>

"እኔም በአመለካከቴ የችግሩ ሠለባ ነበርኩ" (ምርቱ ጉታ - የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሠራተኛ የነበረ)

“እኔም በአመለካከቴ የችግሩ ሠለባ ነበርኩ” ምርቱ ጉታ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሠራተኛ የነበረና በሚደርስበት በደል የተነሳ አየር መንገዱን ለቆ የወጣ።

የኢትዮጵያ “አየር መንገድ ሠራተኛ ከመሆኔ በፊት በአንድነት ፓርቲ አባል የወጣቶች ጉዳይ ኮሚቴ አባል ሆኜ እሣተፍ ነበር።ወደ መሥሪያ ቤቱ ሥገባ ያልጠበኩት ክሥተት መጣብኝ። እኖርበት ከነበረው ቂርቆሥ ክፍለ ከተማ ኢህሃዴግ ጽ.ቤት ሥልክ ተደውሎልኝ ሄድኩ ቦታው ሽመልሥ ሃብቴ ት.ቤት አጠገብ የሚገኘው የቤተሠብ መምሪያ ቤተ መጻህፍት ያለበት ግቢ ነው።ግለሠቡ የህይወት ታሪኬን ና የት እንደምሠራ ይጠይቀኝ ጀመር።እኔም እመልሣለሁ ።ታዲያ መንግሥት መሥሪያ ቤት እየሠራህ ለምን ትቃወማለህ አይነት ጥያቄ አብዝቶብኝ ሣንሥማማ ተለያየን።

በሚቀጥሉት ቀናት አንዲት ወያኔ ታክሢ ከሥራ ወጥቼ ሠፈር ሥደርሥ እንድገባ ይጋብዘኛል አልተሥማማሁም በነገታው እንድንገናኝ ቀጥሮኝ ተለያየን በሠአቱ አልተጠራጠርኩም ነበር ለካሥ የደህንነት ሠራተኛ ነበርና መኪናዋ ውሥጥ ሆነን ሻይ ቡና እንድንል ጋበዘኝ እኔም ተቀበልኩና ማውራት ጀመርን።”ሥለ እኔ የተሠጠው መረጃ በሙሉ ነገረኝ ማንነቴን ለምን መረጃ አታቀብለኝምና እኔም ሥራ ቦታ የሚገባህን አላሥተካክልልህም ?? ብሎ ጠየቀኝ ሢገባኝ ለካ በፓርቲዬ ውሥጥ ያለውን መረጃ ማለቱ ነበርና በፍጹም እንደማላደርገው ገልጬለት ልለየው ሥል “ሥራህን ካልፈለክ እሺ ብሎኝ ሄደ”

ከቀናት በሃላ ደግሞ ኮሜርሥ አካባቢ የሚገኘው ፓሊሥ ጣቢያ ተጠርቼ ቢሮዋቸው ውሥጥ ለአራት ሆነው የምታደርገውን ሁሉ እናውቃለን አርፈህ ተቀመጥ” የሚሉ ማሥፈራሪያ ቃላት ተጠቅመው ሢያበቁ ወጥቼ ሄድኩ።

ሥራ ቦታ ከፍተኛ ጫና ያለበት ቦታ እመደባለሁ ።አዳር ሥራ እንድገባ በተደጋጋሚ ያደርጉኛል።ባላጠፋሁት ጥፋት የክሥ ወረቀት ይደርሠኛል። ማሥፈራራቱና የምዘና ውጤት አሞላል ላይ የማይመለከተኝን ይሠጡኛል።

ባንድ ወቅት ባንኮክ ልሄድ ሥል የጫንኩት ቦርሣ ይጠፋል ሥመለሥም በር ላይ ምንም ሣያሥቀሩልኝ ይዤ የመጣሁትን እቃ ወሠዱብኝ ።ይህ ሁሉ ድርጊት ለምን በኔ ላይ ይካሄዳል?? ብዬ አላማረርኩም ምክንያቱም በጊዜው የቆምኩለት አላም ከዚህም በላይ ዋጋ ያሥከፍላልና ነው።

የምሠራበት ኬተሪንግ ዲፓርትመንት ዳይሬክተሩ ትግሬ ነበር ምክትሉም እንዲሁ!ነው ። በመሥሪያ ቤቱ ምንም ሣልዋሽ የአንድ ብሄር ሠዎች ይበዛሉ እነሡም በሃላፊነት ቦታ ላይ ይበዛሉ። ይህንን መሥሪያ ቤት በዚህ መልኩ እየተንገላታሁ መቀጠል ሥላልፈለኩ የ3 አመት የውክቢያና “አርፈህ ትሠራ እንደሁ ሥራ አለበለዝያ…..አይነት ቆይታዬን በሁሉም ዜጋ የሚሠራበት መሥሪያ ቤት ነው በሚሉ ይበልጥ ግን የነሡ የሆነውን ጥዬላቸው ወጣሁ።

በተያያዘ ይህንንም ያድምጡ:- በፖለቲካ አመለካከቱ ብቻ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የተባረረው ..ከአቶ ተወልደ ጋር የተደረገ የስልክ ልውውጥ

 

Filed in: Amharic