>

ስውሩ ሰው በግልጽ ተመልሶ መጥቷል!!! (ጌታቸው ሽፈራው)

ስውሩ ሰው በግልጽ ተመልሶ መጥቷል!!!
ጌታቸው ሽፈራው
ትህነግ/ህወሓት ጌታቸው አሰፋ የሚባለውን የቀድሞው የደሕንነት መስርያ ኃላፊ ማዕከላዊ ኮሚቴነቱን አስቀጥሎለታል።
 ትህነግ/ህወሓት እንደፓርቲ የበርካታ ኢትዮጵያውያን ነፍስ ቀጥፏል። ንብረት ዘርፏል። ተስፋ አጨልሟል።
ጌታቸው አሰፋ የሚባለው ጨካኝ ሰው ደግሞ  የበርካታ ኢትዮጵያውያን ደም እጁ ላይ አለበት።   በቅርቡ ወደ ሱዳን ፈረጠጠ ተብሎ ነበር። አቶ ጌታቸው በሀገር ደረጃ ለሚፈጠሩ ግጭቶች ዋናው አቀነባባሪ ነው ተብሎ ይጠረጠራል።
ጌታቸው አሰፋ የትህነግ/ህወሓት ብቻ ሳይሆን የኢህአዴግም  ማዕከላዊ ኮሚቴ ሆኖ ይቀጥላል።  ኢህአዴግ ደግሞ ገዥ ፓርቲ ነው፣ መንግስት ነው። ከዚህ መንግስት ውስጥ እነ ጌታቸው አሰፋ አካል ናቸው!
ብዙውን ጊዜ ትህነግ የመገንጠል አጀንዳ ያነሳል፣ አሁንም ስም የተገንጣይ ስም ነው። የሚገነጠለው ከኢትዮጵያ ነው። በዚህ ወቅት፣ በጌታቸው አሰፋ እና ጓደኞቹ ቆስሎ ትንሽ እፎይታ አገኘሁ ሲል እነዚህን አረመኔዎች መልሰው እያመጡ ነው። በዚህ ወቅትስ ትህነግ/ህወሓት የመገንጠል አጀንዳውን ማንሳት ነበረበት። መገንጠል አለብኝ ማለት የነበረበት እነ ጌታቸው ያቆሰሉት የኢትዮጵያ ሕዝብ ነበር! ከትህነግ/ህወሓት!
Filed in: Amharic