>
5:13 pm - Thursday April 20, 9116

ህወሀት በ አማራው ህዝብ ላይ የነበረው የዘር ጥላቻና ግፍ በጥቂቱ  (ናትናኤል መኮንን)

ህወሀት በ አማራው ህዝብ ላይ የነበረው የዘር ጥላቻና ግፍ በጥቂቱ 
ናትናኤል መኮንን
አማራውን ነፍጠኛ እና ትምክህተኛ እያለ የሌላው ጎሳ እንዲነሳበት፣ የበሬ ወለደ የጥላቻ ዘመቻ በአፄ ሚኒሊክ ላይ በሰፊው በመክፈት እና በሰፈራ ሄደው የሚኖሩትን ዜጎች የአማራ ተወላጆችን አስወጡ በማለት ከተለያዩ ክልሎች በ2004 ዓም. ከደቡብ ክልል እንዲፈናቀሉ ከአስደረገ በኋላ አማራዎች አይደሉም ምሥራቅ ጎጃሞች ናቸው አለ፣ ቀደም ሲልም በአማራው ላይ ነፍጠኛ ትምክህተኛ የሚል ቅጽል ስም አሰጥቶ የጥላቻ መርዙን ከረጨ በኋላ ሰሜን ሸዋዎችን ነው ብሎ ለመከፋፈል ሞከረ
• በሰሜን ምዕራብ ጎንደር እና በወሎ ክፍላተ ሃገራት በኩል ያሉትን ሰፋፊ እና ለም ወረዳዎች ቆርሶ ተወላጁን እና ነዋሪውን አማራ በግዴታ አፈናቅሎ ወደ ትግራይ ክልል አጠቃለለ፣
• በምዕራብ ኢትዮጵያ በኩል በቦታው ያሉትን ኢትዮጵያውያንን፣ በተለይም አማራውን በማፈናቀል፤ ለአማራ ብሔር ጥላቻ ባለው የሕወሃት ዘረኛው የጎሳ ፓርቲ ታዛዥ በሆነው የአገው ተወላጁ በደመቀ መኮነን ፈራሚነት፤/በወቅቱ የአማራ ክልል ም/ፕሬዚዳንት ስለነበረ እና ለዚያ አገር ቆርሶ የመሸጥ ውለታው የሚኒስቴርነት አሁን ደግሞ የም/ጠ/ሚኒስቴርነት ምዕረግ የተሰጠው/ ከ60 ኪሜ በላይ ወደ ውስጥ ከ1000 ኪሜ በላይ ርዝማኔ ያለው ለም የእርሻ መሬት እና አፄ ዮሐንስ አንገታቸውን የተሰየፉላትን የዮሐንስን ከተማ ጨምሮ ለሱዳን ገፀ-በረከት ሰጠ፣
• ደርግ የሠራውን ወያኔ እያፈረሰበት እና በቀን በሚሊዮን የሚቆጠር ወጭ እያወጣ፣ ያለምንም እርዳታ እና ብድር የሠራውን በፓዌ የጣና በለስን፣ በጋምቤላ የአልዌሮን እንዲሁም በጎዴና ሌሎች አካባቢዎች የሠራቸውን ሰፋፊ የመስኖ ፕሮጀክቶች 21 ዓመት ሙሉ በከንቱ እንዲፈስሱ እና የእርሻ መሬቱ በጫካ እንዲወረር፣ በአገሪቱም የምርት እድገት እንዳይኖር አደረገ፣
• ዘረኛው የሕወሃት ፓርቲ ሥልጣን ሲይዝ ከ18 ዓመት በታች ዕድሜ የነበራቸው የገበሬ ልጆች በወቅቱ መሬት አላገኙም ነበር። ዛሬ ቢያንስ 38 ዓመት ይሆናቸዋል። ከዚህ ዕደሜ በታች ያለው እና ጎጆ ወጥቶ የሚኖር አርሶ አደር በሙሉ የሚያርሱት መሬት አጥተው፣ በጋምቤላ እና ፓዌ የሚገኘውን ሰፊ የመስኖ ቦታ ለአረቦች እና ለህንዶች ሰጠ – ለዚያውም ምርቱ ለአገር ውስጥ ፍጆታ ለማይውል እና የጋምቤላ እና መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰያምኑበት እና ሳይቀበሉት፣
• የዘረኛ ፖለቲካየን አልተቀበላችሁም በሚል በሽህዎች የሚቆጠሩ የአማራ አርሶ አደሮችን “ቢሮክራት” የሚል ቅጽል ስም በመስጠት መሬታቸውን ነጥቆ፣ ከቤተሰቦቻቸው ጋራ ጦም እንዲያድሩ ፈረደባቸው፣
• ኢትዮጵያዊ በኢትዮጵያዊነቱ እንዳይኮራ “ለወላይታው የአክሱም ሃውልት ምኑ ነው” ብሎ ዘረኛነቱን በይፋ አሳወቀ፣
• ከትግራይ ብሔር ውጭ ያለውን የንግዱን ማህበረሰብ በግብር ሰበብ አዳክሞ የንግድ እንቅስቃሴው በአንድ ጎሳ እጅ ውስጥ እንዲወድቅ አደረገ፣
• በ17 ዓመት የትጥቅ ትግል ወቅት በወያኔ እና በደርግ በኩል ያልሞተ የወታደር ቁጥር በባድሜ ሰበብ ሁለት ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከ60 ሽህ በላይ ንፁሃን ዜጎችን ከአስጨፈጨፈ በኋላ፣ ለኤርትራ እንዲሰጥ አስደረገ – ለዚያውም ኢትዮጵያ ልታሸንፍበት የምትችለውን ማስረጃ አልቀበልም ብሎ የወደቀ እና በአድዋ ጦርነት የተሻረ የጣሊያንን ማሥረጃ በመምረጥ- ለዚያውም ኢትዮጵያ በይገባኝ የመጠየቅ መብት እንዳይኖራት አስቀድሞ ፍርዱ ይግባኝ እንዳይኖረው በመማፀን – ለዚያውም ኢትዮጵያውያን የሕግ ባለሙያዎች ጥብቅና በነፃ እንቁም እያሉ በብዙ ሽህ ዶላር ለኢትዮጵያ ደንታ የሌለው ሰላቶ ጥብቅና እንዲቆም በመግዛት፣ • በሳሊኒ አማካይነት ጎጃም ድንበር የነበረውን የጣና-በለስን ከፍተኛ የመስኖ ፕሮጀክት በማፈራረስ ማሽነሪውን ዘርፎ ሱር ኮንስትራክሽን ብሎ ካምፓኒ መሠረተ፣ ለመስኖ ሥራው ደጋፊ ቱቦ ማምረቻ የነበረውን የፕላስቲክ ፋብሪካ በፕራይቬታይዜሽን ስም ወረሰው፣ በተመሳሳይ መልኩ በመላ አገሪቱ /በተለይም ጎንደር በጎጃም በወሎ በወለጋ በከፋ በአርሲ ክፍላተ ሃገራት/ ሜካናይዝድ እርሻ ዘመናዊ የእንስሳት እርባታ ጀምረው የነበሩትን የገበሬዎች አምራቾች የህብረት ሥራ ማኅበራት እና የመንግሥት እርሻዎች አፈራርሶ ማሽነሪዎቹን ወደ ኤርትራ በማጓጓዝ ኢትዮጵያ ወደ ጥንታዊውና ኋላቀሩ የማረሻ እርሻ እንድትመለስ እና የተጀመረው ዘመናዊው የግብርና ዘዴ 21 ዓመት ወደ ኋላ እንዲሄድ አደረገ፣ ታሪኩ ይቀጥል
Filed in: Amharic