>

የአብይ ዲቃሎች!! (ተስፋዬ ሀይለማርያም)

የአብይ ዲቃሎች!!
ተስፋዬ ሀይለማርያም
“I know he is a bastard, but he is our bastard” የሚባል አባባል አለ፡፡ ይህ  ንግግር እንደመመሪያ ተቆጥሯል፡፡ ንግግሩ የድሮው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የሃሪ ትሩማን ንግግር ነው፡፡
ትሩማን ይህንን የተናገረው ስለ አምባ ገነኑ የኒካራጓ መሪ ስለነበረው ስለ ሶሞዛ ክፋት ፣ ሌብነትና ነፍሰ-ገዳይነት ተጠይቆ ሲመልስ ነበር፡፡ በግርድፉ ሲተረጎም “ሰውየው ሌባና ነፍሰ-ገዳይ እንደሆነ እናውቃለን፡፡ ሌባም ነፍሰ-ገዳይም ቢሆን ፤ የኛው ነው፡፡” እንደማለት ነው፡፡ አቶ መለስ “የኛው የመንግሥት ሌቦች አሉን” ብሎን አልነበር? አዎ ሥርዓቱን እስካስቀጠሉልን ድረስ የኛው ሌቦችና ነፍሰ-ገዳዮችን ተንከባክበን እንይዛለን፡፡ Our Bastards.
በ1970ዎቹ መጀመሪያ ላይ የኒካራጓ ዋና ከተማ ማናጉዋ በመሬት መንቀጥቀጥ ብዙ ነዋሪዎቿን ከማጣቷም በላይ ከተማዋ  እንዳልነበረች ሆነች፡፡ ዓለም ይህንን አይቶ በዚያን ዘመን የገንዘብ መጠን 70 ሚሊዮን ፓውንድ አሰባስቦ ለችግሯ ደረሰላት፡፡ ይሁን እንጂ ሶሞዛ በቴሌቭዥን ቀረቦ በሁለት ዓይኖቹ እንባውን እያዘራ ምሥጋናውን ካቀረበ በሁዋላ ገንዘቡን በሙሉ ስዊዝ ባንክ የግል ሳጥኑ ውስጥ አስገባው፡፡ America’s Bastard.
ሰውየው በጊዜው የአምባገነኖች አምባገነን ይባል ነበር፡፡ እስረኞችን በሄሊኮፕተር ጭኖ አገሩ ውስጥ ወደሚገኘው እሳተ-ጎመራ በመውሰድ ከሰማይ ላይ ይወረውራቸው ነበር፡፡ ይህ ሳይበቃው መጠጥ ጠጥቶ ከሰከረ በሁዋላ ፤ ጋዜጠኞችን ሰብስቦ ሽጉጡን ጠረጴዛ ላይ በማስቀመጥ “ደፋር የሆነ በዚህ ሽጉጥ ይግደለኝ?” ይል ነበር፡፡  ይሄ ነበር እንግዲህ የአሜሪካ ዲቃላ፡፡
ዶ/ር አብይም የራሱ ዲቃሎች አሉት፡፡ ወይ አላሰራቸው ፣ ወይ ሥርአት አላስያዛቸው እንዲሁ የመጣውን ለውጥ እያደናቀፉ ተቀምጠዋል፡፡
የጋራ መግለጫ በሚል አገርን የሚበትን ንግግር የሚያደርጉ ፣ ወንጀል የሌለበትን የአዲስ አበባን ወጣት በረሃ ውስጥ ያሰሩ የአብይ Bastards  አሉ፡፡ ትጥቅ ፍቱ ሲባሉ ፈቺና አስፈቺ የለም የሚሉ ፤ በግብር ከፋዩ ገንዘብ ሸራተንና ሂልተን መጠለያ ተሰጥቷቸው “ብንፈልግ ኦሮሚያን መገንጠል እንችላለን” በሚል የሚደነፉና ከመሬት ተነስተው “ፊንፊኔ ኬኛ” የሚሉ  የአብይ ዲቃሎች አሉ፡፡
አብይ አቶ ተወልደ የተባለውን የአየር መንገዱን  አምባገነን ጫፉን ሊነካው አልፈለገም ወይም ፈርቶታል፡፡
ዶ/ር አብይ ሆይ ህግና ስርአት ሳይጠፋ ዲቃሎችህን አስወግድልን፡፡ ስለ እነ ኦነግ ፣ ጃዋርና ተወልደ ስትጠየቅ ፤ “I know they are bastards, but they are my bastards.” እንደማትለን እርግጠኞች እንሁን
Filed in: Amharic