>

ከፑሻፑ ጀርባ ሰርዓተ አልበኝነት ይሸተኛል!! (ግርማ ሰይፉ)

ከፑሻፑ ጀርባ ሰርዓተ አልበኝነት ይሸተኛል!!
ግርማ ሰይፉ
“አስር ፐሻ ተቀጥተው እራት ተጋብዘው ሄደዋል፡፡” የአቶ ዘይኑ መግለጫ ነው፡፡ የሁሉም ችግር ፈቺ ዶ/ር አብይ አህመድ የሚመስለው መብዛቱ ብዙም አያሰገርምም፡፡ ለማንኛውም እውነቱ ግን ወታደሮች ተሰባሰበው ከነ ሙሉ ትጥቃቸው የመንግሰት መቀመጫ ደጅ ደርሰዋል፡፡ ይህ ጉዳይ የሚናገረው ነገር አለው፡፡ በወታደር ቤት ይህን ያህል ስብስብ ጥያቄውን ምን ይሁን ጥያቄው ለማቅረብ ሲወያይ (ሲያሴር ላለማለት) ወታደራዊ ደህንነት የሚባል ነገር አልነበረም፡፡ ይህ ሁሉ ወታደር ያለ መሪ በዚህ ደረጃ መንቀሳቀስ መቻሉ አጃይብ የሚያስብል ነው፡፡ ነገ ደግሞ የአየር ሀይል ጀት ይዘው መጥተው ዶክተር አብይን ካላናገርን ሊሉ ነው፡፡ ዛሬ “ነበር“ የሚለውን የገስጥ ተጫኔን መፅኃፍ እና ጓድ መንግሰቱ ካላናገሩን የሚለውን የሚያስታውስ ነው፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒሰትር ይህ ነገር መለመድ ያለበት አይመስለኝም፡፡ በተለይ በዚህ በሸግግር ወቅት ተነሰቶ ደሞዝ አነሰኝ የመሳሰሉ ጥያቄዎች ተገቢ አይመስለኝም፡፡ ለዚህ የሽግግር ወቅት የሚመጥን “የአሰቸኳይ ጊዜ አዋጅ” ያስፈልጋል፡፡ ይህ እምነቴ አገርን ከማረጋጋት እና የደህንነትና የመከላከያ ሰራዊቱን ለማስልጠን ጊዜ መግዛት ስለሚያስፈልግ ነው፡፡ ይህ ጉዳይ በአዳራሽ ውስጥ ለሚደረግ ማንኛውም ዓይነት ሃሳብ የሚገድብ መሆን የለበት፡፡ ለመድገም ያህል የአደባባይ ሰላማዊ የሚባሉ ሰልፉች መቅረት አለባቸው፡፡ የአዳራሻ ሃሳቦች እና የሚዲያ ውይይቶች መበራከት ይኖርባቸዋል፡፡
በተለይ በመከላከያ፣ ፖሊስና ደህንነት መዋቅር ያሉ ሰራተኞች በከፍተኛ የአገር አንድነት ጥበቃ ላይ በማተኮር ለውጡን የሚቀላቀሉበትን የለውጥ ሂደት ከማከናውን አልፈው ጠመንጃ ይዘናል ብለው እጅ መጠምዘዝ መቆም አለበት፡፡ በትላንት እለት ግዳጃቸውን በብቃት ለተወጡት ለቤተመንግሰት የጥበቃ ልዩ ሀይል ከፍተኛ ምስጋና ይገባቸዋል፡፡ መሳሪያ ይዘን ቤተመንግሰት ካልገባን ለሚሉ ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት ያደረጉት ቁርጠኝነት ሁሉ ድርሻውን የመወጣት ጉዳይን ያስተምረናል፡፡
ለማንኛውም መብት መጠየቅ ማፈን በሚል እንደማይወሰድ እና ይህ ወቀት ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚጠይቅ መሆኑን ለማስገንዘብ የተፃፈ
መሆኑን እንድትረዱ አደራ እላለሁ፡፡ ለመቶ ሺዎች የደሞዝ እና ኑሮ ችግር የሚሰጥ የኢኮኖሚ አቅም ላይ አይደለንም፡፡ ጥቂቶች በቢሊዮን የትም ዘርተውት በተዓምር ያለች አገር መሆኗን መዘንጋት የለብንም፡፡ የወታደር ሲመለስ፣ ያስተማሪ፣ ቀጥሎ የሐኪም፣ እንዲህ እያለ የሁሉም ደሞዝተኛ ጥያቄ ተመሳሳይ ነው፡፡ መፍትሔውን ለመረጥ ነው መንግሰት ለመጠበቅ ወገባችንን ጠበቅ አድርገን ሽግግሩን በሰላም ለማለፍ የበኩላችንን ብናደርግ ምን ይመስላችኋል?
Filed in: Amharic