>

እንዲህ ነበር ወጉ ማእረጉ የቤተ መንግስቱ! (ብሩክ ሽመልስ)

እንዲህ ነበር ወጉ ማእረጉ የቤተ መንግስቱ!
ብሩክ ሽመልስ
አባ ውቃው ብሩ!
የቤተ መንግስት የወታደር ግርግር ቢባል አንድ ታሪክ ትዝ አለኝ፡፡ የአራት ኪሎው ጊቢ የዘብ ግርግር ሲያስተናግድ የዛሬው የመጀመሪያው አይደለም፡፡
አባ ውቃው ብሩ በምኒልክ ቤተመንግት በልፍኝ አሽከርነት አድገው በኋላ በዘውዲቱ ዘበን የዘበኞች አለቃ/የክብር ዘበኛ አዛዥ/ የነበሩ ሞገደኛ መኮንን ነበሩ፡፡
በነሃሴ ወር 1920 ዓ.ም አልጋ ወራሽ ተፈሪ ንግስቲቱን በአፋጣኝ ከስልጣን አውርደው ሊነግሱ የተጠነሰሰ ሴራ እንዳለ መረጃው ደርሶኛል ብለው ማናቸውንም አድማ ለመደምሰስ ግዴታዬ ነው፤ ይፍቀዱልኝ በማለት ንግስቲቱን ይጠይቃሉ፡፡
ተፈሪ እንዲህ ያለ ነገር አያስብም፤ አርፈህ ቁጭ በል ቢባሉም አሻፈረኝ በማለት ለያዥ ለገራዥ ያስቸግራሉ፡፡ ንግስት የዋህ ስለሆኑ ነው የነተፈሪ ተንኮል ያልታያቸው ነው ነገሩ፡፡
ንግስትም ወሬውን ለማጥራት በንጋታው ተፈሪን ቤተመንግት ጠርተው በጉዳዩ ሲመክሩ ዋሉ፡፡ከዛም ወሬው ከየት እንደመጣ እስኪጣራ አባ-ውቃው ሆዬ በጉዳዩ አለበት ከተባለ ከሌላ አንድ መኮንን ጋር ታስረው እንዲቆዩ ይወሰናል፡፡
በትዛዙ መሰረት እጅ ስጥ ሲባሉ “እኔ የምኒልክ አሽከር እንዴት ተደርጎ፤ አሻፈረኝ” ይላሉ፡፡ ከወታደሮቻቸው ጋር ሽለላውና ፉከራው ይጦፋል፡፡
ይህንን የሰማ አዲስአበቤ ወሬ ለመቃረም ቤተ መንግስቱን ያጥለቀልቀዋል፡፡ (ደጉ ዘመን፤ እንዳንተ ኢንተርኔቱ ሁሉ ተዘግቶበት ወሬ ጠሮበት ሲበረግግ የሚውል አልነበረም የዛ ዘበን አዲስአበቤ…ቀጥ ብሎ ግቢ መሃል ጉብ ነው! ሃሃሃሃ) በኋላ ላይ ተፈሪ በሽመል ጠርጎ ከግቢ እስኪያስወጣው ህዝቡ ፈነጨ፡፡
ወደ አባ ውቃው እንመለስ፡፡ ይንግስትን ደህንነት ባይኔ በብረቱ ካላየሁ ከምኒልክ መታሰቢያ ቤት ላይ ወጥቼ እታኮሳለሁ ብለው ገጀሩ፡፡ መልዕክተኞች ተላኩ፤ ሳላይ እንዴት ተደርጎ ሆነ፡፡ ንግስተ ነገስታት አንድ ቁጭራ የዘበኛ አለቃን እንዴት ሄደው ይጎበኛሉ፤ ይህ ዘውዱን ማስናቅ ነው አለች ተፈሪ… የሰው ማኛ! 🙂
ያኔ መንግስታችን እንደምታውቁት በሃሳበ-ዱሽ እና ደናቁርት አልነበረም የሚከበበው፡፡ ብልሃተኛ በየጓዳው አድፍጦ እስኪጠራ ይጠባበቃል፡፡ አንድ ልበ ብሩህ ከእልፍኝ ወደ አባውቃው የመሸጉበት የምኒልክ መታሰቢያ ስልክ ይዘርጋ እና ይነጋገሩ አለች፡፡ ተደወለ፡፡
“ምናባክ ነው ጊቢ ምትበጠብጠው?”
“ደህና ኖት ወይ ንግስት?”
“ደህንነት ይንሳህ!”
አባውቃው እጅ በሰንሰለት አሉ፡፡ ይሙት በቃ ተፈረደ፡፡ ወደ እድሜልክ ዝቅ ተደረገ፡፡ ግዞት ወደ አንኮበር!!
ወጉ፤ ማዕረጉ፤  ስነ-ስርዓቱ እንዲህ ነው!! የምን እልፍኝ ፊጥ ብሎ ስብሰባ ነው??!! የምን ፑሽ አፕ ነው??
በተመሳሳይ :-
ጃንሆይ እና ወታደሮቹ!
ታማኝ በየነ
የዛሬ 45 ዓመት ገደማ ከኮንጎ የተመለሱ ወታደሮች የአገልግሎት ክፍያ ይገባናል በማለት ጃንሆይን ብቻ ነው ማነጋገር የምንፈልገው በማለት ቤተመንግስቱን ጥሰው ገቡ ::ጃንሆይም ወታደሮቹን በሰላም አነጋግረው  መለሷቼው፡፡ ያች አጋጣሚ ግን ለደርግ መፈጠር ምክንያት ሆነች
Filed in: Amharic