>

"ስለ ንፁሀን አዲስ አበቤዎች ዝም አልልም!!!" (እየሩሳሌም ተስፋው)

“ስለ ንፁሀን አዲስ አበቤዎች ዝም አልልም!!!” 
እየሩሳሌም ተስፋው
* በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ‘ብሄሬ ተበደለ’ ካላልክ የሚጮህልህ ተበደልክ ብሎ ጥሪ የሚያሰማልህ ጥቂት ነው። ይህ ሁነት የአዲስአበቤ እጣ ፈንታ ነው ማለት ይቻላል። ‘አደገኛ ቦዘኔ ‘ ሲል የመንግስት ባለስልጣን ወይንም የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ተብዬ ቢዘልፍህ ቆዳው የሚቆጣ ስሜቱ የሚጎፈንን እምብዛም ነው። አዲስአበቤ ነሃ ! የብሄር ቀለም የለህማ ! 
በቅርቡ በአዲስ አበባ ከተማ በተፈጠረው አለመረጋጋት የከተማዋን ሰላም ከፖሊስ ጎን ሆነው ለማስጠበቅ የሞከሩ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ከተለያዩ አካላት መጠነ ሰፊ ጥቃት ተሰንዝሮባቸዋል ። በገጀራ ፣ በዱላ በድንጋይ ተቀጥቅጠዋል ። አትግደሉን ብለው አደባባይ በወጡበትም ወቅት ከፖሊስ በተተኮሰ ጥይት ህይወታቸውን አጥተዋል ።
በማግስቱም ፖሊስ ኮሚሽነሩ “የተገደሉት ከፖሊስ መሳሪያ ሊነጥቁ ሲሉ ነው” ሲሉ በንፁሀን ሟቾች ተሳልቀዋል ። ከዚህ ሁሉ በኋላም ፖሊስ በየሰፈሩ የሚገኙ ወጣቶችን ያለ ፍርድ ቤት ትእዛዝ በጅምላ በማፈስና አሰቃቂ ድብደባ በመፈፀም ከ2000 በላይ ንፁሀን ያለምንም የፍርድ ቤት ትእዛዝና ቀጠሮ በማንአለብኝነት ቤተሰብ ሊያገኛቸው ወደማይችልበትና በበሽታ በረሀብና በድብደባ ወደሚሰቃዩበት ያልታወቁ የጦር ካምፖች በማጋዝ በሰብአዊነታቸው ላይ አሰቃቂ ወንጀል እየፈፀመባቸው ይገኛል ።
በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ‘ብሄሬ ተበደለ’ ካላልክ የሚጮህልህ ተበደልክ ብሎ ጥሪ የሚያሰማልህ ጥቂት ነው። ይህ ሁነት የአዲስአበቤ እጣ ፈንታ ነው ማለት ይቻላል። ‘አደገኛ ቦዘኔ ‘ ሲል የመንግስት ባለስልጣን ወይንም የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ተብዬ ቢዘልፍህ ቆዳው የሚቆጣ ስሜቱ የሚጎፈንን እምብዛም ነው። አዲስአበቤ ነሃ ! የብሄር ቀለም የለህማ !
ከነገ ጀምሮ እስከረቡዕ ድረስ የሚቆይ በህገ ወጥነት ወደአፈና ተቋማት የተጋዙ የአዲስአበባ ወጣቶችን ለማስፈታት የሶሻል ሚዲያ ዘመቻ ተጠርቷል። በንቃት እንሳተፍበታለን። ጥሪው ግን የታፈኑት ወጣቶች እንዲፈቱ ብቻ ሳይሆን ህግ ተላልፈው አፈናውን የፈጸሙትን ተቋማትና ፓለቲከኞች በፍትህ አደባባይ እስከመሞገት የሚደርስ መሆን አለበት። አለዚያ መጪው ጊዜ ብሄረተኞች ለጫሩት እሳት ዘር ቆጥረው መጮህ የማንችለው ወገኖች ሁለተኛ ዜግነትን ባልታወጀ ህግ የምንቀበልበት ይሆናል።
በመሆኑም ማንኛውም ለሰብአዊ መብትና ለፍትህ የሚቆረቆር ኢትዮጵያዊ ሁሉ ከሰኞ ጥቅምት 5/2011 እስከ ጥቅምት 7/2011 ( October 15-17 2018 ) ድረስ “ስለ ንፁሀን አዲስ አበቤዎች ዝም አልልም” በሚል መሪ ቃል የሚካሄደውን የማህበራዊ ድረ ገፅ ዘመቻ በመቀላቀል
1)በየአካባቢው የታሰሩ ወጣቶችን ስም ዝርዝር ፎቶና የደረሰባቸውን ግፍ በመለጠፍ
2)ንፁሀኑ አዲስ አበቤዎች በአስቸኳይ እንዲፈቱ አሳሪዎቻቸውና ገዳዮቻቸው ለፍርድ እንዲቀርቡ የሚጠይቁ ፅሁፎች በግልፅ ደብዳቤ መልክ ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለፖሊስ ኮሚሽነሩና ለአዲስ አበባ ከንቲባ በመፃፍ
3 ) የተዘጋጁ ምስሎችን ፕሮፋይል ፒክቸር በማድረግ ወ.ዘ.ተ
ከንፁሀን ወገኖቻችን ጋር ብሎም ከፍትህና ከዲሞክራሲ ጎን መቆማችንን እናረጋግጥ!!
Filed in: Amharic