብታሙ አያሌው) 

የማንቂያ ደውል!!!
ሀብታሙ አያሌው 
ለውጥ ማለት ንቅለ ተከላ አይደለም።  በወንበዴ ጉሮሮውን ተሰንጎ ለሚጮህው ህዝብ ድረስለት ስትለው ጆሮ ዳባ የሚልህ የመከላከያ ኃይል የድርጅት ሰንደቅ አላማ ይዞ ሲነወልል እያየህ ለውጡ እንዳይደናቀፍ ዝም በል የምትል ይሄን ደጋግመህ እየው።
የለውጡን ሂደት ተገን አድርገው የፖለቲካ  አሻጥር የሚሰሩት  የብሔር ጠርዝ እረጋጮች የት እንደደረሱ ማወቅ ከፈለክ ይህው መለኪያውን እንካ ፎቶው ይነግርሃል።  ያለከልካይ በሚዲያ ቀን ከሌት ጥላቻቸውን ይሰብካሉ፤ በህቡ የሚያደራጇቸውን እያሰማሩ የክልል መንግስታትን አስር ሚሊዬን ገብር ወይም ህዝቡን በውሃ ጥም እንጨርሰዋለን እያሉ በግልፅ ለቆሙለት አላማ ይሰራሉ።
ለምን ስትል ለውጥ የናፈቀውን ህዝብ ተገን አድርገው የዶክተር አብይ እና የአቶ ለማን ምስል ፕሮፋይል አድርገው ይመጡልሃል። ሸፍጣቸውን ስታጋልጥ “የኦሮሞ ጥላቻ ነው” በሚል ታክቲካቸው ዝም ሊያሰኙህ ይጥራሉ።
እነዚህ አካላት የለውጥ አመራሩን  መከለያ አድርገው ቀላል በማይባሉ  የአመለካከታቸው ተሸካሚዎች በኩል በርካታ የፖለቲካ ስልጣንም እየቶቆጣጠሩ ነው።
የራሳቸውን ሲገነቡ የሌላውን ለማፍረስና ለማዳከመ በእኩል አቅም መስራታቸው ደግሞ የአካሔዳቸውን አደገኛነት የበለጠ ያሳይሃል።  በሚዲያቸው ቀን ከሌት ቅማንት አርጎባ እና አገው ሲሉ የሚውሉት ለምን እንደሆነ ካልገባህ ለፖለቲካው እሩቅ እንደሆንክ እመን። ከዚህ በኋላ የአይናፋርነት ትግል ፈፅሞ አዋጪ አይደለም። ካልተናገርክ አትደመጥም። የነሱ ድምፅ የጎላው እኛ ዝም ስላልን ነው።
አገሩን የሚወደ ኢትዬጵያዊ ሁሉ ሳሩን ብቻ ሳይሆን ገደሉንም ቢያይ መልካም ነው።
ለለውጥ የሰራነው ለውጥ ቀልባሽ አይደለንም የለውጡን ሂደት ወደፈለጉት አጣምመው የሚቀለብሱ ሃይሎች ሲገነግኑ ደግሞ ዝም አንልም።
Filed in: Amharic