>

የዘር መድልዎ ሰለባ  የነበረው (አቶ ወረታው ዋሴ)

የዘር መድልዎ ሰለባ  የነበረው
 አቶ ወረታው ዋሴ 
አየር መንገዳችን በፓይለቱ እይታ ሲገለጽ
    “የኢትዮጵያ ኩራት በሆነው አየር  መንገድ ውስጥ ወደ 30 ዓመት በአውሮፕላን አብራሪነት ስራ ተሠማርቼ  ስሰራ ብዙ ጊዜ በይበልጥ ላለፉት 8 ዓመታት በሀዘን አንገት የሚያስደፋኝ ብዙ ጉዳዮችን ብመለከትም ከሰሞኑ ከማያቸው የፌስቡክ  እንካ ሰላምታ ያህል ያዘንኩበት ጊዜ የለም በዚህ የተነሳ ይህን ለመፃፍ ተገድጃለሁ፡፡ ይህን ስፀፍ በተቻለ መጠን ብዙ ዋጋ የተከፈለበትን አየር መንገዳችንን ብሎም አገራችንን በማይጎዳ መልኩ በይበልጥ አስተዳደራዊ ችግሮች ላይ ለማተኮር እሞክራለሁ፡፡
  ከእናቱ እንድጀምር ይፈቀድልኝና አቶ ተወልደ ገ/ማርያም በቅፆል ስሙ ሜሲ (ብዙ ዋንጫ በመሰብሰባቸው ግቢ ውስጥ የወጣላቸው ስም ነው) እስቲ አንድ ጥያቄ ልጠይቃቸው ::ለመሆኑ በአየር መንገድ ታሪክ ውስጥ በዚህ አይነት ብዛት ሰራተኛ የለቀቀበት የተባረረበት ወይም የቀናው አምልጦ አገር ጥሎ የጠፋበት ጊዜ አለ ?  አምልጦ ያልኩበት ምክንያት ለምን እንደሆነ ይገበዋቷል፡፡ ለማያቁት ጥቂት ልናገር :: የአየር መንገድ ሠራተኞች በዋናነት አብራሪዎችና የአውሮፕላን ጥገና ሠራተኞች የተሻለ ስራ አግኝተው ወይም ከባርነት ለማምለጥ በሚሞከረባት ጊዜ በዘረጉት የውስጥና የውጭ መረጃዎች በመጠቀም ፓስፖርት እንደሚነጠቁ የኢትዮጵያ ህዝብ ሲሰማ ማመን እንደሚያቅተው እገምታለሁ፡፡ በቅርብ ጊዜ ከአብራሪዎች ጋር ባደረጉት ስብሠባ ይሄው ጥያቄ ተነስቶ አሁን ይሄን ለመመለስ አልችልም ማለታቸው የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡ አንድ ከዚህ ጋር በተያያዘ በቅርብ የሆነውን ልንገራችሁ ::በምን መልኩ እንደሆነ ግራ በሚገባ መልኩ ከዚህ የመረጃ መረባቸው ያመለጠ አንድ የአውሮፕላን አብራሪ በዋና አውሮፕላን አብራሪነት ተቀጥሮ ወደ ኩዌት (kuwait) ይሄዳል፡፡
    ይህ በመሆኑ ያበዱት አቶ /ተወልደ (ሜሲ) ከመንግስት ጋር ባላቸው የጠበቀ ግንኙነት በመጠቀም kuwait የጀመረውን ትምህርት አስገድደው አቋረጦ እንዲመጣ ካደረጉት በኃላ ወደ አንድ ዓመት የሚጠጋ ያለምንም ደሞዝ አስቀመጡት፡፡ ከኛ በመለየቱ አልቅሰን ሸኝተነው በደረሠበት ግፍ አልቅሰን ሲመለስ ተቀበልነው፡፡ ባረነት ከዚህ በላይ ምን ይገልፃዋል ?
    ጥያቄዬን ልቀጥልና አየር መንገዱን ለማስተዋወቅ ካወጡት ገንዘብ የበለጠ መቼስ ራስዎን ለማስተዋወቅ ያወጡት ሳይበልጥ አይቀርም እንጂ ከሌሎቹ አየር መንገድ ኃላፊዎቸፍ እርሶ በምን ተሽለው ይሄ ሁሉ ሽልማት እንዳገኙ ቢነግሩን ደስ ይለናል? ምክንያቱም የባርነት አስተዳደር ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ውጭ በዚህ ዘመን የትም ማግኘት አይቻልምና  ! ለማወዳደርም ይከብዳል፡፡  ይህንን አባባሌን ለማጠናከር ይረዳኝ ዘንድ ለመሆኑ ከአብራሪዎች ጋር ያለውን የመተዳድሪያ ደንብ ለመጨረሻ  ጊዜ መቼ ነው የተፈረመው ? ላስታውሳት  እርሶ ስልጣን ከያዙ በሁላ ምንም አልተፈመም::እንግዲህ የባሪያ አገዛዝ ሰራተኛው ላይ የሰፈረው ሰርዓት አልበኝነትና ህገወጥነት ጥግ የደረሠው safty ጥያቄ ውስጥ የገባው እዚህ ላይ ስለ safty ካነሳሁ አይቀረ ሁሉንም ማንሳት ባይቻልም በቅርብ ጊዜ የሆኑትን በጥቂቱ ልንገራችሁ * አንድ ቦይንግ 787 የመንገደኛ አውሮፕላን መንገደኛ እየጫነ በአፍንጫው  መሬት ላይ  የወደቀበትን
* አንድ MD-11 የጭነት አውሮፕላን እቃ እየጫነ በኃላው የወደቀበትን
* መሬት ላይ እየሄደ ያለ ቦይንግ 777 ከኤርባስ ጋር የተጋጨበትን
*  ታይቶ በማይታወቅ መጠን የአውሮፕላን ላይ አስተናጋጆች (cabin-crew) በስህተት  የሚዘረጉት የአደጋ ጊዜ መንሸራተቻ በያንዳንዱ ክፍል (department) ያለውን ችግር በጥቂቱ ያሳይልኛል ብዬ አምናለው ፡፡
 ይህ ሁሉ ከአቅም በላይ ያለረፍት በማሰራት እንዲሁም ሰራተኛው በፍረሃትና በጭንቀት ከመስራት የሚመጡ ጥፋቶች ለመሆናቸው ከርሶ በስተቀር ሁሉም ያምንበታል፡፡ የእርሶ መልስ ግን ሁሌም መንግስት ላይ የሚደረግ የፖለቲካ አሻጥር በማለት ከስራ ማበርና እንዳንዶችንም ወደ እስር መላክ ነው ፡፡
  ለመሆኑ ይህ ሁሉ የበረራ አስተናጋጆች በቅርብ ያገቡና የወለዱ ሳይቀሩ ትዳራቸውንና ቤተሰብ በትነው በየአገሩ የሚጠፉት ለምን ይመስሎታል ? ወደሚቀጥለው ጉዳይ ልውሰዳችሁ ፡፡
   ካፕቴን ዮሐንስ ሐ/ማርያም (ማይጋይቨር) ሁሉን እችላለሁ ስለሚል የወጣለት ቅጽል ስም ነው:: ኒኒበቀድሞው ፍላይት ኦፕሬሽን ሀላፊ የነበሩት የካፕቴን አማሀ ቀፀላ ምልምል ናቸው፡፡ እስኪ ከማያልቀው ግፋቸው  ጥቂቶቹን እንድናገር ይፈቀድልኝ፡፡ ይህን አሳዛኝ ግፋቸሁን አንተና ጥቂት ጓደኞችህ ስትጀምሩ እጃችሁን ያሟሻችሁበትን ( እዚህ ላይ ስሙን መጥቀስ  አስፈላጊ ሆኖ አላገኘሁትም) የግፋችሁን መጠን መቋቋም አቅቶት አማኑኤል ሆሲፒታል አእምሮው ተነክቶ ሲገባ ምን ተስማችሁ ? ያኔ የጀመርከው እኩይ ተግባር ነው እንግዲህ አባዜው እስከ ዛሬ ሳይለቅህ የረዳት አብራሪ ዮሐንስ ተስፋዬን ስም በአደባባይ ለማጠልሸት የአቶ ተወልደ ትእዛዝ ተቀብለህ በግፍ የተባረረውን የረዳት አብራሪ ዮሐንስ ተስፋዬን ውጤት በሚዲያ ለመናገር የወጣኸው፡፡  ኸረ ለመሆኑ ህጉን ባትፈራው እንኳ የሞራል ብቃቱ እንዴት ኖረኾ? ለዛውም ውሸት በተቀለቀበትና በተጋነነ መልኩ:: ረዳት አብራሪ  ዮሐንስ ተስፋዬ ከተናገራቸው መሀል *ከፈለኩ እንደ ሲጋራ አጠፋሀለሁ” የምትለዋ የተለመደች አባባልህን ብዙዎች ያውቋታል፡፡ አንድ ቀን  እሳቱ እንዳያቃጥልህ እንድትጠነቀቅ ወንድማዊ ምክሬን እሰጥኃለሁ፡፡
   ባለፈው ሳምንት ካፕቴል ሊሆን ያለውን አብራሪ ጉቱ ከማልን ጨምሮ የጣላችሁት እና ያባረራችሁት ምን ያህል ይሆን ? ያለማጋነን በዚህ ተግባራችሁ በአለማችን ቀዳሚውን ቦታ ትይዛላችሁ፡፡ ይህ ደግሞ ለአቶ ተወልደ ሌላ ዋንጫ ያስገኝ ነበር፡፡
   አሁን በኩራ ከ250 በላይ የውጭ ሀገር አብራሪዎች አሉን ተብሎ ሲነገር እና በጥቂቱ ለእያንዳንዱ ከነ ጥቅማ ጥቅሙ በወር ከ13,000 ዶላር በላይ የሚከፈላቸውን ጥቂት በማይባል መልኩ በተኩ ነበር፡፡ ይህ የግፍ ማነቆ ግን አየር መንገዳችን ብሎም አገራችን ላይ ከዚህ በላይ ጥፋት ማድረስ የለበትም እላለሁ ፡፡ ልቀጥል
  ካፕቴን ዮሴፍ ሀይሉ ብዙም ስለ እሱ ማለት አልችልም ጥሩ እና ቀና ልብ ያለው ነው ብል ብዙዎች ከእኔ ጋር ይስማማሉ፡፡ ባለፈው በሚዲያው ላይ የተናገረው አሳዛኝ ንግግሩ ግን የአፍ ወለምታ ብለን ብናልፈው ደስ ይለኛል፡፡
   የችግራችንን ጫፍ ፈረንጆች እንደምሉት tip of the iceberg ይህን ያህል ካልኩኝ ጥቂት የራሴን አስተያየት ተናግሬ ላብቃ፡፡ ፀጉራም አምበሳ አለ ሲሉት ይሞታል እንደሚባለው ሳይዘገይ መንግስት አየር መንገዱን በጊዜ ሊፈትሸው ይገበዋል፡፡ መንግስት ጊዜ አግኝቶ ፊቱን ወደ እኛ እስኪምያዞር ግን ለኢትዮጵያ ህዝብ እርግጠኛ ሆኜ የምናገረው የኢትዮጵያ ኩራት የሆነውን አየር መንገዳችንን ሁሉም ሰራተኛ በኃላፊነት እንደሚጠብቅ በእርገጠኝነት መመስከር እችላለሁ፡፡
  ይህ ከላይ የሰጠኋችሁ መረጃ አንድም ቃለ አጋኖ ሳይሆረው እንደ ወረደ ሀቁን ሳላዛንፍ እንደሆነ ልገልፅላችሁ እወዳለሁ፡
 አምላክ ኢትዮጵያን እና አየር መንገዳችንንይጠብቅልን!! “‘
Filed in: Amharic