አቻምየለህ ታምሩ
* አገራችን ከወይዘሮ ሣሕለ ወርቅ ዘውዴ በፊት ንግስተ-ነገስታት ዘውዲቱ ምኒልክ፣ ሕንደኬ፣ ማክዳና ዮዲት የሚባሉ ሴት ርዕሳነ ብሔራት ነበሯት!
የኢትዮጵያን እድሜ ከወያኔ የአገዛዝ ዘመን ጀምረው የሚቆጥሩ እንደ BBC News Amharic አይነት ጋዜጠኞች ወይዘሮ ሣሕለ ወርቅ ዘውዴን የመጀመሪያዋ ሴት የኢትዮጵያ ርዕሰ ብሔር እያደረጓቸው ይገኛሉ። ከዛሬ 98 ዓመታት በፊት ወይዘሮ ሣሕለ ወርቅ ዘውዴ ዛሬ በገቡበት የኢትዮጵያ ቤተ መንግሥት ውስጥ የኢትዮጵያ መሪ ሆነው የገቡ ሌላ ሴት ርዕሰ ብሔር ነበሩ። ስማቸው ወይዘሮ ዘውዲቱ ምኒልክ ይባላል!
* ወይዘሮ ሣሕለ ወርቅ ዘውዴን ርዕሰ ብሔር አድርጎ የሾመው ኦሮሞው ዐቢይ አሕመድ ነው።
* ወይዘሮ ዘውዲቱ ምኒልክንም ርዕሰ ብሔር አድርገው የሾሟቸው የዘመኑ አንጋሽና የጦር መሪ የነበሩት ኦሮሞው ፊታውራሪ ኃብተ ጊዮርጊስ ዲኔግዴ (አባ መላ) ናቸው።
ከወይዘሮ ዘውዲቱ ምኒልክ በፊት ሕንደኬ፣ ማክዳና ዮዲት የሚባሉ ሴት የኢትዮጵያ ርዕሳነ ብሔራት ነበሩ። ወይዘሮ ዘውዲቱ ምኒልክን ጨምሮ ከወይዘሮ ሣሕለ ወርቅ ዘውዴ በፊት የነበሩት የኢትዮጵያ ሴት ርዕሳነ ብሔራት ሁሉ በሥልጣን ረገድ ከዛሬዋ ርዕሰ ብሔር እጅግ የገዘፈ የሙሉ ሥልጣን ባለቤቶች ነበሩ።