>
5:13 pm - Saturday April 19, 7704

እነ አብዲ ኤሊ ላይ የተሰነዘረ የፍትህ በትር ምነው ለነ ጌታቸው አሰፋ  ሲሆን አቅም አነሰው?!? (ፍጹም አለሙ)

እነ አብዲ ኤሊ ላይ የተሰነዘረ የፍትህ በትር ምነው ለነ ጌታቸው አሰፋ  ሲሆን አቅም አነሰው?!?
ፍጹም አለሙ
 
 
* ታጥቦ ጭቃ እንዳይሆን ታስቦ ወቅታዊ ማሻሻያ ተደርጎበት እንደገና የተከተበ።
* ይህ  ኢትዮጵያን ለጥፋት የሚያዘጋጅ ግለሰብ ለፍርድ መቅረብ አለበት። ህወሀት እሱን ለማዕከላዊ ኮሜቴ የመረጠው ያለ መከሰስ መብቱ እንዳይነካ ነው። ይህ ደግሞ አገር አጥፊ ነው።
ጌታቸው አሰፋ ይባላል።በማዕረግ ሥሙ የብሔራዉ መረጃ ምንትሴ ዳይሬክተር ነው።እንደሚመስለኝ የሚንስቴር ደሞዝ ይበላ ነበር።የሀገር ደህንንነት(የስለላ) ሚኒስቴር ነበር ፣ክንፈ ከሞተ በኃላ ለ 17 ዓመት ያህል።
የሀገሪቱን ምስጥር ለብቻው የያዘ፣ማን ይታሰር፣ ይፈታ፣ ይቀጥቀጥ፤ ቶርቸር ይደረግ ፣ ከሀገር ይባረር፣ ሀገር አይግባ፣ ታፍኖ ይግባ… ወዘተን የሚወስን እስከ ቅርብ ጊዜ ዶ/ር ዓቢይ ሥልጣን እስኪይዝ ድረ ማለት ነው ከኃላ ሆኖ የሀገሪቱ ፈላጭ ቆራጭ ነበር።ኃይለማርያምንማ ሳሞራ እስኪያሾፍበት ድረስ አሽከሩ ነበር።
ግን 1 ሳምንት አለፈው ሥራ ገበታው ላይም የለም።።የታለ ልጁ የታለ?!
 ፎቶ አይነሳም።አይወድም ። እሱ ግን የሚሊዬኔቻችን ፎቶና ማንነት አለው።ይህንን የሚያነቡ የእኔው ፌስቡክ ጓደኞች ሰላዩች ሁሉ አሉት።
በ 20-30 000 ብር ሚኒስተር ደሞዝ ይበላ የነበረው ጌታቸው 2 ልጆቹንንየግል ዩንቨርስቲ ኢንዲያና “ስቴት” ውስጥ ያስተምራል።ቢያንስ ለ 2 ልጅ 120000 ዶላር ያወጣል።ከየት አመጣው።የታለ ልጁ የታለ?!
አንዳርጋቸውን ለማያዝ ለየመኖች በ”ካሽ” “ከተከፈለው”ብዙ ሚሊየን ዶላር ቆንጠር አርጎ ይሆን?ለመረካከብ ሲሄዱ በሳምሶናይት ካሽ ተይዞ ነው የተኬደው።ከረዱት የመኖች መሀል ሀለቱ ደብዛቸው ጠፍቷል አሉ።ስለዚህ….
 ውይስ ሌላ ገቢ አለው?ብር ወረሰ አይባል አባቱ የፓሊስ መኮንን ነበሩ።ወይስ በተለያዩ ሰዌች ስም ይነግዳል?ማን ያውቃል።ግን ሰሞኑን ደብዛው ጠፍቷል።የታለ  ልጁ?!ይኸው መቀሌ።ተመረጦ ደግሞ ሊመጣ ነው። እንደገና።
ጌታቸው የደህንነት መሥሪያ ኃላፊ ብቻ ሳይሆን ኃይለማርያምን ሳይቀር እጅ ጠምዛዡ ፣ሀይ ፕሮፋይል ሰዎች ሲያዙ በአካል የታሰሩበት ቦታ እይሄደ የሚያስፈራራ ሰይጣን ነው።ከጠቅላይ ሚኒስተር እስከ ከንቲባ የሚያዝ፣ዳኛን ውሳኔ የሚያስቀይር፣እስረኛ የሚታከምበት ሆስፒታል ሀኪም የሚያስፈራራ፣ የቀድሞ ፍትህ ሚንስትርን እንደሎሌው የሚያዝ ርህራሄ የሌለውና በመሰሎቹ በተሞላው መስሪያ ቤት ኢ-ሰብዓዊ ኢ-ኢትዬጵያዉ ድርጊቶች እንዲፈጸሙ የሚያዝ አውሬ ነው።የታለ ልጁ?!
አንድ ሊያስቆመው የቻለ ሰው ሳሞራ ነበር።ባለፉት 7 የጭንቅ ወራቶች  ስብሳባ ላይ ሳሞራ 2 ጊዜ እትቀመጠበት ድረስ ሂዶ እንቆታል ይባላል።ባይገላግሏቸው ምን እንደሚደርስ አይታወቅም ነበር።
 ጌታቸው የዚህ ለውጥ ተቃዋሚ ብቻ ሳይሆን ከነስብሀት፣ አባይ ፀሀዬና፣አባ ነፍሶና  ደብረጽዬንጋ ሆኖ በሚችለው ሀሉ ለውጡን  ሉያደናቅፍ ሞክሯል።ሳሞራ የለውጡ ደገፊ ባይሆን ኖሮ ዛሬ ለማና ዐቢይ እንደጌታቸው ፍላጎትም ቢሄን እስር ቤት ነበሩ ማለት ነው።
ሳሞራም ከሥልጣን ገለል ያለው ጊታቸው ከስራው ብቻ ሳይሆን ከከተማው ደብዛው ከጠፋ በኃላ ነው። ለዙህ የሳሞራ ሚና ምን ነበር?ወደፊት እናየዋለን። ሳሞራ ግን ለምን የለውጡ ደጋፊ ሆነ?እንቆቅልሽ ነው።ሌላ ጊዜ እመለስበታለሁ። ግን እንዴት የጌታቸው አጋር የሆነው ሰዐረ ኢታማጆር ሹም  ሆነ?ከጀርባም ዲል አለ?አናቅም።ሳዕረ ስለጌታቸው ሚያቀውን ተናግሮ ይሆን? ይህስ ለዓቢይም ሆነ ለጥገና ለውጡ እንቅፋት አይሆንም? ጌታቸው ከሥልጣን ውጪ ሆኖ ይተኛልን?አልተኛም።አየነው።
እንደማንኛውም ከፍተኛ የሕውሀት ባለሥልጣን እንደገንዳ ውሀ የተዘፈዘፈበት የሙስና ባህርስ ማነው ዋኝቶ የሚያወጣው? እናያለን።ብዬ ነበር ከወራቶች በፊት። ዛሬ ደግሞ ህግና ሥርዓት እንዲከበር እጠይቃለሁ።
የማሰሪያ ትዕዛዝ የወጣበት ሰው የፈለገው ድርጅት ለፈለገው ቦታ ሊመርጠው ይችላል።ግን ከህግ በላይ ሊሆን አይችልም።ስለዚህ ካለበት ቦታ ተይዞ ይህ አስገዳይ፣መዝባሪ፣ቶርቸር አስደራጊ፣ኢሰብአዊ ድርጉት እንዲፈጸም አዛዥ፣ይህ ለውጥ ተቃዋሚና ኢትዮጵያን ለጥፋት የሚያዘጋጅ ግልሰብ ለፍርድ መቅረብ ለበት።ካለበት።ታድኖ።
እሱን ለማዕከላዉ ኮሜቴ የመረጠው ድርጅት ፣ወያኔ ማለት ነው ይህን።ያደረገው የዚህ አጥፊ ግለሰብ ያለ መከሰስ መብቱ እንዳይነካ ነው። ይህ ደግሞ አገር አጥፊ ነው።
ምን ተይዞ ነው ጉዞ ታዲያ?!
ስለዚህ፥ብአዴንም ሆነ ኣህድድ ክከ እንደዙህ ዓይነት ድርጅትጋ አንድ ላይ ሆነው ኮአሊሽን ውስጥ ማለት ኢህአዴግ ውስጥ መቆየት አይችሉም።አይገባቸውምም።ይህ ሰውና ሌሎች የስጋ ወንደሞቹና ግንረ አበሮቹ ያሉበት ድርጅት በሚወስነው ውሳኔ ኢትዮጵያ አትመራም።ገዳይ አስገዳይ በሚሳተፍበት ድርጅት ውሳኔ ኢትዮጵያ መመራትም የለባትም ወይ ኢህአዴግ መፍረስ አለበት።ወይ ብአዴንና ኦህድድ ከኢህአዴግ መውጣት አለባቸው።ከዛ ፖርላማ ውስጥ  ያለው መቀመጫቸው በቂ ከሆነ ለብቻቸው ለ 2 ዓመት ምርጫ እሲኪካሄድ ይግዙ፤ ካለሆነ ሌሎች ፓርላማ ውስጥ ያሉትን የደቡብ፣የሶማሌና የአፋር ድርጅቶችን ጨምረው ይግዙ፤ያ ካልሆነ ደግሞ ፓርላማውን በትኖ ለአዲስ ምርጫ መዘጋጀትና እንደጊዚያዉ መንግስት ማገለገል ግድ ይላል።
እዚህ ላይ ነው እንጂ የለውጡ ቁምነገር፤ አለበለዚያማ  ታጥቦ ጭቃ እንዳይሆን ይሄ ሁሉ ነገር።
Filed in: Amharic