>
5:13 pm - Tuesday April 19, 8974

ከወልቃይት  ጠገዴ የተፈናቀሉ ወጣቶች በወልቃይት አማራዎች ላይ የሚፈፀመው ስቃይ ይናገራሉ  (ጌታቸው ሽፈራው)

ከወልቃይት  ጠገዴ የተፈናቀሉ ወጣቶች በወልቃይት አማራዎች ላይ የሚፈፀመው ስቃይ ይናገራሉ 
ጌታቸው ሽፈራው
 
~”አማራ ነን ስላልን ብዙ በደል ደርሶብናል”
 
~  “ወደ ትግርኛ ቀይራችሁ አምጡት፣ አማርኛን ልናጠፋ እየጣርን ነው ብለው ሶስት መቶ፣ አራት መቶ ብር ከፍሎ ነው አማርኛን ወደ ትግርኛ የሚተረጎመው።”
~”ወልቃይት ውስጥ ሀዘን  እንኳ መግለፅ አንችልም። ተከልክለናል……የእኛ አባቶች ደግሞ ግጨው በሚባል በርሃ ሄዳችሁ ካልሰለጠናችሁ ምሽግ ካልያዛችሁ እየተባሉ መሳርያቸውን እየተቀሙ ነው”
~” በሏቸው ካልተደበደቡ ካልተገደሉ አይለቁም እየተባልን ሌት ተቀን ነው የምንደበደበው።  አማርኛ ስለተናገርን።”
~”የፌደራል መንግስት ጣልቃ ገብቶ ያረጋጋልን።   ካልሆነ መኖርያ የለንም።”
~”ጓደኛዬ የአብይን ስቲከር ለጥፎ ስለነበር በመኪና እያራወጡ ገጭተውታል።  ሶስት ጥይት ተኮሰው ስተውት ነው የገጩት”
~”ጠፍተው የቀሩ የወልቃይት ጠገዴ ተወላጆች አሉ። እነ ማማዬ አንጋውም በልዩ ሀይል አንገታቸው ተቀጭቶ በግልፅ ሞተዋል። በእነሱ አጎበር ላይ ብዙ ሰዎች መሳርያቸውን ተዘርገዋል። ተደብድበዋል።”
~”አማራ ተከዜ ቀርቶ፣ ብድብዴ ተሻግሮ  እርፍ አይቆርጥም፣ ከተሻገረ እንዋጋለን፣ ታጠቁ፣ ሰልጥኑ” ተብለን “እኛ አማራ ነን አማራን አንወጋም፣ አንሰለጥንም” አልን።
~”ከበው እጅህን ስጥ አሉኝ።  ገሎ መሞት እንጅ እጅ መስጠት ባህላችን አይደለም ለአማራ ሕዝብ፣ ለወልቃይት ሕዝብ፣ እኔ አልሰጥም እሞታለሁ ብየ ቦታ ይዤ ስቀመጥ ሚሊሻውም፣ ህዝቡም፣ ሀገሩም ደረሰ”
~”ሰራተኛ ውል ገብቶ በአማርኛ ተፅፎ ወደ ክስ ሲገባ “ወደ ትግርኛ ቀይራችሁ አምጡት፣ አማርኛን ልናጠፋ እየጣርን ነው ብለው ሶስት መቶ፣ አራት መቶ ብር ከፍሎ ነው አማርኛን ወደ ትግርኛ የሚተረጎመው።”
“እኔ ሕዝባዊ ሚሊሻ ነኝ። ከመንግስቱ ጋር ያለያየ ማንነታችን አማራ ነው የሚሉትን እኛን አይወክሉም ብላችሁ በሉ ስንባል አይደለም እኛ አማራ ነን አልን።   ማንነታችን አማራ መሆኑን ዘጠኝ ክልል ቀርቶ፣ ዘጠኝ ሽማግሌ ከልሎ ይሰጠናል። ርስታችን ነው፣ ማንነታችን ነው። እስከ 83 ዓመተ ምህረት  በጎንደር ክፍለ ሀገር፣ በዳባት አውራጃ ነው ስንተዳደር የነበረው። ቅስና ይሁን ድቁና እንደ ሀይማኖታችን ስናመጣበት የነበረው ጎንደር ክፍለ ሀገር፣ ዳባት አውራጃ ነው።  እኛ አማራ ነን። ይህ ነው ሊያለያየን የቻለው።
ወልቃይት ውስጥ፣ የህወሓት ሚሊሻ የነበረው እና በአማራነቱ  በደል የደረሰበት አዳነ ይናገራል!
“አማራ ተከዜ ቀርቶ፣ ብድብዴ ተሻግሮ  እርፍ አይቆርጥም፣ ከተሻገረ እንዋጋለን፣ ታጠቁ፣ ሰልጥኑ” ተብለን “እኛ አማራ ነን አማራን አንወጋም፣ አንሰለጥንም”አልን። “ይህን የማታደርጉ ከሆነ መሳርያችሁን ታራግፋላችሁ (ታወርዳላችሁ) ተባልን፣ “ሕዝብ ነው የሰጠን” አልን። በዚህ ላይ ቅዋሜ እያለን ቆየን።
የመስቀል በዓላችን ልናከብር ወደ መስቀል አደባባይ ወጣን።  መስቀል አክብረን፣ ቄሶች ተመልሰው ሽፈራው ሰናይ የሚባል ቡና ቤት ገብተን ኩታራዎቹ (ወጣቶቹ) “ያች ምሰሶ ወደ አማራ ወደቀች ደስ ብሎናል ብለው ጭፈራ ጀመሩ። በአማርኛ ጭፈራ ሲጀምሩ። አማርኛ ጭፈራ ሲጀምሩ ባንዴራ ነው ያወጡ ብሎ ልዩ ሀይሉን  እንቦለሌ  አስከበቧቸው። ከዚህ መሃል ተኩስ ተታኮሱ። ሲታኮሱ ልዩ ሀይሉ ተመታ። እኔ ቤት እያለሁ ሕዝብ እየዘለለ ገባ። ልዩ ሀይሉ ሲደግንብኝ እኔም  መሳርያ አውርጄ ልቡ ላይ ደገንኩበት፣ ቆመ። ከዚህ በኋላ ከበው እጅህን ስጥ አሉኝ።  ገሎ መሞት እንጅ እጅ መስጠት ባህላችን አይደለም ለአማራ ሕዝብ፣ ለወልቃይት ሕዝብ፣ እኔ አልሰጥም እሞታለሁ ብየ ቦታ ይዤ ስቀመጥ ሚሊሻውም፣ ህዝቡም፣ ሀገሩም ደረሰ። ይህን ልጅ ከባችሁ አትግደሉት። የሚገድለውን አይተናል  ብለው እነ ካሳ ብሩ   ተናገሩ።  “በል እንፈልግሃለን፣ ምስክርነት” ብለው አሸብር ተቀብሎ ገሬ ለሚባል  ፖሊስ ሰጠው። ሊመሰክር ሄደ። ምንድን ነው ያየኸው ሲሉት “አዳነ አልገደለም፣ ራሳቸው ልዩ ኃይሎች ሲታኮሱ ልዩ ሀይል ነው የመታው” ሲል፣ “ምን አባህ እንዲህ ብለህ ትመሰክራለህቀጥቅጠው?”  ብለው ቀጥቅጠው፣ሰባብረው ጣሉት።  ጎንደር ሆስፒታል ይገኛል።
ከዚህ በኋላ ማንነቴን ሕገ መንግስት ይመልስልኛል። እሰዋለሁ፣ እጅ አልሰጥም፣ የተበተነ ንብረት ይበተን ብዬ ያን ጊዜ እንደወጣሁ በዳንሻ ዙሪያ  በጫካው ሰንብቼ ወደዚህ ስደውል “ና” እንደናንተ ያሉ ሰዎች አሉ ማንነትክን ጠይቅ ሲሉኝ መጣሁ።
አሁንም ባድማችን አንለቅም። ባህላችንም አይደለም። መንግስትም እንዲያውቅልን። ሄደን ብንሞትም ከቤተ ክርስትያናችን፣ ከደብራችን  መቀበር እንጅ በስደት አንቆምም። ……ማንነታችን ዛሬም አማራ ነው። ነገም አማራ ነው።
 መጀመርያ ጊዜ ክልል 1 ( ትግራይ ድንበሩ) ሶረቃ ወንዝ ነው ብለው ወሰኑ። እስካሁን ድረስ የእኛ ነው ብለውን በ2001 ዘመቻ አደረግን።  የህወሓት ሚሊሻ በብአዴን ሚሊሻ ዝመት ተብሎ ተደናግረን አብረን ዘመትን። እንደገና በ2006 ዓም  ዝመቱ ተባልን። ዘመትን። ያነም ሽቅብ ተኮሰ። እኛም ሽቅብ ተኮስን። ወንድማማቾች ነን አንገዳደልም ተባብለን ተለያየን። ፌደራል ይገባል ብሎ እያንጓለለን ይገኛል።
ከአማራ ጋር ግንኙነት ያላቸው፣ ማንነት የሚጠይቁ አሸባሪ ናቸው ተብሎ ገበሬዎች በቅጥቀጣ ለይ ይኖራሉ። ……ድሮም የሚታወቀው ተከዜ ነው። በ83 ዓም ህወሓት ሲነግስ  ለራሱ ነው የሰጠው እንጅ የወልቃይት ሕዝብ ወስኖ የሰጠው  መሬት የለም።
ሰራተኛ ውል ገብቶ በአማርኛ ተፅፎ ወደ ክስ ሲገባ “ወደ ትግርኛ ቀይራችሁ አምጡት፣ አማርኛን ልናጠፋ እየጣርን ነው ብለው ሶስት መቶ፣ አራት መቶ ብር ከፍሎ ነው አማርኛን ወደ ትግርኛ የሚተረጎመው።
Filed in: Amharic