>
5:13 pm - Wednesday April 20, 8738

አባራሪና ተባራሪን ያፋጠጠው የብአዴን ስብሰባ፦ (አያሌው መንበር)

አባራሪና ተባራሪን ያፋጠጠው የብአዴን ስብሰባ፦
አያሌው መንበር
ብአዴን የመጨረሻና ብቸኛ እድሉ ይህ ስብሰባ ብቻ ነው። ወይ አማራ መሆን አልያም የህወሃት ፈረስነቱን ማስጠበቅ። መሀል. መስፈር አይፈቀድም!!
♦<<አቶ አለምነው መኮነን የአማራ ልጆች ደም እጅህ ላይ ስላለ ይቅርታ ጠይቀህ ስብሰባውን ለቀህ ውጣ>>
  ወንድወሰን ለገሰ 
.♦<<በህይወት የኖርኩት በገዱ ጥረት ነው፤ ገዱና አባይ ወልዱ በጫማ እስከማደባደብ ደርሰዋል>> ግዛት አብዩ
♦<<የወልቃይት ጉዳይ እና የፌደራሊዝም ጉዳይ ሲወሰን የተቃወሙ 65 ወታደሮች በመለስ ተባረዋል>>
  ምልስ ወታደር (ከአዊ ዞን)
♦ << የአማራ ህዝብ ከዚህ ጉባኤ የሚጠብቀው አመርራ መቀያየር አይደለም፤ መሰረተ ልማትም አይደለም።የማንነትና የወሰን ጥያቄ ሳይመለስ እንቅልፍ አንተኛም።ብአዴን ታሪካዊ ስህተት እንዳይሰራ ይጠንቀቅ>>
ከምስራቅ ጎጃም የመጣ ወጣት
ትናንት ከሰዓት በኋላ የነበረው የብአዴን ጉባኤ ከጠዋቱ በእጅጉ የተሻለና ፖለቲካዊ ጉዳዮች የተዳሰሱበት እንደነበር ተሳታፊዎች ተናግረዋል።በተለይም አራት ተሳታፊዎች ያነሷቸው ሀሳቦች መድረኩን የሚመጥኑ ነበሩም ነው ያሉኝ።
የጉባኤውን መድረክ መንፈስ ከቀየሩት ውስጥ ከዚህ በፊት በወልድያ፣ አዱስ ዘመንና ባህር ዳር አካባቢዎች የብአዴን አመራር ሆኖ ሲሰራ ቆይቶ በ2008 መጨረሻ ባህር ዳር ላይ እነአለምነውን በመሞገቱ የተባረረው  አቶ ወንድወሰን የተባለ ግለሰብ አለምነውን በህዝብ ፊት የሚገባውን ነገር ተናግሮታል ብለውኛል። አቶ ወንድወሰን አለምነው ብዙ ወጣቶች ለማለቃቸውና ብዙዎች ለመታሰራቸው ተጠያቂ ነው ካለ በኋላ አለምነውን ተሰብሳቢውን ይቅርታ ጠይቆ ስብሰባ እንዲወጣ ከመጠየቁ ጋር ተያይዞ አንድ ተሳታፊ የላከልኝ እንዲህ ሲል ነው <<መለስን አበበ ገለው እንዳዋረደወ አለምነውንም በህዝብ ፊት ወንዳለ ልኩን ነግሮታል>> ይላል።ወንድወሰን ለማለት ነው።
የብአዴን የ27 ዓመት ጉዞ የአማራን ህዝብ ለበደልና ለችግር የዳረገ ነበር፤ ለዚህ ዋናው ችግር ከፍተኛ አመራሩ ነው በማለትም ገልጿል።ጌታቸው ረዳ በጉባኤያችን ላይ የተገኘው አጋርነቱን ለመግለፅ ነው ወይስ የስራ መመሪያ ለመስጠት? በማለትም በአቶ ጌታቸው የተወከለውን የህወሃት ፅሁፍ ተችቷል።የተነበበው ፅሁፍ ትክክል አልነበረም ብሏል።
ሌላኛው ተናጋሪ በ2008 ዓ.ም የህወሃት ተላላኪ ነህ ተብየ ከማዕከላዊ ኮሚቴነት ተባረርኩ ያለው የቀድሞው የሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳዳሪ አቶ ግዛት አብዩ ሲሆን እርሱ ግን ለመባረሬ ምክንያቱ የመተማ እና የጠገዴ (ግጨው) መሬት ነው በማለት እውነቱን አፍርጦታል።የ42 ዓመታት የአማራን ህዝብ ችግር ያወሳው አቶ ግዛት የብአዴን አመራርም #ተለጣፊ ፣#ሪፖርተር  (ቀን ቀን ብኣዴን ማታ ማታ ህወሃት)፣ በትንሹ #ተቃዋሚ፣ እና #መሃል ሰፋሪ ተብሎ በ4 እንደሚከፈል ገልጿል።ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ ከህወሃት ጋር ግጭት  በይፋ እንደተጀመረ ያብራራው አቶ ግዛት በወቅቱም በአቶ ገዱና በአባይ ወልዱ መካከል ጫማ እስከመወራወር የደረሰ ግጭት ተከስቶ እንደነበር ለጉባኤተኛው ተናግሯል ብለውኛል።አቶ ገዱን በእጅጉ ያመሰገነውና ያደነቀው አቶ ግዛት በእርሱ ጥረት ቢያንስ ከእስራት እና ስቃይ እንደዳነ ተናግሯል።((ገዱና ግዛት የቅርብ ሰዎች መሆናቸው ይታወቃል።))
ሶስተኛው ተናጋሪ ከአዊ ዞን የመጣው ምልስ ወታደርና አሁን አርሶ አደር ነው የተባለ ሲሆን ከትግል ታሪክ ጀምሮ ያለውን አብራርቶ ህገመንግስቱ አማራን እንደማይወክል አስረግጦ ተናግሯል። የወልቃይት ጉዳይ እና የፌደራሊዝም ጉዳይ ሲወሰን የተቃወሙ 65 ወታደሮች በመለስ ተባረዋል>> ብሏል።ለዚህ ደግሞ ብአዴን አማራ አመራር ባለመኖሩ ነው በማለት የእነ በረከትን ኤርትራዊነት በአስረጅነት አቅርቧል።
አራተኛው እና የብዙሃኑን ሀሳብ አንስቶ ያንፀባረቀው ሌላኛው ወጣት ነው አሉ።የአማራ ህዝብ ከዚህ ጉባኤ የሚጠብቀው አመርራ መቀያየር አይደለም፤ መሰረተ ልማትም አይደለም።የማንነትና የወሰን ጥያቄ ሳይመለስ እንቅልፍ አንተኛም።ብአዴን ታሪካዊ ስህተት እንዳይሰራ መጠንቀቅ አለበት ብሏል።የወሰንና ማንነት ጉዳዮች በህዝብ እናስመልሳለን እንጅ ከእንግዲህ ብአዴንን አንጠብቅም አይነት የህዝቡን ስሜት ገልጿል።ወጣቱ ብአዴን የመጨረሻ እድሉ ይህ እንደሆነም አስምሮበታል ብለውኛል።.
……….
ዛሬ ህዝብ ፊት የሞገታችሁ ሁሉ ምስጋናችን በያለንበት ይድረሳችሁ።እድሉን ሳታገኙ ስለቀራችሁ ውስጣችሁ ያረራችሁንም ዛሬ እድል ታገኙና ስሜታችሁን ገልፃችሁ ጥሩ አቅጣጫ እንዲይዝ ታደርጉ ዘንድ ምኞታችን ነው።
በአጠቃላይ የትናንቱ የከሰዓት ውሎ የተሳካ ነበር።ዛሬም ውይይቱ  ቀጥሏል።እነ ቹቹ፣ የሻንበል፣ እነ ላቀ፣ እነ ፈንታ፣ ምግባሩ፣ ንጉሱ ገና አልተናገሩም።ብአዴን የመጨረሻና ብቸኛ እድሉ ይህ ስብሰባ ብቻ ነው።ወይ አማራ መሆን አልያም የህወሃት ፈረስነቱን ማስጠበቅ።መሀል ማስፈር አይፈቀድም።ምክንያቱም ምርጫ ዝርዝሩ ውስጥ የለምና።የጠራ አቋም መያዝ ያሻል።
Filed in: Amharic