>

አ.ዴ.ፓ ካለማፈሩ ማሳፈሩ!!! (ቹቹ አለባቸው)

አ.ዴ.ፓ ካለማፈሩ ማሳፈሩ!!!
ቹቹ አለባቸው
የዛሬውን የካቢኔ ሹመት ተመለከትኩት፡፡ ሴቶችን በስፋት ለማካተት መሞከሩ ጥሩ ነው፡፡ ጥያቄው፤ የሴቶቹ ቁጥር በርከት ማለቱ፤አልኩ ለማለት ነው ወይስ፤እውነት ነብስ ያላቸው ሴቶች ናቸው ወደ ስልጣን የመጡት? የሚለው ነው፡፡ እስኪ ሳንቸኩል፤ ይሄን ጉዳይ ቀስ ብለን እንመለከተዋለን፡፡ ብቻ አንዱ በጎ ነገር አድርገን እንመልከተው፡፡አጠቃላዩን የሹመት ሁኔታ ዘልየ፤ወደ አማራዎቹ የካቢኔ ተመዳቢዎች ልመለስ፡፡
መቸም ዛሬ በተካሄደው የካቢኔ ሹመት፤ከአዴፓ በለይ የሚያፍር አካል ይኖራል ብየ አልጠብቅም፡፡ አዴፓስ መቸም ከሀፍረት ጋር መኖሩን ተለማምዶታል፡፡ አሁን ችግር የሆነው፤በአዴፓ ላይ ትንሽ ተስፋ ጥሎ የነበረው የአማራ ህዝብ ጭምር ማፈሩ እንጅ፡፡ እኛ ለአማራ ህዝብ የሚመጥን ውክልና ፈለግን እንጅ፤እንዲህ የቁጥር ጨዋታ መች ጠበቅን፡፡ የተሰጡን የሚኒስትር ቦታዎች 4/5 መሰሉኝ፡-
ትምህርተ፤ ትራንስፖርት፤ ቱሪዝም፤ከተማ ልማት፡፡ ያው ለነዚህ ቦታዎች የተመደቡትን ሰዎችም አውቀናቸዋል፡፡ እነዚህ ሰዎች በሙያቸው ጥሩ ሊሆኑ ይችላሉ( ከጃን ውጭ ሌሎቹን በቅርበት ስለማላውቃቸው ነው)፤ነገር ግን እነዚህ ተሸሚዎቻችን፤ የአማራን ህዝብ የተወሳሰበ ፖለቲካ፤በፌደራል ደረጃ አጀንዳ አድርገውና ተሟግተው ማስከበራቸው ላይ እጅግ ሲበዛ እጠራጠራለሁ፡፡እንዴውም፤እኔ እስከማውቀው ድረስ ከተሸሚዎቹ መካከል( ከጃን ውጭ ) አንዳንዶቹ የፖለቲካ ሀሁ አጥንተው ስለመጨረሳቸውም እጠራጠራለሁ፡፡
ሙያና ፖለቲካ እንዲሁም የአስተዳር ችሎታ የተለያዩ ናቸው፡፡ ስለሆነም፤በእኔ ግምገማ፤ የዛሬው ሹመት፤ አማራን ጨረቃ ላይ ጥሎት ያለፈ ይመስለኛል፡፡እኛ የፈለግነው፤ ቁጥር አልነበረም፤ፍሬ ያለው ሰው በወሳኝ ቦታዎች ላይ፤በተለይም አማራ ሲገፋባቸው በኖሩ ታዎች ላይ እንዲመደብ እንጅ፡፡ የከተማን መሬት መጠበቅ፤መኪና መቆጣጠር፤ተማሪዎችን ወደ ት/ቤት ማስገባት፤ ወዘተ… እማ ድሮስ ማን ከለከለን? አማራ እንዳይደርስባቸው ተከልክለው የኖሩት የፌደራል መ/ቤቶች ዛሬም ለአማራ ተከልክለዋል፡፡ ብቻ ነገሩ ጥሩ አይደለም፡፡ በዛሬው እለት አዴፓና ዶ/ር አብይ በቁጥር ሸውደውን ነው ያለፉት፡፡
አንዳንዱ የዋህ፤የካቢኔዎቻችንን ቁጥር ተመልክቶ፤እንዲሁም የደመቀን መካተት ጨምሮበት፤ምን ችግር አለው? ሊልህ ይችላል፡፡ ችግርማ አለው፤ቁጥርና ደመቀ መኮንንን እማ እኮ ላለፉት 27 አመታትም አብረውን ዘልቀዋል፡፡ ችግር ሆኖ ከረመው እኮ፤ቁጥርና ደመቀ የአማራን ህዝብ አጀንዳና ጥቅም ከማስከበር አንጻር አቅመ ቢስ ሆነው መክረማቸው ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ በኩል የሚቀርብ መከራከሪያ ካለ ከወዲሁ ውድቅ ነው ለማለት ነው፡፡
አቶ ንጉሱ ጥላሁን፤ተረጋጉ፤ዶ/ር አምባቸውና መላኩ፤ለሌላ ቦታ ስለታሰቡ ነው፤ይሄም በቅርብ ቀን ይገለጻል ማለታቸውን ተመለከትኩ፡፡ ጎበዝ ሌላ ካቢኔ ይቋቋማል እንዴ? የካቢኔ ነገር እኮ ዛሬ አለቀ መሰለኝ፡፡ነው ለነዶ/ር አንባቸው የምትሆን፤ የኢህአዴግ/ አዴፓ ጽ/ቤት፤ምን አልባትም፤የአገሪቱ ፕሬዝዳንት፤ካልሆነም ዳግማዊት ትታው የሄደችው ቦታም አለ፤ኮሚሽንና ኤጀንሲ ቦታዎችም ገና አልተሾሙባቸውም ወዘተ… ሊሉን ይሆን? ዘንድሮ እኮ መቸም አንሰማው ጉድ የለም፡፡ አምባቸው መኮንንና መላኩ አለበልን ከካቢኔነት አግልሎ፤ተረጋጉ፤ቦታ ተይዞላቸዋል ማለት ምን ማለት ነው? ይሄ ነገር እኮ አይናችሁን ጨፍኑና እናሞኛችሁ እንደማለት ነው፡፡
እንግዲህ፤ለምን ወደዚህ ደረጃ እንደተደረሰ፤አዴፓም እራሱ አፍሮ ለምን እኛንም እንዳሳፈረን፤ ለማወቅ፤ነገሮች በራሳቸው ስለሚመሰክሩ፤ሳንቸኩል፤ነገሮችን በጥንቃቄ እንከታተል፡፡ እንዲህ ጨረቃ ላይ የጣለን አካል ማን እንደሆነም፤በግምት ሳይሆን፤በመረጃ ተመስርተን እንወቀው፤ያኔ ትግላችንን ከነሱ ጋር እናደርጋለን፡፡ ለጊዜው ግን፤አሻግረን አንመልከት፤ችግር ካለ ከቤታችን  ውስጥ መሆኑ አይቀርም፡፡ የዛሬው ሁኔታ የሚነግረን ነገር ቢኖር፤ ዛሬም ቢሆን ቤታችን ውስጥ የተላለኪነት አባዜ ያለቀቃቸው ቅሪቶች ያሉ መሆኑን ነው፡፡ ስለሆነም እነዚህን ቅሪቶች፤አንድም መክረን ማስተካከል ሊኖርብን  ነው፤ ያለበለዝያም፤ እንደነ እንቶኔ ፤ከነጭራሹ ከአዴፓ መሸኘት ነው፡፡
ከቤታችን ወጥተን ዙሪያችንን ስንቃኝ :-
በኦሮማራ ስም ሲምል ሲገዘት የከረመው ኦ.ዴ.ፓ በራስ ሰው የመታጠር (የህወሀትን ሌጋሲ) በማስቀጠል ወሳኝ የሚባሉ የስልጣን ቦታዎችን ተቆጣጥሯል:-
1) ጠቅላይ ሚኒስትር – ኦሮሞ
2) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር – ኦሮሞ
3) ፕሬዝዳንት – ኦሮሞ
4) የአዲስ አበባ ከንቲባ – ኦሮሞ
5) ዋና አቃቤ ህግ – ኦሮሞ
6) የግብርና ሚኒስትር – ኦሮሞ
7) የገቢዎችና ጉምሩክ ሚኒስትር – ኦሮሞ
8] የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጅ ሚኒስትር – ኦሮሞ
9) የውሃ፣ መስኖና ኢነርጅ ሚኒስትር – ኦሮሞ
11) የኢንደስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፓሬሽን – ኦሮሞ
12) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ -ኦሮሞ
13 )የሰላም (ብሄራዊ ደህንነት፣ ፌደራል ፖሊስ፣ ኢንሳ፣
ፌደራል ጉዳዮች) ሚኒስትር -ኦሮሞ
14) የገንዘብ ሚኒስትር – ኦሮሞ።
የአዲስ አበባ መገናኛ ብዙሃን አዲሱ መዋቅር የሹመት ዝርዝር:-
1. እናትአለም መለስ …ዋና ዳይሬክተር (ኦሮሞ)
2. ነጻነት አለሙ…………ም/ዳይሬክተር (ኦሮሞ)
3. ሳሙኤል ከበደ ……..ም/ዳይሬክተር (ኦሮሞ)
4. ዮሚ ተመሰገን…….……..ም/ዳይሬክተር (ኦሮሞ)
5. ካሳ ወ/ሰንበት…….. አማካሪ (ኦሮሞ)
6. ውብሸት ወልዱ……..ልዩ ረዳት (ኦሮሞ)
ብቻ ትግሉ ገና ነው!
Filed in: Amharic