>

የአቶ ዳዉድ አነጋገር በንድፈ ሀሳብ ደረጃ ምን ማለት ነዉ?  (ታዬ ደንደአ)

የአቶ ዳዉድ አነጋገር በንድፈ ሀሳብ ደረጃ ምን ማለት ነዉ? 
ታዬ ደንደአ
 “ትጥቅ የሚፈታም የሚያስፈታም የለም” ብሏል። የዝህ ትርጉም ሰፊ ነዉ። ግን ሁለት ነገሮች በሚገባ መታየት አለባቸዉ። አንደኛዉ መንግስትን ዕዉቅና መንፈግ ነዉ። የኢትዮጵያ መንግስት የሚባል ነገር የለም እንደማለት ይመስላል!!
 
ብዙ ፓርቲዎች ከዉጭ መግባታቸዉ ይታወቃል። አመጣጣቸዉ ደግሞ  ለኢትዮጵያ መንግስት እውቅና ከመስጠት አልፎ ከመንግስት ጋር መስማማትን ያካትታል።  ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን ማክበር ላይ የተመሠረተ ነዉ። ሁሉም በሰላም እና በህግ መሠረት አላማዉን ለማሳካት መምጣቱ እሙን ነዉ ።
ይህ ጉዳይ ትጥቅ መፍታትን ይጨምራል። ምክንያቱም አንድ ፓርቲ ጠመንጃ ይዞ ለሰላማዊ ምርጫ መወዳደር አይችልም። ሁሉም ተፎካካሪ ፓርቲዎች በእኩል ሜዳ ላይ መንቀሳቀስ አለባቸዉ። አንዱ ታጥቆ ሌላዉ ባዶ እጁን ከሆነ ደግሞ እኩልነት የለም። ስለዝህ ከመንግስት ዉጭ ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ትጥቅ መፍታታቸዉ አግባብ ነዉ።
በዝህ ጉዳይ ላይ አቶ ዳዉድ ኢብሳ የሰጡት ሀሳብ ህግን እና ሎጅክን የሚቃረን ነዉ። ዋልታ TV እንዳስነበበን አቶ ዳዉድ “ትጥቅ የሚፈታም የሚያስፈታም የለም” ብሏል። የዝህ ትርጉም ሰፊ ነዉ። ግን ሁለት ነገሮች በሚገባ መታየት አለባቸዉ። አንደኛዉ መንግስትን ዕዉቅና መንፈግ ነዉ። የኢትዮጵያ መንግስት የሚባል ነገር የለም እንደማለት ይመስላል። ትጥቅ የሚያስፈታ የለም ማለት መንግስት የለም ከማለት አይተናነስም።
ሁለተኛዉ ደግሞ ህገ-ወጥነት ነዉ። ንግግሩ አቅም ስላለን ህግንም ሆነ መንግስትን አናከብርም እንደማለት ይመስላል። ትጥቅ የሚፈታ የለም ማለት ህገ-መንግስቱንም ሆነ ሌሎች ህጎችን አናከብርም ማለት ይሆናል። በጣም ገራሚ ጉዳይ ነዉ። መንግስትን ዕዉቅና መንፈግ እና ህግን አለማክበር ምን ይባላል? ለኢትዮጵያ መንግስት እዉቅና ካልሰጡ እና ህግን የማያከብሩ ከሆነ ከአስመራ ለምን መጡ?
ለማንኛዉም የኢትዮጵያ መንግስት መኖሩን ማወቁ አይከፋም። ህገ-መንግስቱን እና ሌሎች የሀገሪቱን ህጎች ማክበርም ግድ ይላል። መንግስትን እና ህግን መቀየር ይቻላል! ህገ-መንግስቱም ይፈቅዳል። ነገር ግን ህጋዊ አካሄድን መከተል ያስፈልጋል። ከህግ ዉጭ መሄድ ለማንም የማይጠቅም አማራጭ ይሆናል።
የህግ የበላይነት ይከበራል!
Filed in: Amharic